አጥፊዎችን በስም ጠቅሶ ማስጠንቀቅ!!
ከሰለፎች ፈለግ!
ዛሬ ዛሬ ስለቢድዐ ማውራት ሙብተዲዖችን ማጋለጥ እንደ አፍራሽ እየተቆጠረ ነው፣ ከጠላት ጋር እንደማሴር፡፡ ይሄ አካሄድ ስሜታዊ ሽፋን ስለተሰጠው እንጂ ውድቅነቱ ለማንም አይሰወርም፡፡ እነዚህ የሰው ስም አታንሱ የሚሉ ሰዎች እራሳቸው የሚጠሉትን ስም ባደባባይ በማብጠልጠል የሚታወቁ ናቸው፡፡ እነዚህ አካሄዳቸው እርስ በርሱ የሚጣረስ የሆኑ ሰዎችን ወደ ጎን እንተውና ጥንት በሰለፎች ዘመን የነበረው አካሄድ ምን ይመስል እንደነበር እንመልከት፡፡ ከኢብኑ ተይሚያ በስተቀር ሁሉም የተዘረዘሩት ከሞቱ ከአንድ ሺህ አመት በላይ አልፏቸዋል፡፡
1. ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ ረሒመሁላህ በአንድ ወቅት “ሙዐላ ኢብኑ ሂላል ጥሩ ሰው ነበር በሐዲሥ ላይ ይዋሻል እንጂ” ይላሉ፡፡ በዚህን ጊዜ የሆነ ሱፊ ሰማቸውና “የዐብዱረሕማን አባት ሆይ! ሰው ታማለህ እንዴ?” አላቸው፡፡ ኢብኑ ሙባረክ ታዲያ “ዝም በል! ግልፅ ካላደረግን ሐቅና ባጢል እንዴት ይለያል?!” አሉት፡፡ (አል-ኪፋያህ፡ 9)
2. ዑቅባህ ኢብኑ ዐልቀማህ እንዲህ ይላሉ፡- “በአንድ ወቅት ከአርጣህ ኢብኑ ሙንዚር ጋር ነበርኩኝ፡፡ በቦታው ከነበሩ ሰዎች አንዱ ‘ከአህሉ ሱና ጋር እየተቀመጠ፣ እየተቀላቀላቸው ስለቢድዐ ሰዎች ሲወራ ግን ‘ተውን እንግዲህ ስማቸውን አታንሱ’ ስለሚል ሰው ምን ትላላችሁ’ ሲል ጠየቀ፡፡ የዚህን ጊዜ አርጣህ ‘እሱ እራሱ ከነሱ ነው፡፡ እንዳያታልላችሁ!!’ አለ፡፡ ይሄ የአርጣህ ንግግር አልተመቸኝምና ወደ አውዛዒ ሄድኩኝ፡፡ አውዛዒ እንዲህ አይነት ነገሮች ሲደርሱት ገላጭ ነበር፡፡ ጠየቅኩት፡፡ ‘አርጣህ እውነት ተናግሯል፡፡ ሐቁ እሱ ያለው ነው፡፡ ይሄ ሰውየ ስማቸው እንዳይነሳ ይከለክላል፡፡ ሰማቸው ካልተገለፀ እንዴት ሰዎች ይጠነቀቋቸዋል?!!’ አለ፡፡” (ታሪኹ ዲመሽቅ፡ 8/15)
3. ሙሐመድ ኢብኑ በንዳር የተባሉ ሰው ኢማሙ አሕመድን፡ “በውኑ እኔ እከሌ እንዲህ ነው፣ እከሌ እንዲህ ነው ማለት ይከብደኛል” ቢሉ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- “አንተም ዝም ካልክ እኔም ዝም ካልኩ መሀይም የሆነ ሰው ጤነኛውን ከበሽተኛው እንዴት ይለየው?!” (አልፈታዋ፡ 28/231) አሁንም ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁላህ “ትርፍ ፆም ከሚፆም፣ ትርፍ ሶላት ከሚሰግድ፣ ኢዕቲካፍ ከሚያደርግ ሰውና ስለሙብተዲዖች ከሚያወራ ሰው የትኛው ነው አንተ ዘንድ ይበልጥ የተወደደው?” ተብለው ቢጠየቁ “ቢሰግድ፣ ቢፆም እንዲሁም ኢዕቲካፍ ቢያደርግ ለራሱ ነው፡፡ ስለሙብተዲዖች ሲያወራ ግን ጥቅሙ ለሙስሊሞች ነውና ይሄኛው ይበልጣል” ብለዋል፡፡ (አልፈታዋ፡ 28/231)
4. አልኢማም አልሑመይዲ ረሒመሁላህ (የቡኻሪ ሸይኽ ናቸው) እንዲህ ይላሉ፡- “ወላሂ! ተመሳሳይ ቁጥር ባላቸው ከሃዲዎች ላይ ከምዘምት እነዚህን የአላህ መልእክተኛን ﷺ ሐዲሥ የሚመልሱት ላይ ብዘምት እመርጣለሁ፡፡” (ዘሙል ከላም፡ 228)
5. ኢማሙ አሕመድ እንዲህ ይላሉ፡- “ለቢድዐ ሰው ሃሜት የለውም!!” [ጦበቃቱል ሐናቢላ፡ 2/274]
6. ኢብራሂም አንነኸዒይ እንዲህ ይላሉ፡- “ለቢድዐ ሰው ሃሜት የለውም!!” [አልኢባና፡ 2/449]
7. ሐሰን አልበስሪ እንዲህ ይላሉ፡- “ለቢድዐ ሰው ሃሜት የለውም!! አመፁን ባደባባይ ለሚያወጣ አመፀኛም ሃሜት የለም፡፡” [ሸርሑ ኡሱሉ ሱና፣ ላለካኢ፡ 1/158]
8. አቡ ኢድሪስ አልኸውላኒ እንዲህ ይላሉ፡- “አዋጅ! አቡ ጀሚላ በቀደር አያምንም፡፡ እንዳትቀማመጡት!!” [አልኢባና፡ 2/449]
