ሰማእቱን ስንዘክረው
[ክፍል አንድ]
በአላህ ስም. . በመልእክተኛው ላይ ሶላትና ሰላም ይውረድ. .
.. … .. ምንም እንኳን ድባቡ አስግቷቸው የዚህ ሰማእት ጓዶች የቤቱን መግቢያ ከማንም ሰርጎ ገብ ለመጠበቅ እበሩ ላይ ለጥበቃ ቢቆሙም ደም የተጠሙት አማጽያኑ ግን ከቤቱ ጀርባ በድብቅ አጥሩን አንድ በአንድ ዘልለው በመግባት ወደ ውስጥ ዘለቁ. . . ያ ታላቅ ሰው በዚህ አጋጣሚ መለኮታዊው መጽሐፍ የሆነውን ቁርኣን በሚያምረውና በሚያስረቀርቀው ድምጹ በማንበብ ላይ ነበር . . የቤቱን አጥር ዘለው ከገቡት አማጽያን መካከል አንዱ ጥቁር ሰው ወደዚህ ሰማእት ተጠጋ. . ! ያለምንም እፍረት አጓጉል ጸያፍ ቃላትን ወርውሮ ጺሙንም ጨምድዶ ያዘው. . ወደ መሬትም አስተኛው. . በያዘው ረዥም የተሳለ ጩቤ የዚህን ሰማእት ሆድ በጭካኔ ለዘጠኝ ግዜ ያህል አከታትሎ ወጋው. . .!
ይህ ሰማእት መሰዋቱን ካረጋገጡም ወዲህ እነኝህ ደም የተቀቡት አውሬዎች ቤቱን ለቀው ወጡ . . ሸሹ !!
ሸይጧን በደስታ ሰከረ. . . ! አማኞች በሐዘን ተከዙ. .!
ይህን እጅግ አሳዛኝና እኛ ሙስሊሞችን ለዘመናት በቁጭት ከንፈራችንን እንድምመጥ የጋበዘንን የዚህን ሰማእት ደም የተቀባ እንባ አስጨራሽ ታሪክ ዛሬ አብረን እንዘክራለን!!
ቆይታችሁ ከእኔ ጋር ይሁን . . !
እስከዛሬ የብዙ ታዋቂ ሰዎችን የህይወት ታሪክ አንብበን ሊሆን ይችላል። እስከዛሬ የብዙ ጀግናዎችን ገድል አድምጠን ሊሆን ይችላል። በርካታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ስብዕናዎች አውስተን ተምሳሌትነታቸውን አወድሰን ሊሆንም ይችላል።
ዛሬ የምንዘክረው ግን በምድራዊው ዓለም ብቻ እውቅና ተችሮት በላእላዩ ዓለም ስለተዘነጋው ተራ ግለሰብ አይደለም።
ዛሬ የምንወሳው ግን በሰዎች ዘንድ ተከብሮ በፈጣሪ ዘንድ ቦታ ስለሌለው የንዲያው ነገር አይነት ግለሰብ አይደለም።
እርሱ. . . ተምሳሌታችን ነው ብለን የምንከተለው!
እርሱ. . . ብጹእ ነው ብለን የምናጥራራው!
እርሱ . . . ድንቅ ነው ብለን የምናወሳው!
እርሱ . . . ጀግና ነው ብለን የምንዘክረው!
እርሱ . . . ጻድቅ ነው ብለን የምናወድሰው! . . . ታላቅ ሰው ነው!
ይህ ሰማእት ማን ነው?
የተወለደው በወበቁ ቆላ ስፍራ፤ በገላጣው የዓረቢያ ምድር በጧኢፍ ከተማ ከአባቱ ዐፋን ቢን አቢ ዓስ ቢን ኡመያህ ሲሆን የዘር ሃረጉ ወርዶ ከዐብድ መናፍ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የቁረይሽ ግንድ ይዋሃዳል። እናቱ ኡርዋ ቢንት ከሪማህ ስትባል በእናቷ አልበይዷእ በኩል የዐብዱል ሙጦሊብ የልጅ ልጅ ሆና ከረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር በአጎቷ በኩል ትዛመዳለች። ይህ ሰማእት የተወለደው እንደ ጃሂሊያው ዘመን አቆጣጠር ከዝሆኑ ጦርነት ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ነው። ይህም ማለት እንደ ግሪጎራውያን አቆጣጠር በ576 ዓመተ ልደት ይሆናል።
ስሙ ዑሥማን ቢን ዐፋን ይባላል። አጭር አይሉት ረዥም መካከለኛ ቁመና የነበረው፥ የአይን ብሌኑ ጎላ ያለ፥ ባለቀጠን ያለ ሰውነትና ባለ ሰፊ ትከሻ፥ መልከመልካም ፊትና ባለ ባለ ረግረግ ጥቅጥቅ ያለ ረዥም ጢም. . በአጠቃላይ ውብ ቁመና እና መልክ ያለው ግለሰብ ነበር። ከኢስላም በፊት በጃሂሊያው ግዜ የታወቀ፥ የተከበረ፥ የተወደሰ፥ ባለግርማ ሞገስ፤ የናጠጠ ጥበበኛ ባለንዋይ ነጋዴ የነበረ ሲሆን ይህም ከመሆኑ ጋር ስሙ በመልካም ስነምግባር ባልተቤትነቱና በለጋስነቱ እንጂ አይወሳም። ከተውሒድ በፊት በህይወቱ አንድም ቀን ለጣዖት አጎብድዶ አያውቅም። ከኢስላም በፊትም ይሁን በኋላ አስካሪ መጠጥን ነክቶ፤ ዝሙትንም ቀርቦ አያውቅም።
