አካባቢያችንንና ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከበከሉ በርካታ መርዞች ውስጥ ሽርክና ቢድዓ በዋናነት ይጠቀሳሉና እነዚህን ሁለት አጥፊ የልብ ህመሞች በቁርአን በሓዲስ እንዲሁም በሰለፎች ግንዛቤ ለመደምሰስ መነሳት ይጠበቅብናል!
ሽርክና ቢድዓን ለመዋጋት በተነሳን ጊዜ ግን እነዚህን ሁለት መርዞች ፈልፍለው ወይም አዳቅለው በሹቡሃት እያደለቡ የሚበትኑ የሽርክና የቢድዓ አንጃዎችና ግለሰቦች መኖራቸውን እንዳንዘነጋ!! እነዚህን መርዝ በታኞች ሳንታገል ቢድዓንና ሽርክን እንገረስሳለን ማለት ከንቱ ትልም ነው!! የቁም ቅዠት!!
ሽርክና ቢድዓ እጅ ፣እግር እና አእምሮ ኖሯቸው እየተንቀሳቀሱ ሙስለሙን የመበከል አቅም የላቸው! የሚንቀሳቀሱትና የሚዘዋወሩት በሱፊዮች ፣ በአሽዓሪዮች ፣ በማቱሪዲዎች ራስ፣ ጀርባ እና እግር ነው! የሚሰራጩት በአሕባሾች፣ በኢኽዋኖችና፣ በተብሊጎች ምላስና ብእር ነው!!
ነብዩ የኸዋሪጆቹ ራስ ወደነበረው ግለሰብ እያመላከቱ ከጀርባው ስለሚወጡ ጫጩቶቹ አስጠንቅቀዋል — በኢባዳቸው እጅግ ጠንካሮች መሆናቸው ከመጠቆም ጋር! ይህ ጥንካሬ ግን በነብዩ አንደበት ከከክፉዎች ከመመደብ አላተረፋቸውም ።
ነብዩ ቢድዓን ብቻ ሳይሆን የቢድዓ ሰዎችንም እንድንታገል መክረዋል! የታገለውን አካል በኢማን መስክረውለታል!!
ኡለሞቻችን የበርካታ ጥመት አንጋቢ ግለሰቦችን እየጠሩ በማስጠንቀቃቸው።በአላህ ፈቃድ በርካቶች ተርፈዋል ከጥመት ተጣሪዎች መንጋጋ ወጥተዋል — አንዳንዶች የኡለሞችን ማስጠንቀቅ ላለመቀበል አሻፈረን ብለው እየተፈጩ ቢሆንም!
አላህ ይምራን!!
