Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢኽዋንን በጨረፍታ በዑለማዎች እይታ


ኢኽዋንን በጨረፍታ
በዑለማዎች እይታ

1. አሕመድ ሻኪር (ግብፃዊ)፡-
“የሸይኽ ሀሰነልበና እና የሙስሊም ወንድማማቾቹ ንቅናቄ የኢስላማዊ ደዕዋን ወደ አፍራሽ የጥፋት ደዕዋ የገለበጡ ናቸው፡፡ ኮሙኒስቶች እና አይሁዳውያን እንደሚረዱት በተጨባጭ እናውቃለን፡፡” [ሹኡኑ ተዕሊም ወልቀዷእ፡ 48] 
2. ኢብኑ ባዝ፡-
“አላህ መልካም ይዋልልዎትና ህዝቦቼ ወደ 73 ቡድኖች ይከፋፈላሉ፡፡ አንዷ ስትቀር ሁሉም የእሳት ነው የሚለውን የነብዩ ﷺ ሐዲሥ መሰረት በማድረግ ሺርካ ሺርክና ቢድዐዎች ያለባቸው የተብሊግ ቡድን እና ቡድንተኝነትና በመሪዎች ላይ በማመፅ ሰሚና ታዛዥ ባለመሆን ልዩነት የሚፈጥሩት ኢኽዋነል ሙስሊሚን እነዚህ ሁለት አንጃዎች ከጠፊዎቹ አንጃዎች ውስጥ ይካተታሉን?”
መልስ፡- ከ72ቱ ውስጥ ይገባሉ፡፡ የአህሉ ሱናን ዐቂዳ የጣሰ ከ72ቱ ውስጥ ይገባል፡፡ “ህዝቦቼ” ሲሉ የተፈለገው ለጥሪያቸው አወንታዊ መልስ የሰጡትና እሳቸውን መከተልን ያንጸባረቁትን ነው፡፡ እነዚህም 73ናቸው፡፡ የምትድነዋ ያቺ የተከተለቻቸውና በዲናቸውም ላይ የፀናችው ናት፡፡ በ72ቱ ውስጥ ግን ከሃዲም ይኖራል፤ ወንጀለኛ ይኖራል፡፡ ሙብተዲዕም ይኖራል፡፡ ብዙ ክፍል ነው፡፡
ጠያቂ፡- ስለዚህ እነዚህ ሁለት አንጃዎች ከ72ቱ (ጠፊ አንጃዎች) ውስጥ ይገባሉ ማለተ ነው?”
ኢብኑ ባዝ፡- አዎ! ከ72ቱ ውስጥ ናቸው፡፡” [ሸሪጥ ሸርሑል ሙንተቃ] ከመሞታቸው 2 አመት ቀደም ብለው ጧኢፍ ውስጥ የተናገሩት ነው፡፡
ሸይኹ ይህን ፈትዋ የሰጡት ከመሞታቸው ሁለት አመት ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው፡፡
3. ሙሐዲሥ ሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒ፡-
ጥያቄ፡- በዘመናችን የሚገኙት የሱሩርያና የኢኽዋን ቡድኖች ከሱና ከሚወጡ ቡድኖች ውስጥ ናቸውን?”
መልስ፡- ከአህሉ ሱና አይቆጠሩም፡፡ ክብረ ቢስ ናቸው፡፡ የሚቀረው በተናጠል አባላቶቻቸው ላይ ብይን መስጠት ነው፡፡ አባሎቻቸው ላይ በተናጠል ብይን መስጠት አንችልም፡፡ ምክንያቱም አላዋቂ መሀይም ሊሆን ይችላልና፡፡ የኢኽዋንና የሱሩርያን ሰበካ የሚያውቅ ወደዚያ የሚጣራና ለነሱ በጭፍን የሚሞግት የሆነው ቁንጮ ግን እሱ ከምትተርፈዋ አንጃ ውስጥ አይደለም ልንል ይቻለናል፡፡” [ቱሕፈቱል ሙጂብ፡ 10]
“ጥያቄ፡- ከኢኽዋን አልሙስሊሚን አንፃር የአህሉ ሱና ወልጀማዓ አቋም ምን ሊሆን ይገባል?”
