ሰዎች ግን ምን ነክቷቸዋል??
ያለንበት ሁኔታ እጅግ በጣም ያሳዝናል ነገረ ዓለሙ ተገለባብጧል።ጉዳዬቻችን መቋጠሪያ አጥተው ተበታትነዋል። ሁሉም ለራሱ ጥብቅና ቆሞ ለአላህ ለዲን ብሎ መወገን የውኃ ሽታ ሆኖ ጠፍቷል።
ብዙዎቻችን አላህን ረስተናል ፣ አኼራ ጀነት ጀሀነም ፣ አላህ ዘንድ መቆም ፣ ሚዛን ፣ ሲራጥ ፣ የስራ መዝገብ መቀበል … ሁሉ የሌለና የቀረ አስመስለነዋል!
የምንዋኝበት የወንጀል ባሕር ፣ የጥፋት አዘቅጥ አልበቃ ብሎን በዲን ስም የምንሰራው ሸፍጥና ንግድ ነገሩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል።
በተለያየ ጠርዞች ላይ እየገሰገስን እንገኛለን…
አንዳንዶች መናገሪያ መድረክ አገኘን ብለው ሰዎች ላይ የምላስ በትር ማሳረፍን የእለት ተእለት ስራ አድርገው ይዘውታል። ትልቁ ትንሹ ፣ ዓሊሙ ጣሊበል ዒልሙ ሳይቀራቸው ከፍ ዝቅ አድርገው ዘርጥጠዋል። ጀነት በልብስና በስም ብቻ የሚወረስ መስሏቸው ጮቤ ረግጠዋል።
ተጀሱስ ማጭበርበርና ውሸትን ወደ አላህ መቃረቢያ ታላቅ ዒባዳ አድርገው ይዘውታል። ከአላህና ከመልዕክተኛው ﷺ ቃል የበለጠ ለግለሰብ ንግግር ሁለመናቸውን ሰጥተው ለእርሱ ጋሻ ጃግሬ ጠበቆች ሆነዋል። ዒልም ትተው ስድብ ፣ ቁርኣን ትተው የሰው ስም ፣ ሐዲስ ትተው ነቆራን መሐፈዝን አዘውትረው ይዘውታል።
ከእነርሱ ውጪ የሐቅ ሰው እንደሌለ ወስነው በሌሎች ላይ የባጢል ባለቤትነት ማህተም መተዋል። ወንጀል የማያውቃቸው ጥብቆች እንደሆኑ አስበዋል የራሳቸውን ጥፋት "ሐባ" የሌሎች "ቁባ" አሳክለው መናገርና መለፈፍን ተክነውበታል።
እነርሱ ዘንድ ትልቁ ሽርክ ማህበር ማቋቋም ከባዱ ቢድዓ ሱሪ መልበስ ሆኗል። ሰዎች በኩፍር ፣ ሽርክና ቢድዓ ተዘፍቀው በስሜት ባሕር ጦዘው በዝሙት በተለከፉበትና እያለቁ ባሉበት ተጨባጭ እነርሱ ስለ ጀምዒያና ቢንጣል በማውራት ራሳቸውን መሽጉል አድርገዋል።
ከላይኛው ጫፍ በተቃራኒ አቅጣጫ ደግሞ እዚህ ጋር ሌላ በታችኛው ጠርዝ በኩል የሰፈሩ አሉ
"ወሰጢያ" ማለት በሐቅና ባጢል መካከል ያለ የሰፈራ ጣቢያ አድርገውታል። ሰዎች በሽርክና በቢድዓ ሲያልቁ ሞቅ ያለ ፈገግታ እያሳዩ ባላየ ማለፍ ፣ የራስ ድክመትን መሸፈኛ ምሽግ ፣ ስህተትንና ጥፋት መከለያ ጋሻ ፣ ሰዎችን ባልዋሉበት መሰየምና ደጋፊና ተከታይ ማብዣ ፕሮፖጋንዳ መስሏቸዋል።
"ተነጡዕነት" ማለት አላህ ግዴታ ያደረገባቸውን ለእርሱ ሲል የፈጠረበትን አላማ ተውሒድ ማስተማር ፣ እህቶችን ስለ ሒጃብ ወንድሞችን ፂማቸውን እንዲያሳድጉ ልብሳቸውን እንዲያሳጥሩ መስበክ ፣ ከሽርክና ቢድዓ እንዲርቁ ሰዎችን ማስጠንቀቅ ከመጥፎ ሱሶች እንዲርቁ መገሰፅ መስሏቸዋል።
