ተማሪ መምህሩን ሲያሞግስ
ሸይኽ ረቢዕ ቢንሀዲ አልመድኸሊ(አላህ ያቆያቸውና) ተጠየቁ፡ "ሸይኽ አልባኒ(ረሂመሁላህ) በዚህ ዘመን የሐዲስ ሰዎች ቁንጮ ነውን?" ሸይኹ እንዲህ ሲሉ መለሱ ... "ወላሂ ይህንን እኮ እነሸይኽ ኢብን ባዝ፣ ኢብን ዑሰይሚን እንዲሁም በዘመኑ የነበሩ ዑለማዎች ተጠይቀዋል፤ እርሱኮ በሐዲስ አይደረስበትም በፍፁም አይደረስበትም! እንደውም በዘመኑ አንድም ሸይኽ አልባኒ በደረሰበት ላይ የሚደርስ የለም! እንዳውም እንደኔ እይታ ኪታቦችን በማዳረስ (በንባብ) ማንም አያገኘውም ኢብኑ ተይሚያም ኢብኑሐጀርም ቢሆን፤ ኪታቦችን በመሐፈዝ ከርሱ በበዛ መልኩ ይሐፍዙ (ይሸመድዱ) ነበር፤ ነገር ግን በንባብ በማዳረስ በጥናት በመሰብሰብ በጥናቱ ላይ ብርቱ ጥረት በማድረግ ይህ ሰው አምሳያ ይለውም! ሀገራትና ተቋማቷ ያን ያክል ማበርከት የማይችሉትን ቤተ-መፅሀፍ ለኢስላም አበርክቷል! አሁን ማንኛውም በሐዲስ ዙሪያ የሚፅፍ ግለሰብ በዚህ ሰው ላይ ጥገኛ ሁኗል! ይህ ሰው ግን ተበድሏል፤ ዓረብ ደረጃውን አላወቀለትም። አላህ ከአውሮፓ መሀል አንስቶ በምስራቅ ምርጥ በሆነው ዟሂሪያ ቤተ-መፅሀፍት ላይ ሲያደርገውና ስልሳ አመት በዛ ውስጥ ሲቀመጥ እንዲሁም ይህን ትልቅ ጥረት ሲያበረክት ከኛ ምን አገኘ? የሚያሳዝነው ሰዎች ካላጡት በስተቀር ችሮታ አይታወቅም፤ ዑለማዎች ግን ደረጃውን አውቀው ተቀብለውታል፣ እንደ ኢብን ባዝ ኢብን ዑሰይሚን ሌሎችም የኢስላም ሊቃውንቶች፣ የህንድ እና የፓኪስታን ዓሊሞች፣ የምዕራብ ዓረብ ዓሊሞችና ሌሎችም እንዲሁ የዚህን ሰው ደረጃ እና ለዑማው በዓቂዳ በመንሐጅ የነቢዩን(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሱና በማገልገል በኩል እንዲሁም በሌሎችም ያበረከተውን እና ደረጃውን አውቀዋል። አላህ ይዘንለት ለአላህ ዲን እና ለነቢዩ (ሰለላሁ ኣለይሂ ወሰለም) ሱና ላበረከተው አላህ ዓለምን ከሚመነዳበት ለዲኑና እና ለነቢዩ (ሰለላሁ ኣለይሂ ወሰለም) ሱና ላገለገሉ ሁሉ ከሚመነዳው በላቀ ይመንዳው" ﻣﺠﻠﺲ ﻳﻮﻡ 26/01/1426 ﻫ በግርድፉ የተተረጎመ
Abu Ibrahim Mohammed Ibnu Ibrahim