መልስ፡- ከኢኽዋን አልሙስሊሚን አንፃር የአህሉ ሱና ወልጀማዓ አቋም መንገዳቸው የፈጠራ መንገድ እንደሆነ ይፈርዳሉ፡፡ በተናጠል አባላቱ ዘንድ ስንመጣ መንገዱን ካወቀ በኋላ የሚፀናበትም እንዲሁ ሙብተዲዕ ነው፡፡ መንገዱን ሳያውቅ እንዲሁ ኢስላምንና ሙስሊሞችን እረዳለሁ ብሎ የሚያስብ ግን እንደ ስህተተኛ ይቆጠራል፡፡” [ቱሕፈቱል ሙጂብ፡ 10]
“ሐሰን አልበና እና ሰይድ ቁጥብ ወደ አላህ በሚደረገው ጥሪ ላይ ኢማሞች (መሪዎች) ናቸው የሚል አለ” ተብለው ሲጠየቁ “አዎ ኢማሞች ናቸው ነገር ግን ኢማምነታቸው ለቢድዐ ባለቤቶች ነው…” ብለው ነው የመለሱት፡፡
4. ሸይኽ ፈውዛን
ጥያቄ፡- እነዚህ አንጃዎች ከ72ቱ ጠፊ አንጃዎች ውስጥ ይገባሉን?
መልስ፡- አዎ፡፡ ወደ ኢስላም እራሱን ከሚያስጠጋ ውስጥ በደዕዋ ወይም በዐቂዳ ወይም በሆነ የኢማን መሰረቶች ውስጥ የአህሉ ሱንና ወልጀማዐን ዐቂዳ የሚጣረስ ሁሉ ከ72ቱ አንጃዎች ውስጥ ይገባል፡፡ ዛቻውም ይመለከተዋል፡፡ በተቃርኖው ልክ ውግዘትና ዛቻም ይኖረዋል፡፡” [አልአጅዊባ]
5. ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ
ስለተብሊግና ኢኽዋን ቡድኖች ሲጠየቁ እንዲህ ብለው መልሰዋል፡-
“እነዚህ የተለያዩ አዳዲስ ቡድኖች መጤዎች ናቸው፡፡ በ14ኛው ክ/ዘመን ነው የተወለዱት፡፡ … ለምሳሌ የኢኽዋን ቡድን ከነሱ ዘንድ የገባ ወዳጃቸው ነው፡፡ ይወዳጁታል፡፡ ከነሱ ያልሆነን ከሱ ተቃራኒ ይሆናሉ፡፡ ከነሱ ጋር ከሆነ ግን ቆሻሻ ከሆኑ የአላህ ፍጡሮች ቢሆንም፣ ራፊዳ (ሺዐ) ቢሆንም ወንድማቸው ወዳጃቸው ነው፡፡ ለዚህም ነው አካሄዳቸው ያለፈ ያገደመን የሚሰበስበው፡፡ ሶሐባን የሚጠላ ራፊዲ ለምን አይሆንም?!...” [ፈታወል ዑለማእ ፊልጀማዓት ወአሠሩሃ ፊ ቢላዲል ሐረመይን]
6. ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ
“የኢኽዋን አልሙስሊሚን ቡድንን በተመለከተ ጎላ ካሉ መታወቂያዎቻቸው ውስጥ አንዱ ትክክለኛ ማንነታቸውን መደበቅ፣ መለዋወጥ፣ ይጠቅመናል ብለው የሚያስቡት ዘንድ መቀራረብ፣ ትክክለኛ ገፅታቸውን ግልፅ አለማውጣት ነው፡፡ ማለትም በሆነ በኩል ሲታይ ባጢኒያ ናቸው፡፡…
ሌላኛው ኢኽዋኖችን ከሌሎች የሚለያቸው እነሱ ሱናን አያከብሩም፡፡ የሱና ሰዎችንም አይወዱም፡፡ ምንም እንኳን ይህንን አደባባይ ባያወጡትም፡፡ ግና በተጨባጭ ሱናን አይወዱም፡፡ ወደሱና ሰዎችም አይጣሩም፡፡ ..” [ፈታወል ዑለማእ ፊልጀማዓት ወአሠሩሃ ፊ ቢላዲል ሐረመይን] የቻለ ሙሉውን ይስማ፡፡
ይህንን እንደ ሰደድ እሳት የተሰራጨ ብልሹ አስተሳሰብ የዑለማዎችን ፈትዋዎች በማጣቀስ፣ የኢኽዋኖች ከባባድ የአቂዳ ጥፋቶችን ሚዛናዊ የሆነና ለዐቂዳው ዋጋ የሚሰጥ ሰው አይቶ እንዲፈርድ በማቅረብ ማጋለጥ ያስፈልጋል፡፡ አቡበክር ኢብኑ ዐያሽ ረሒመሁላህ “ሱኒ ማነው?” ተብለው ሲጠየቁ ሱኒ ማለት “ስሜቶች (ቢድዐዎች) ሲወሱ (ሲጋለጡ) ለየትኛዋም ወግኖ የማይቆጣ ነው” ይላሉ፡፡