ሰዎችን ማስበርገግ ማለት ሽርክን ሰርቶ ሳይቶብት የሞተ አላህ ፈፅሞ የማይምረው መሆኑንና የነብይዩን ﷺ ሸፈዓ እንደማያገኝ ማሳወቅ፣ ቢድዓን የሰራ ስራው ተቀባይነት እንደሌለውና ወደ ራሱ ተመላሽ እንደሚሆን የነብይዩን ﷺ ሐውድ እንደማይጠጣ ማስገንዘብ መስሏቸዋል።
ዳዕዋን በሒክማ (ጥበብ) ማድረግ ሰዎች የሚፈልጉትን እንጂ መማር ያለባቸውን አለማስተማር ፣ ስለ ወላጅና ጎረቤት ሐቅ ተናግሮ የፍጥረታት ሁሉ ጌታ ስለሆነው አላህ እና ስለ መልዕክተኛው ﷺ ሐቅ አለመናገር ፤ ስለ አኽላቅ ተናግሮ ስለ ተውሒድ ዝም ማለት ፣ ስለ አመጋገብና አጠጣጥ ሱና አስተምሮ ስለ ፂምና ልብስ ስለ ሒጃብ/ ኒቃብ እና አኽቲላጥ ፀጥ ረጭ ማለት ፣ ስለ ሀሜትና ዝሙት ከባድነት ተናግሮ ሽርክና ቢድዓን እንደ ጥፍር ቆሻሻ አሳንሶ መቁጠር መስሏቸዋል።
"አመለካከተ ሰፊነት" ማለት ሰዎች የሚያስደስታቸውን እንጂ የሚያስፈልጋቸውን ፣ የሚገስፃቸውንና የሚስጠነቅቃቸውን ያለባቸውን ችግር የሚገመግሙበት ትምህርት አለመስጠት መስሏቸዋል። በዚህም ገሩን ዲን አክብደው ከባዱን ወንጀል አቅለዋል።
የቀረው ወገን ደግሞ…
እኔ ከየቱም አይደለውም ጥጋቹን ያዙ የሚለው ደግሞ የተሳሳቹ ስህተት ሳይሆን የአራሚው መልስ ተራራ መስሎ ይታየዋል። አንዱ ስለሌሎች የፈለገውን ሲናገር ፣ ያሻውን ሲለጥፍባቸው እንደ ፅድቅ አይቶ ሌላኛው ሲናገር ደግሞ የሰዎችን ስህተት እንደሚለቃቅም የሀሜት ሱስ እንደተጠናወተው አድርጎ ያስባል። ምንኛ የከፋ ፍርድ ነው???? በአደባባይ ለተሰራጨ ስህተት በጓዳ ምክር ይሰጥ ብሎ ይምግታል ፣ ፍርደ ገምድል የሆነ ሀሳብ ይሰነዝራል።
አላሁል ሙስተዓን! ሰዎች ግን ምን ነክቷቸዋል??
እራሴን ከስህተት የፀዳሁ ነኝ አላልኩም አልልም! በየትኛውም አቅጣጫ ያለ ጠርዘኛ አመለካከትና አካሄድን ግን አልደግፍም!
"ﻭَﻣَﺎ ﺃُﺑَﺮِّﺉُ ﻧَﻔْﺴِﻲ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻨَّﻔْﺲَ ﻷَﻣَّﺎﺭَﺓٌ ﺑِﺎﻟﺴُّﻮﺀِ ﺇِﻻ ﻣَﺎ ﺭَﺣِﻢَ ﺭَﺑِّﻲ ﺇِﻥَّ ﺭَﺑِّﻲ ﻏَﻔُﻮﺭٌ ﺭَﺣِﻴﻢٌ"
«ነፍሴንም (ከስህተት) አላጠራም ፤ ነፍስ ሁሉ ጌታዬ የጠበቃት ካልሆነች በስተቀር ፤ በመጥፎ ነገር በእርግጥ አዛዥ ናትና ጌታዬ በጣም መሓሪ አዛኝ ነው» (ዩሱፍ: 53)
በመጨረሻም ውድ ወንድሜ/እህቴ! እስኪ መለስ እንበልና ራሳችንን እንገምግመው።
የቱ ጋር ነን?!
[ሐይደር ኸድር
እሁድ ጥር 14 2009]