Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

"ባለ ዲኗን ምረጥ!" አሉ ውዱ ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም።

"ባለ ዲኗን ምረጥ!" አሉ ውዱ ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም።
በዲንህ ጥሩ አቋም ላይ ላለኸው ወንድሜ: ዲኗን፣ ፀባዩዋን አይተህ አግባ። መስፈርትህ ዲን ካልሆነ ግን
① ለነብያዊው ምክር ትኩረት ነፍገሃል፣
② በራስህ ህይወት ላይ ቀልደሀል፣
③ የመጪ ልጆችህን ሐቅ ገሸሽ አድርገሃል፣
④ ባለ ዲኗ እህትህን ካልሆነ ቦታ የመውደቅ እድሏን በአንድ ሰው ከፍ አድርገሃል፣
⑤ ለማህበረሰብህ ተምሳሌት የመሆን ፣ ጥሩ ነገር የማበርከት እድልህን በእጅጉ አመንምነሃል።
ስለዚህ "ኋላ አስተካክላለሁ" እና መሰል ማመካኛ እየደረደርክ እራስህን እንዳትሸውድ። ዛሬውኑ ባለ ዲኗን ምረጥ። ካልሆነ ግን ወይ ስትነፍር ትኖራለህ። ወይ ትዳራችሁ ይነፍራል። ወይ ልጆችህ ንፍሮ ይሆናሉ።

ማሳሰቢያ
"የምትስተካከልስ የለችም ወይ?" እንዳይባል። ልትኖር ትችላለች። ግና የተስፋ ዳቦ ከማለም ከወዲሁ ለነብያዊ ምክር ዋጋ ሰጥቶ ሰበብ ማድረስ ይሻላል።

Ibnu Munewor