ብዙ
ሰዎች ኢብኑል ጀውዚ እና ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያ ይቀላቀሉባቸዋል፡፡ የመቀላቀሉ መንሰኤ “ጀውዚ” እና “ጀውዚያ”
የሚሉትን ቃላት ካለማስተዋል የመጣ ነው፡፡ ሁለቱ ዓሊሞች ግን በስምም፣ በኩንያም፣ በዘመንም፣ በሃገርም፣ በዓቂዳም
የተለያዩ ናቸው፡፡
1. ኢብኑል ጀውዚ፡-
ኩንያቸው፡- አቡል ፈረጅ
ለቀባቸው፡- ጀማሉዲን
ስማቸው፡- ዐብዱርረሕማን ኢብኑ ዐልይ ኢብኑ ሐሰን
ዘመናቸው፡- ከ510 እስከ 597 ዓ.ሂ.
የተወለዱትም የሞቱትም፡- በግዳድ ውስጥ ነው፡፡
ዐቂዳቸው፡- ወጥነት የለውም፡፡ በከፊል ወደ አሽዐርያ ያዘነብላል፡፡ ይህንን በመመልከት አሽዐርዮች ይጠቀሙባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሰለፍያን ዐቂዳ የሚያንፀባርቁባቸው ቦታዎችም ቀላል አይደሉም፡፡ እንዲያውም አቡል ሐሰን አልአሽዐሪን ክፉኛ የሚኮንኑባቸው ቦታዎች በተጨባጭ አሉ፡፡ ይህንን እውነታ ኢብኑ ረጀብ ዘይሉ ጦበቃቲል ሐናቢላ በተሰኘው ድርሳናቸው በከፊል ገልፀውታል፡፡ [1/414]
“ኢብኑል ጀውዚ” በሚል ቅፅል የታወቁበት ምክንያት “ዋሲጥ” አካባቢ በሚገኘው ግቢያቸው ውስጥ የጀውዝ ዛፍ ስለነበር ነው፡፡ በአካባቢው ሌላ የጀውዝ ዛፍ አልነበረም፡፡

2. ኢብኑ ቀይም አልጀውዝያ
ኩንያቸው፡- አቡ ዐብዲላህ
ለቀባቸው፡- ሸምሰዲን
ስማቸው፡- ሙሐመድ ኢብኑ አቢበክር ኢብኑ አዩብ
የኖሩበት ዘመን፡- ከ691 እስከ 751 ዓ.ሂ.
ዐቂዳቸው፡- የሰለፍያ ዐቂዳ ነው፡፡ የኢብኑ ተይሚያ ተማሪ የነ ኢብኑ ከሢር፣ ኢብኑ ዐብዲል ሃዲ፣ ኢብኑ ረጀብ፣ … ሸይኽ አናቸው፡፡
“ኢብኑል ቀይም” በሚል በአጭሩ ይታወቃሉ፡፡ ከስማቸው ተቀጥሎ የሚጠራው “አልጀውዚያ” ቃል መነሻው አባታቸው ደማስቆ ውስጥ በሚገኘው የአልጀውዚያ መድረሳ ሃላፊ ስለነበሩ ነው፡፡ እናም ኢብኑ ቀይም አልጀውዝያ ማለት የጀውዝያ መድረሳ ሃላፊ ልጅ እንደማለት ነው፡፡