እንግዲህ “ቫለንታይን” ያሉት “የፍቅር ቀን” 24 ሰዓቱ ተገባዶ ሌላ የፍቅር 24 ሰዓት ጥበቃ የሚቀጥለውን ዓመትን በተስፋ. .
ቀኑ ተገባዷልና. .
ይደባደቡ የነበሩ ጥንዶች ድብድቡን ካቆሙበት ይጀምራሉ!!
ባ’ናት ባ’ናታቸው ይማግጡ የነበሩ ጥንዶች ወደ ውስለታቸው!! ዳይ!
አፍቃሪነት አላርጂኩ የነበረ ባል ትናንት እንደምንም አምጦ “ሃኒዬ. . “ ሲል አርቴፊሻል የአፍቃሪነት ተውኔት ለሰዓታት ሲተውን ደክሞታልና ዛሬ ወደ ነበረበት ሻካራነት ተመልሷል!! “ማነሽ ሴትዮ! ቁርስ ደርሷል?”
እስከዛሬ እቤት ቤት ቀዳዳውን ድሪያ ስትለብስና በዛ የነተበ ሻሽ ደግሞ ጸጉሯን ድብን አድርጋ ታስር የነበችው እመቤት ትናንት ያለ የሌለ ውበቷን ሰብስባ ተቆነጃጅታ፤ በዲነር ድሬስ አሸብርቃ ነበርና. . ሰዓቱ ተገባዷል! ለአንድ ቀን ያወለቀችውን ወንፊቱን ድሪያ ዳግም ትልበሰው!!
እሱስ ቢሆን ያንን የመነቸከ የቤት የቤት ቲሸርቱን ይገደግድ አልነበር? ለትናንቱ “ክብረ በዓል” ግን በነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረቫት ቀይሮትስ አልነበር? አሁን “የፍቅር” ቀነ ገደቡ ተገባዷልና. . “ኤጭ! የቱ ጋር ነበር ቲሸርቴን ያወለቅኩት?” እያለ ቤቱን በአንድ እግሩ ያቁም. . ! አረረ! በቦክስ ሳይለጋሽ በፊት ፈልጊለት. . !
በቀዩና በነጩ አልባሳት፤ አበባና፥ ስጦታ የታጀበው “የፍቅር ቀን” የዛሬ ጠዋቷ ጸሐይ ምስራቅ ከተሰኘው ቤቷ ፈንጥቃ ስትወጣ አለቀ!! ዳግም “ፍቅርን” ለማጣጣም አንድ ድፍን ዓመት እንጠብቃት?
እኛ ስማችን ሙስሊሞች ይባላል! እምነታችን ፍቅር ነው! ህልውናትችን በፍቅር ነው! ሁለመናችን ፍቅር ነው! ጌታችንን በማፍቀር ኖረን ጌታችንን በማፍቀር እንቀሰቀሳለን።
እምነታችን ፍቅርን አስተምሮናል! ሲያስተምረን ግን ለአንድ ቀን የሚቆይ አጭር ኮርስ አይደለም! ለውሃ አጣጫችን ፍቅርን ስንሰጥና ስንቀበል ኖረን በጌታችን እዝነት በቀጣዩም ዓለም እንቀጥለዋለን!
አንተ በፈረንጁ ቄስ ሃሳዊ የ24 ሰዓት "ፍቅር" ክፉኛ የተለከፍከው ወጣት ሆይ! ይህን መሰል የፍቅር ቃለምልልስ ከኮመኮምካቸው ፊልሞች ውስጥ በአንዱ እንኳን ታገኛለህን?
እመት ዓኢሻ ለባለቤቷ ሙሐመድ እንዲህ ስትል ጠየቀቻቸው. .
“አንተ ለእኔ ያለህ ፍቅር እንዴት ነው”
እሳቸውም . .
“ልክ ገመድ ላይ እንዳለ ቋጠሮ ነው!” (እጅግ ጠንካራ እና የማያወላውል) ብለው መለሱ።
ብልኋ እመት ዓኢሻም ከረዥም ግዜ በኋላ አረሳስታ መሆኑ ነው ዳግም ጠየቀች. . እሳቸውም መለሱ. . “ዓላ ሓሊሃ!” (ባለበት ነው!) [ሒልየቱል አውሊያእ፥ ሊሳን አልሚዛን፥ ፈዋኢድ አልመጅሙእ]
ይህ የሚያመላክተን እርሳቸው እናታችንን ዓኢሻ የሚወዷት ዓመት ጠብቀው ለአንድ ቀን ሳይሆን ፍቅራቸው ዘውታሪ እንደሆነ ነው!
ታዲያ ይህን መሰል ተምሳሌት እያለን
ፈረንጅ ቄስ ጋር ምን አስመለከተን?
እስኪ ይህንንም እንመርቅ. .
ኡሙ ሰለማህ ለባለቤቷ እንዲህ አለችው. .
