Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነብዩን ማላቅና ማወደስ ወሰን ሲያልፍ

ነብዩን ማላቅና ማወደስ ወሰን ሲያልፍ
ትርጉሙ፡-
ቋንቋዊ ትርጉሙ፦ “ጉሉው” በዓረብኛ ወሰን ማለፍ ለምሳሌ አንድን ነገር በማወደስ ወይም በማውገዝ ከሚገባው በላይ መጨመር ማለት ነው::
ሸሪዓዊ ትርጉሙ ፦ በእምነትም ይሁን በአምልኮ አላህ የደነገገውን ድንበር መጣስ ማለት ነው፡፡
ሸሪዓዊ ብይኑ ሀራም (የተከለከለ) የሚለው ምድብ ውስጥ የሚጠቃለል ነው፡፡ ድንበርን መተላለፍ በዱንያም በአኺራ የከፋ እንደሆነ የሚገልፁና ከመፈፀምም የሚያስጠነቅቁ ማስረጃዎች በርካታ ናቸው:: አላህ እንዲህ ይላል፡-
يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ وَلَا تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ إِلَّا الْحَقَّ
‹‹እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡›› (አል ኒሳህ 171)
قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لَا تَغْلُوا فِي دِينِكُمْ غَيْرَ الْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعُوا أَهْوَاءَ قَوْمٍ قَدْ ضَلُّوا مِن قَبْلُ وَأَضَلُّوا كَثِيرًا وَضَلُّوا عَن سَوَاءِ السَّبِيلِ
«እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ከእውነት ሌላ የኾነን (ማለፍ) ወሰንን አትለፉ፡፡ በፊትም በእርግጥ የተሳሳቱትንና ከቀጥተኛው መንገድም (አሁን) የተሳሳቱን ሕዝቦች ከንቱ ዝንባሌዎች አትከተሉ» በላቸው፡፡ (አል ማኢዳህ 77)
ኢብኑ ዓባስ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “ድንበር ማለፍን ተጠንቀቁ ከእናንተ በፊት ለነበሩ ህዝቦች መጥፊያ የሆነው በሀይማኖት ድንበር ማለፍ ነው” ኢብኑ መስዑድ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል “አጉል አጥባቂዎች ጠፉ” ሶስት ጊዜ በመደጋገም አሉ፡፡
ዑመር ኢብኑል ኸጧብ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል “ክርስቲያኖች ዒሳ የመርየምን ልጅ በማወደስ ድንበር እንዳለፉት እናንተም እኔን በማወደስ ድንበር እንዳታልፉ፡፡ እኔ የአላህ ባሪያና መልዕክተኛው ብቻ ነኝ”
የዚህ ሀዲስ ትርጉም፡- ክርስቲያኖች ዒሳን ጌታ አምላክ በማድረግ ድንበር እንዳለፉበት እናንተም እኔን በማወደስ ድንበር እንዳታልፉ፡፡ እኔ የአላህ ባሪያ በመሆኔ አላህ የሰጠኝን ባህሪ በመስጠት ባሪያና መልዕክተኛ በሉኝ ማለት ነው፡፡
ይሁንና ትክክለኛውን መንገድ ሳቾች የነብዩን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ትዕዛዝ በመጣስና የከለከሉትን በመፈፀም ከፍተኛ የሆነን ተቃርኖ ፈጠሩ፡፡ ነብዩን ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም በማወደስ ድንበር አልፈው ክርስቲያኖች ዒሳ ላይ ካሉት የማይተናነሱ ቃላቶችን ተጠቀሙ ፡፡ኃጢያትን እንዲምር፣ ችግሮችን እንዲያስወግድ፣ በሽታን እንዲፈውስና የመሳሰሉትን የአላህ ብቻ መለያ ተግባሮችን እንዲፈፅም ለመኑት፡፡ ይህ ሁሉ በሃይማኖት ድንበር ማለፍ ነውና ከቅርብ ግዜ ወዲህ በአንዳንድ አካዳሚ ምሁራን የሚደጋገሙ ለነብይ፣ ለመልአክም ሆነ ለወልይ ወሰን ያለፈ ስልጣን የሚሰጡ ጥሪዎች ሁሉ ከንፁሁ የኢስላም አሀዳዊ ጥሪ ጋር የማይጣጣሙ የሽርክ ግብዣዎች መሆናቸውን ልብ ይበሉ!!