ቃላቶቻችንን እንመዝን!
⭕
ከነዚህም መሀል የተወሰኑትን ለምሳሌነት ስንመለከት፥
1/ አንድ በዲኑ ደካማ የሆነን ሙስሊም ሰው"ኢማንየለውም
አንበል")
ኢማን ከሌለው ካፊር ነውና! ካስፈለገም ("ኢማኑ ደካማ ነው") እንበል
2/ ዱኒያዊ ችግርና ከባድ ነገሮች ሲገጥሙን "ቂያማ ነው፣ ቂያማ ቆመ ወ.ዘ.ተ" አንበል
3/ ከሰላምታ በኋላ
ስለ ጤናና ቤተሰብ ስንጠይቅ
"ኢማን እንዴት ነው?" አንበል
ተጠያቂ "ጥሩ ነው " ካለ እራስን የማጥራራት ችግር ላይ እንጥለዋለን!
4/ መጠሪያ ስማቸው
ያልሆነ ወንዶችን "ቢላል" ሴቶችን ደግሞ "ሱመያ" አንበል!
የቱንም ያህል መልካም ስራ ቢሰራ ሰሓባ ያልሆነ ሰው የሰሓባን ደረጃ ሊደርስ አይችልም
5/ አንድን ነገር ስንወስን ወይም ስንስማማ "አላህና አንተ/እገሌ ካለ" አንበል
6/ለአንድ ሰው ዱዓ
ስናደርግ መጨረሻ ላይ "ኢን ሻ`አላህ" አንበል
7/የእርግማን ቃላቶችን ያለ ቦታቸው ከመጠቀም እንጠንቀቅ! በተለይም ከቤተሰብና ከህጻናት ጋር!
ብዙ ሰዎች ለምዶባቸው በየቀኑ የእርግማን ቃላቶችን በተለያየ መልኩ ይሰነዝራሉ ( ዓይን ይብላህ፣ገደል ግባ ፣ አፈር ብላ ወዘተ ዘግናኝና ፀያፍ የሆኑትም ሳይቀሩ ይሰማሉ
[ሙእሚንን መርገም ልክ እርሱን እንደመግደል ያክል ነው!]
8/ "እናትህ --" ይህ ሙስሊም ዘንድ አይደለም መናገሩ መጻፍና ማድመጡም እጅግ በጣም በጣም ይዘገንናል! ከመሆኑም ጋር ግን አልፎ አልፎ ሙስሊም የሚባሉም ጭምር ሲሉት ይሰማል! ይህ በራሱ ከባድና ውድቅ ቃል ከመሆኑም በተጨማሪ በዚህ መልኩ የሰውን እናት መስደብ የራስን እናት እንደመስደብ ነው! (ይህንንም ያሉት ነቢያችን ናቸው) ምክንያቱም የሰውን እናት የሰደበ የራሱን እናት ማሰደቡ አይቀርምና ነው!
9/ "እናቴ ትሙት አባቴ ይሙት" አይባልም
ምክንያቱም ይህ መኃላ ነው መማል የሚቻለው ደግሞ በአላህ፣በስሞቹና በመልካም ባህሪያቶቹ ብቻ ነው! ሐዲስ ላይም (ከአላህ ውጪ ባለ አካል የማለ ከፍሯል ወይም አሻርኳል ) ተብሏል
✍ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