“አንዲት የገነት የሆነች እንስት ባሏም እንዲሁ የገነት የሆነ ቢሞቱ ከርሱ በኋላ ምንም ካላገባች በገነት ውስጥ በአንድነት ያኖራቸዋል። እንዲሁም አንድ የገነት የሆነ ወንድ ሚስቱም እንዲሁ የገነት የሆነች ቢሞቱ ከርሷ በኋላ ምንም ካላገባ በገነት ውስጥ በአንድነት ያኖራቸዋል። ስለዚህ ስምምነት እናድርግ። አንተን ቀድሜህ ብሞት ሌላ ሴት አታግባ። እኔን ቀድመህ ብትሞት እኔም ሌላ ወንድ አላገባም?”
አቡ ሰለማህ ግን ስምምነቱ አልተቀበለም. . እንዲህ ሲልም ፍቃድ ቸራት. .
“በአዎንታ ተቀበዪኝ! እኔ ከሞትኩ ሌላ ወንድ አግቢ” ካላት በኋላ እንዲህ ሲል ፈጣሪን ለመነላት. .
“አላህ ሆይ! ከእኔ እልፈት በኋላ የማይበድላትም የማይጠላትም ከእኔ የተሻለ ባል ስጣት!” [ጦበቃት ሊ’ብኒ ሰዓድ]
የትኛው ኃያል ጥምር ፍቅር፥ የትኛው ልብ ከልብ ቁርኝት ይህንን መሰል ከባድ የፍቅር ትስስር ቃል ያስነግራል? ኢስላምን መሪ፤ ፍቅር የሆኑ ነቢይን ተምሳሌት ካላደረገ በቀር?
እኛ ጥንዳችንን በትዳር ስንቆራኝ ፍጹም የሆነ ክቡር ቃልኪዳን እንገባለን። ልባችንን የጉዳዩ ተቆጣጣሪ ለሆነው አላህ እጅ ነስተን እንሰጣለን። እርሱ እንዳሻው ይንከባከበናል ላሻውም አካል የትዳር አጋርነት ይመርጠናል። ይህ ነው እጹብ ድንቅ ያለ ልክ ፍቅር!!
እኛ ሌላውን ሦስት መቶ ስድሳ ምናምን ቀናት ከትዳር አጋራችን ጋር በጭቅጭቅ፥ በዱላ አሳልፈን ፌብሯሪ 14 ሲሆን ግን ለአንዲት ነጠላ ቀን ብቻ ፍቅር የምናሳይ ሰዎች አይደለንም። ፍቅራችንን ለማሳየት ዓመት አንጠብቅም። ስጦታ ልንሰጣጥ ካላንደር አንቆጥርም። “እወድሻለሁ” ፤ “እወድሃለሁ” ለመባባል 24 ሰዓታት ብቻ አይበቃንም!!!
እናማ እምነትህ ወይንም የህይወት አኗኗር ዘይቤህ የትዳር አጋርህን ከዓመት ቀናት ውስጥ ነጥለህ ለአንድ ነጠላ ቀን ልዩ ፍቅርን ስጣት የሚልህ እንደሆን ይህ በራሱ ባንተ ላይ ከፈጣሪ የመጣብህ ዓለማዊ ቅጣት ነው!
ዛሬማ የትዳር አጋር እንኳን ሳይኖራችው፤ ክቡር በሆነ ትዳር ሳይቆራኙ የቄስ ቫለንታይንን “የፍቅር ቀን” በድምቀት ሲያከብሩ እናያለን። በመሠረቱ ይህ የአንድ ቀን የዝሙት አዳር እንጂ ሌላ አይደለም። አንቺም ክብረ ንጽህናሽን ለቫለንታይን ቀን ስጦታ ካበረከትሽ ለቀጣዩ ደግሞ ልጅ ልታበረክቺ ነውን? አንተስ ያንን ቀን ረክሰህ ቀሪውን ልከኛ ልትሆን አማረህ?
ትክክለኛ ፍቅር ምን እንደሆነ የሚያስተምረንን ሐይማኖት እንተግብር። እርሱም ኢስላም ነው። የነቢያት ሁሉ ሐይማኖት። ያ ኢብራሂምን እና ሳራን፤ ሙሐመድን እና ዓኢሻን፤ ዓሊይንና ፋጢማን. . ፍቅር ያስተማረው የሆነውን የፍቅር ሐይማኖት «ኢስላም»ን የህይወት መሠረታችን እናድርገው። በሒደቱ ልባችን ምን ያህል የተረጋጋ እና ፍጹም ሰላማዊ እንደሚሆን እናያለን። ከዚያም እየደጋገመ ፍቅርን የሚቸረንን የፍቅር አጋር በፈጣሪ ፍቃድ እንጎናጸፋለን።
ሆኖም በሚያሳዝን ሁኔታ ይህን እውነታ የተጋረደባቸው በርካታ ጥመት የገባባቸው ልቦች አሉ። አላህ ይመልሳቸው።