ከልጅነቱ ጀምሮ የአባቱ የንግድ ባህል ሲማር ቆይቶ ከአባቱ ህልፈት ወዲህ የንግድ ስራውን ወርሶ ከበኒ ኡመያ ትላልቅ ቱጃር ነጋዴዎች አንዱ ለመሆን በቅቷል። ከፈጣሪ በተሰጠው መልካም ስነምግባር፥ በጎሳው ውስጥ ክብርን የተጎናጸፈ፥ ሲናገር የሚደመጥ፥ አይናፋር፥ በለጋስነቱ የሚታወቅ ታላቅ ሰው ነበር።
ዑሥማንና ኢስላም
ዑሥማን ቢን ዐፋን ቀድመው ኢስላምን ከተቀበሉ ታላላቅ ሶሓባዎች አንዱና ታላቁ ሲሆን የሰለመውም በታላቁ ኸሊፋ አቡ በክር አስሲዲቅ ጥሪ ነበር። እንዲህም ሲል አቡ በክር ዑሥማንን ወደ ተውሒድ ጠራው. .
« ዑሥማን ሆይ! ወዮልህ! ወላሂ! አንተ እኮ ቆራጥ ግለሰብ ነህ። ሐቁ ከሐሰት አይደበቅብህም። ያንተ ጎሳዎች የሚያመልኩት የሆነው ጣዖት የማይሰሙ፥ የማያዩ፥ የማይጠቅሙና የማይጎዱ የሆኑ ድንጋዮች አይደሉምን? . .»
ዑሥማንም፡ «እንዴታ ወላሂ! እንደዚያው ናቸው!» ሲል መለሰ . .
አቡ በክርም ፡ «እኚህ ሙሐመድ ናቸው! አላህ ለፍጡራን በጠቅላላ መልእክቱን እንዲያደርሱ የላካቸው የሆኑ. . ቀርበህ ታደምጣቸዋለህን?» ብለው ሲጠይቁት. .
ዑሥማንም ፦ «አዎን!» ብሎ መለሰ።
ወዲያውም ወደ አላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ካቀኑ ወዲህ እንደደረሱም . .
ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም ፦ « ዑሥማን ሆይ! አላህን ወደ ጀነት (ሊያስገባህ) እሺ በል። እኔ ወደ አንተ እና ወደ ፍጥረታቱ በሙሉ ተልኬያለሁና።» አሉት . .
ዑስማንም ይህንን ክስተት በራሱ አንደበት ሲተርክ ፦ «በአላህ እምላለሁ! ይህንን ስሰማ ከመስለም ራሴን አላቀብኩም። እናም አላህ ብቸኛና በሐቅ ተመላኪ ጌታ መሆኑን ብሎም ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛና ባሪያ መሆናቸውን መሰከርኩ።»
ዑሥማን ቢን ዐፋን በሰላሳ አራት ዓመቱ፤ በኢስላም ታሪክ ውስጥ ከአቡ በክር፥ ከዐሊይና ከዘይድ ቀጥሎ በአራተኛ ደረጃ የሰለመ ከመጀመሪያዎቹና ከቀዳሚዎቹ ሶሓቦች (አልሳቢቂነ አልአወሊን) ግንባር ቀደሙ ሆነ።
«ዙ ኑረይን»
ዑሥማን ረዲየላሁ ዐንሁ በትዳር ካሳለፋቸው እንስቶች መካከል ሁለቱ የታላቁ ነቢይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሴት ልጆች ይጠቀሳሉ። የመጀመሪያዋ ሩቀያህ ስትሆን ሁለተኛዋ ደግሞ ኡሙ ኩልሡም ናት። ከሩቀያህ ጋር በፍቅር ትዳርን ካሳለፉ ከጥቂት ዓመታት ወዲያ ሩቀያህ ወደ አኼራ ሄደች። የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጃቸውን ሩቀያን በዑሥማን ጉዳይ አደራ ይሏትም ነበር። አንድ ቀን ልጃቸው ሩቀያህ የታላቁን ኸሊፋ ጸጉር እያጠበች ሳለ ወደ ቤት ይገባሉ። እንዲህም አሏት. . «አንቺ ልጄ ሆይ! ለአቢ ዐብዲ’ላህ (ዑሥማን) መልካምን ዋይ! እርሱ እኮ ከአስሓቦቼ ከሁሉም በላይ በስነምግባር የሚመሳሰለኝ ነው። » አሏት።
ሩቀያህ ወደ አኼራ ከሄደች ከዓመታት በኋላ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጃቸውን ኡሙ ኩልሡምን በትዳር አጣመሩት። እንዲህም ሲሉ የዑሥማንን እና የኡሙ ኩልሡምን ትዳር መለኮታዊ ትእዛዝ እንዳለበት አበሰሩ . . « እኔ ኡሙ ኩልሡምን ለዑሥማን አልዳርኩትም ከሰማይ በመጣ ራእይ (ወሕይ ትእዛዝ) ቢሆን እንጂ!. .» ።