9. ኢስማዒል ኢብኑ ዑለያ እንዲህ ይላሉ፡- “ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ሳልጠይቀው፣ ጭራሽ ሳላነሳለት ጦልቅ ጋር አትቀመጡ” አለኝ፡፡ ሙርጂኣ ስለሆነ ነው፡፡ [አልኢባና፡ 2/450]
10. ዓሲም አልአሕወል እንዲህ ይላሉ፡- “ቀታዳ ዘንድ ተቀምጬ ነበር፡፡ ዐምር ኢብኑ ዑበይድ ስሙ ሲወሳ በክፉ አነሳው፡፡ ዑለማዎች ከፊሉ በከፊሉ ላይ እንደሚናገር አላውቅም ነበር ስለው አሕወል ሆይ! አንድ ሰው ቢድዐ ሲያንፀባርቅ ሰዎች ይጠነቀቁት ዘንድ ስሙ ሊጠቀስ እንደሚገባ አታውቅም እንዴ? አለኝ፡፡” [አልሚዛን፡ 5/330]
11. የሕያ ኢብኑ ሰዒድ አልቀጧን እንዲህ ይላሉ፡- “ሱፍያን አሥሠውሪን፣ ሹዕባን፣ ማሊክ ኢብኑ አነስን፣ ሱፍያን ኢብኑ ዑየይናን የሆነ ውንጀላ ወይም የዘገባ ድክመት ስላለበት ሰው ሁኔታ ዝም ልበል ወይስ ግልፅ ላድርግ? ብየ ስጠይቃቸው ግልፅ አድርግ አሉኝ፡፡” [ሸርሑ ዒለል አትቲርሚዚ፡ 1/49]
12. አቡ ሰለማ አልኹዛኢ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ሐማድ ኢብኑ ሰለማን፣ ማሊክ ኢብኑ አነስን፣ ሸሪክ ኢብኑ ዐብዲላህን ቢድዐ ስለሚፈጥር ሰው ነገሩ ግልፅ ይደረጋል ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡” [ሸርሑ ዒለል አትቲርሚዚ፡ 1/49]
13. ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ከነዚህ ቢድዐዎች ማስጠንቀቅ የግድ ይላል፡፡ ስማቸውን ነጥሎ መጥቀስ ካስፈለገም ይደረጋል፡፡” [አልፈታዋ፡ 28/233]
እስካሁን የተዘረዘሩት ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር፣ አቡ ኢድሪስ አልኸውላኒ፣ ሐሰን አልበስሪ፣ ኢብራሂም አንነኸዒ፣ ኢብኑ ሙባረክ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ አውዛዒይ፣ ዐርጧህ ኢብኑ ሙንዚር፣ ሐማድ ኢብኑ ሰለማ፣ ሸሪክ ኢብኑ ዐብዲላህ፣ ሱፍያኑ ሠውሪ፣ ሹዕባ፣ ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና፣ ቀታዳ፣ ኢማሙ አሕመድ፣ አልሑመይዲ እና ኢብኑ ተይሚያ ናቸው ረሒመሁላህ፡፡ በእርግጠኝነት የነዚህን ብዙ እጥፍ ስም መዘርዘር ይቻላል፡፡ ከነብዩ ﷺ አስተምህሮትም እንዲሁ ማጣቀስ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ያክል ፋጢማህ ቢንት ቀይስ ረዲየላሁ ዐንሃ ሙዓውያህ ኢብኑ አቢ ሱፍያንና አቡ ጀህም ለትዳር እንደጠየቋት ለነብዩ ﷺ ብታማክራቸው “አቡ ጀህም ዱላውን ከትከሻው አያወርድም (ሴት ደብዳቢ ነው)፡፡ ሙዓውያም መንቻካ ድሃ ነው፣ ገንዘብ የለውም፡፡ ይልቅ ኡሳማህ ኢብኑ ዘይድን አግቢ” ብለው ነው የመለሱላት፡፡ ዘገባው ላይ ጣትህን እንዳትቀስር ሙስሊም ናቸው የዘገቡት፡፡ [ሶሒሕ ሙስሊም: 3770] ስለዚህ ለማንም ተቃውሞና ጩኸት ብለን ይህን ጠንካራ መሰረት ያለው ሱና ገሸሽ ልናደርግ አይቻለንም፡፡ ሙብተዲዖች ላይ እንደ አስፈላጊነቱ ስማቸውን እያነሱ ጭምር መልስና ማስጠንቀቂያ ባይሰጥባቸው ኖሮ ዲኑ የማንም መጫወቻ በሆነ፣ ህዝብም ገደል በገባ ነበር፡፡ ደግሞም አስተውሉ፡ ከነዚህ የሰው ስም አታንሱ ከሚሉ ሰዎች ውስጥ የሰው ስም የማያነሳ አለ?! በጭራሽ!! “ስም አታንሱ” የሚሉት እራሳቸው በቢድዐ ቁንጮቆች ላይ የሚሰጠውን ሂስ ዝም ለማሰኘት እንጂ አነሰም በዛ እራሳቸውም የሰው ስም ከማንሳት የሚቆጠቡ አይደሉም፡፡
የአላህ ፈቃዱ ከሆነ በሌላ ተያያዥ ርእስ ልመለስ እችላለሁ፡፡