ሙስሊሞች ዲናቸውን ተዘናግተው በተለያዩ ጎጂ ባህሎችና ተለምዶዎች ሲዘፈቁ ከመሰረታዊው የሃይማኖታቸው መገለጫ ጀምሮ ሁሉንም ግዴታቸውን እየረሱ እየዘነጉና እየተቀላቀለባቸው ይሄዱና ከሃይማኖታቸው የእምነትና የተግባር መሰረት እስከመውጣት ድረስ ይደርሳሉ።
በተለይ ሙስሊም ካልሆኑ ማህበረሰቦች ጋር የሚኖሩ ከሆነ አብዛኛውን ባህላቸውን ይወርሳሉ።
በማደናገሪያዎቻቸውና በሚፈጥሩባቸው ብዥታዎች ሰበብም ከበርካታ ኢስላማዊ ስርኣቶች ይዘናጋሉ።
በመሆኑም ይህንን ኢማናዊም ሆነ ተግባራዊ ኢስላማዊ ስርአት በጥልቀት ተገንዝበው ባህላቸው አድርገው ይተገብሩት ዘንድ ደጋግሞና ተንትኖ ማስተማሩ አማራጭ የሌለው ነቢያዊ ፈለግ ነው።
እነሆም ሰሞኑን በተከታታይ እያቀረብንላችሁ እንዳለው ሁሉ ዛሬም የምንመለከተው ርእስ ብዙሃን የተዘናጉበት የሂጃብ ርእስ ነው።
አላሁ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ሴትን ልጅ ካዘዘበት ነገር አንዱ ባእድ ከሚሆኗት ማለትም እርሷን ሊያገቡ ከሚችሉ ወንዶች ጋር ለሚኖራት ግንኙነት ያስቀመጠላት የሂጃብ ስርአት ነው፡፡
ሂጃብ የአማኝ ሴት መገለጫ የንፅህናዋ ማስታወቂያ ነው። እንዳትደፈርና ክብሯ እንዳይነካ መከላከያ ጋሻዋም ነው።
ሂጃቧን የጠበቀች ሴት በህይወት ጉዞዋ የነቃችና ለቁምነገርም የበቃች ናት ፡፡ ለራሷም ይሁን ለሌሎች የምታበረክተውን መልካም አስተዋፅኦ በፅናት እንድትወጣ ሂጃብ ታላቁ ደጋፊዋ ነውና፡፡
ምክንያቱም፡-
ለሰው ልጆች አጥፊና አውዳሚ ከሚባሉት ሁለት ፈተናዎች መካከል አንዱ የሆነውን የስሜታዊነት ፈተናን በሂጃብ ልጓም እንድትቆጣጠረው ስለሚያስችላት ነው፡፡
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የሚደረግ ልቅ የሆነ የሁለቱ ተቃራኒ ፆታዎች ግንኙነትና መቀላቀልም ከግለሰብ አልፎ ማህበረሰብን ያወደመ ከባድ ወረርሽኝ ነው፡፡
የታሪክ መዛግብትን ብናገላብጥ ይህ የወረርሽኝ ምችና ልክፍት አጣምሞ ጥሏቸው የጠፉና እየጠፉም ያሉ ህዝቦችን በአለም ላይ መመልከቱ ድብቅ ነገርም አይደለም።
ስሜትን በተመለከተ ያላቸው እይታም ልጓመ-ቢስና ልቅ በመሆኑ ለራሳቸውም ይሁን ለሌሎች መልካምና ጠቃሚ ነገሮችን የማበርከት መቅኔያቸው ፈስሷል።
በየትምህርት ገበታው፣ በስራ ቦታዎች፣ በየመዝናኛውና በየጎዳናው ሳይቀር ፍፁም ዘግናኝና እንስሳዊ ግንኙነቶች እየተንሰራፉ የሚገኙትም ለዚሁ ነው።
ፈጣሪ አምላካችን የደነገገልንን ተስማሚና ምቹ ህጎች ከመጣሳቸው የተነሳም የሚደሰቱበትና የሚረኩበት ጠፍቷቸው ከእንስሳውም ከግኡዙም አካል ጋር ለስሜታቸው መታገልን ከተያያዙት ሰነባብቷል፡፡
ከዚህም ኣልፈው በተመሳሳይ ፆታዎች መካከልም የሚያደርጉት ግንኙነታቸው እነሱ ዘንድ ጭራሽ ጋብቻ እስከመባልም ደርሷል።
ይህም ለናሙና ያህል የተገለፀ እንጂ የዚህ የዘቀጠ ግንኙነት አራማጆች አጠቃላይ ሁኔታና የዘቀጡበትን የጥፋት ማእበልን እንዘርዝር ቢባል ብእሮችም ወረቀቶችም የሚወጡት አይሆንም ፡፡
እንደሚባለው “ የሚገባው በጥቆማ ይገባዋል” በማለትም በዚህ ብንወሰን ይሻላል፡፡