ከዓመታት ወዲያ የአላህ ውሳኔ ሆነና ኡሙ ኩልሡምም ከጌታዋ ዘንድ ሄደች። ያኔ ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከወዳጃቸው ዑሥማን ጋር በልጃቸው ሞት እዝነት ላይ ሆነው ብሎም አማችነታቸው መቋረጡ ቆጭቷቸው እንዲህ አሉት. . «ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ሦስተኛ ሴት ልጅ ብትኖረኝ ኖሮ በዳርኩልህ ነበር። አንተ ዑሥማን ሆይ!»።
የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሁለት ሴት ልጆች ባልተቤት በመሆኑ ምክንያት «ዙ ኑረይን» (የሁለቱ ብርሃኖች ባልተቤት) ተብሎ ስያሜ ሊሰጠውም ችሏል።
ዑሥማን እና ሐበሻ
ዛሬ ላይ ኢስላምን ከዐረቢያ ምድር አንስተው በአላህ ፍቃድ ወደኛይቷ የሐበሻ ምድር እንዲሰራጭ ካደረጉት ታላላቅ ታሪክ የሚያወሳቸው ባልመልካም ውለታ አስሓቦች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን ረዲየላሁ ዐንሁ መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናውቅ ይሁን?
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመካ ቆይታቸው ከአጋሪያን የሚደርስባቸው መከራና በደል እየጠነከረ በመጣ ግዜ ከፊል አስሓቦች በነቢዩ ትእዛዝ አማኻኝነት ይህንን ገፈት በመሸሽ ወደ ሐበሻ ምድር ተሰደዱ። ከተሰደዱት የመልእክተኛው ባልደረቦች መካከል ታላቁ ኸሊፋ ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን እና የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ልጅ የሆነችው ሩቀያህ ይገኙበታል። በመካ ሁኔታዎች ረገብ ባሉም ግዜ ወደ ሃገራቸው ተመልሰዋል።
ዑሥማንና ዘመቻ
የሶሓባዎች ጀብድ ሲነሳ፤ ጀግንነታቸው ሲወሳ የዑሥማን ቆራጥነት፥ ታጋይነት አብሮ መነሳቱ የማይቀር ነው። ዑሥማን በበርካታ ዘመቻዎች ከአማቹ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር የተሳተፈ ሲሆን የበድር ዘመቻ ነጋሪት ተደልቆ ክተት በታወጀበት እለት እንኳን የሚወዳትና የምትወደው ሚስቱ ሩቀያህ በጠና ሕመም ላይ ሆና ሳለ ዑሥማን ለጂሃድ ታጥቆ ተነስቶ ነበር። ሆኖም ይህ ጀግና ሚስቱን በፍራሿ ላይ እንዲያስታምማት ትእዛዝ ተሰጠው። የበድር ዘመቻ ላይ የአላህ መልእክተኛ ከአስሓቦቻቸው ጋር ድልን ሲቀዳጁ ልጃቸውና የታላቁ ሶሓባ ዑሥማን ባለቤት ሩቀያህ ግን ወደማይቀርበት ሃገር ሄዳ ነበር። ምንም እንኳን ዑሥማን በዚህ ዘመቻ ባይካፈልም ከአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የበድር ዘመቻ ተሳታፊዎችን ደረጃ እንደሚያገኝ እንዲህ ሲሉ አብስረውታል. .
«ለአንተ የበድር ሰማእት ያለውን ድርሻ እና ምንዳ አለህ!»
ዑሥማንን የነካ አይማርም!
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እምነት ከሚጥሉበት መልእክተኞች አንዱ ታላቁ ኸሊፋ ዑሥማን ቢን ዐፋን አንዱ ነበር። በስድስተኛው ዓመተ ሂጅራ የአላህ መልእክተኛ እና ባልደረባዎቻቸው በዑምራ ወደ መካህ ባቀኑበት ግዜ አጋሪያን መልእክተኛው ከባልደረባዎቻቸው ጋር ለዘመቻ የመጡ ናቸው ብለው በእኩይ እሳቤ ለጥል ይጋበዛሉ በሚል ስጋትና ለዑምራው ብሎም ለተከበረው ስፍራ ክብር ሲሉ ዑሥማንን ወደ አጋሪያን መልእክት እንዲያደርስ፤ ለጥል ሳይሆን ለአምልኮ የመጡ እንደሆኑ እንዲያስረዳቸው ላኩት።
እንዲህም ሲሉ . .
«ወደ ