عَنْ سُفْيَان بْنِ عَبْدِ اللَّهِ قَال
قُلْت፡ يَا رسُولَ اللَّهِ! قُلْ لِي فِي الْإسلَامِ قَوْلاً لَا أَسْأَلُ عَنْهُ أَحَدًا غَيْرَك؛ قَالْ፡ قُلْ፡ آمَنْت بِاَللَّهِ ثُمَّ اسْتَقِمْ
رَوَاهُ مُسْلِمٌ
رَوَاهُ مُسْلِمٌ
ከሱፍያን ኢብኑ ዐብዲላህ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ካንተ ውጭ ሌላን የማልጠይቅበትን ነገር ንገረኝ” አልኳቸው። እሳቸውም “በአላህ አመንኩ በልና ከዚያም ቀጥ በል”አሉኝ።
[ሙስሊም ዘግበውታል]
[ሙስሊም ዘግበውታል]
በአላህ ዲን ላይ በተውሒድ ላይ ፀንተው የሞቱ ሰዎች፣ ሊሞቱ ሲሉ ሽልማታቸው እና ብስራታቸው ምን እንደሆነ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል፦
﴿إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا تَتَنَزَّلُ عَلَيْهِمُ الْمَلَائِكَةُ أَلَّا تَخَافُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَبْشِرُوا بِالْجَنَّةِ الَّتِي كُنتُمْ تُوعَدُونَ﴾ فصلت፡ ٣٠
“እነዚያ ጌታችን አላህ ነው ያሉ ከዚያም ቀጥ ያሉ አትፍሩ፤ አትዘኑም፤ በዚያችም ተስፋ ቃል ትደረግላችሁ በነበራችሁት ገነት ተበሰሩ በማለት በነሱ ላይ መላእክት ይወርዳሉ፡፡”
[ፉሲለት፡ 30]
[ፉሲለት፡ 30]
ይህ እንግዲህ ከተውሒድ ሽልማቶች ውስጥ አንዱ ነው። አላህ ደግሞ ብዙ ሽልማቶችን አምነው ቀጥ ብለው በዛው መንገድ ላይ ለሞቱ አስቀምጧል።
[ተውሒድ እና ሽርክ ከሚለው የሳዳት ከማል መፅሃፍ ከገፅ 69-70 የተወሰደ]