ኢስላም ከዚህ አይነት መስመር ዘለልና ፈር ለቀቅ አካሄድ የሰውን ልጅ ለማዳን ችግሩን ለመቅረፍ ወንዱም ሴቷም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ አስተምሯል።
የዚህም ትምህርት አንዱ ክፍል ሴት ልጅ ከባዕድ ወንዶች ገላዋን፣ ውበቷንና ጌጦቿን ባጠቃላይ ወንዱን ለስሜታዊነት የሚያነሳሳውን መስህቧን በሙሉ ደበቅ እንድታደርግ የሂጃብ ወይም የመሸፋፈን ህግ ደንግጓል ፡፡
ይህንን ድንጋጌም እንዲህ ሲል አምላካችን አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ገለፀው ፡-
« وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُون َ» [٢٤:٣١]
📃«ለምእምናትም ንገራቸው፡-
• ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ (ሰበር ያድርጉ)።
• ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡
• ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ፡፡
• ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡
• (የውስጥ) ጌጣቸውንም
~ ለባሎቻቸው
~ ወይም ለአባቶቻቸው
~ ወይም ለባሎቻቸው አባቶች
~ ወይም ለወንድ ልጆቻቸው
~ ወይም ለባሎቻቸው ወንድ ልጆች
~ ወይም ለወንድሞቻቸው
~ ወይም ለወንድሞቻቸው ወንድ ልጆች
~ ወይም ለእህቶቻቸው ወንድ ልጆች
~ ወይም ለሴቶቻቸው
~ ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ)
~ ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለሆኑ ተከታዮች
~ ወይም ለነዚያ የሴቶችን ሐፍረተ ገላ ላላወቁ ሕፃኖች ካልሆነ በስተቀር አይግለጹ፡፡
• ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው (መሬትን) አይምቱ፡፡
👉ምእመናኖች ሆይ
❗ ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡»
• ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡
• ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ፡፡
• ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡
• (የውስጥ) ጌጣቸውንም
~ ለባሎቻቸው
~ ወይም ለአባቶቻቸው
~ ወይም ለባሎቻቸው አባቶች
~ ወይም ለወንድ ልጆቻቸው
~ ወይም ለባሎቻቸው ወንድ ልጆች
~ ወይም ለወንድሞቻቸው
~ ወይም ለወንድሞቻቸው ወንድ ልጆች
~ ወይም ለእህቶቻቸው ወንድ ልጆች
~ ወይም ለሴቶቻቸው
~ ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ)
~ ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለሆኑ ተከታዮች
~ ወይም ለነዚያ የሴቶችን ሐፍረተ ገላ ላላወቁ ሕፃኖች ካልሆነ በስተቀር አይግለጹ፡፡
• ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው (መሬትን) አይምቱ፡፡
አላህ ባነበብነውና ባወቅነው የምንጠቀም ያድርገን።
