ትዝብተ FB!
በዚህ ፅሁፌ በአላህ ፍቃድ ዳሰሳ የማደርገው FB በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ ያስከተለውን ጉዳትና ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ነው። ርዕሱንም "ትዝብተ FB" ብዬ ሰይሜዋለሁ። ይህ ፅሁፍ ግላዊ እይታ በመሆኑ የተለየ ሀሳብ ያለውና እርምት የሚሰጥ ካለ ሀሳቡን በደስታ እቀበላለሁ!
መንደርደሪያ ሐሳብ!
ፌቢ እንደሚታወቀው መጠቀም ለቻለበት መልካም ነገሮችን ያዘለ መማማሪያ መተዋወሻ የተላያዩ ሐሳቦችን መለዋወጫ ከመልካም ሰዎች ጋር መገናኛና ጥሩ ስራዎቻቸውንም መመልከቻ ወንድማማችነትን እና እህታማማችነትን መፍጠሪያ መድረክ ነው።
ከጥቅሞቹ መካከል በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል፦
✔ የዲናዊ ትምህርቶችን መቅሰሚያ።
✔ በተለያየ የአለም ክፍል የሚገኙና በአቅራቢያቸው የቂርኣት እድልን ማግኘት ያልቻሉ ወንድምና እህቶች ዲናዊ ትምህርቶችን መከታተትል የሚችሉበት።
✔ የተለያዩ መሻይኾች ትምህርት የሚለቀቁበትን ፔጆች ለመጎብኘትና እውቀትን ለመሸመት።
✔ የተለያዩ የዳዕዋ መድረኮች ሲዘጋጁ መልዕክትን ማስተላለፊያነት መፅሐፍትም ሲዘጋጁ ለማስተዋወቂያነት ይጠቅማል።
✔ ሙስሊም ላልሆኑ ሰዎችም ኢስላምን ማስተዋወቂያና የኢስላምን ውበት ማሳያ ትልቅ የዳዕዋ መድረክ ነው ።
✔አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኛ መንገድም ነው።
እና ሌሎችም መሰል መልካም የሚባሉ ተግባራትን ለማከናወኛነት ጠቀሜታው የጎላ ነው። ለዚህ አላማ ምን ያክል እየተጠቀምንበት ነው የሚለው ሌላ ርዕስ ነው። ለጊዜው ተከድኖ ይብሰል።
ወደ ዋናው የዳሰሳ ሐሳብ ደርሰናል መልካም ንባብ!
በተቃራኒው ይህን መድረክ ለመልካም መጠቀም ላልቻለ ደግሞ ትልቅ የጥፋት ዓለም ነው! የሰው ልጅ በገዛ እጁ ራሱን ችግር ላይ የሚጠጥልበት ከዛም አልፎ ሌሎችን እርሱ የተዘፈቀበት የጥፋት ማጥ ውስጥ የሚከትበት ዱንያውንም አኼራውንም የሚያበላሽበት አደገኛ ስፍራ ነው።
FB ጎትቶ ካመጣቸው ችግሮች መካከል ዋና ዋናዎቹን በዝርዝር ለመዳሰስ እንሞክራለን።
በቀንደኝነት ከማስቀምጣቸው ውስጥ
✘ አንደኛ ከዒልም መዘናጋት ፦
በFB ምክንያት ኡማው ላይ ከተጋረጠው አደጋ አንዱና ዋነኛው ብዙዎቻችን FB ላይ ለረጅም ሰዓት በመጣድ ጊዜያችንን እያቃጠልን ከዒልም ማዕዶች መራቃችን ነው። ፌቢ የዲን እውቀት ለማግኘት እድሉን ያጡ እንደ መፍትሄ የሚጠቀሙበት ማስታገሻ እንጂ እድሉ የተመቻቸላቸው ቂርኣታቻውን ጥለውና አሻፈረኝ ብለው ወደ እርሱ ፊታቸውን የሚያዞሩበት መድረሳ አይደለም።
ቂርኣቱን አንተውም ብለን እንደምንም ታግለን የቂርኣት ቦታ የመጣንም ደግሞ ኡስታዙ እያስቀራ እኛ የሱስ ነገር ሆኖብን ፌቢ የምንከፍት ያገር ነን ብቻ መድረሳው ይቁጠረን ሌላ ምን ይባላል።
ይህን ሲያደርግ አይተሀው ምን እየሰራህ ነው ስትለው "ዒልም ፈልጌ" ነው የከፈትኩት የሚል ከሆነ መልሱን ለባለ አዕምሮዎች ትቸዋለሁ።
እንዲህ የምታደርግ ከሆነማ ምን አስመጣህ እዛው አትቀርም! አይባልም!!! ይልቁኑ መምጣትህ መልካም በርታ የሚያስብል ነው ግን ይታረም ነው የሚባለው። እጃችን ይፁም እውነት እውቀት ከፈለግን ዋናው የዒልም ቦታ ላይ ነን ራሳችንን መሸወድ ትተን የሚጠቅመን እናድርግ። ለጊዜው ፌቢውን ዝጋና ዒልምህን ሸምት እላለሁ።
አላህ ያግዘን!
✘ የተቅዋ መቀነስ እና የኢማን መድከም
ከዲናዊ እውቀት መራቅን ተከትሎና መልካሙም መጥፎውም ፣ ሙስሊሙም ካፊሩም ፣ መተቁም ፋሲቁም አዋቂውም አላዋቂውም ፣ ትንሹም ትልቁም ብቻ ምን አለፋቹ በያይነት ሕዝብ ወደ ሞላበት ዓለም በየሰዓቱ እየተመላለስን በምናያቸው በምንሰማቸው በምናነባቸው ክልክል ነገሮች ምክንያት ኢማናችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ የአላህ ፍራቻችን እየቀነሰ አብዛኞቻችን ላያችንን አሳምረን እንጂ ውስጣችን ባዶ ቀፍ ሆኖ እየተንቀሳቀስ ነው።
ወንዶች ከዒልም ማዕድ እየራቅን ፣ ከሰላተል ጀማዓ እየፎረፍን ላያችን ላይ በሚታይ ሸዓኢረል ኢስላም ላይ እየተዘናጋንና እያለዘብን እንገኛለን።
ኢማናችን ከመድከሙና ተቅዋችን ከመቀጨጩ የተነሳ ብዙ ክልክል ተግባራትን በመዳፈርና እንደ ቀልድ በመመልከት እንዲሁም የአላህን ትዕዛዛት ላለመፈፀም የተለያዩ ምክንያቶችን በመደርደር ላለመስራት ትግል ላይ እንገኛለን። ይህም በህይወታችን ላይ መጥፎ ጠባሳንና አሻራን እያኖረ ይገኛል።
ቆም ብለን እናስተውል!
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል…
መልካም ሆኖ ካገኙት እባክዎ ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር ያድርጉት።
【ሐይደር ኸድር ጥር 19/2009】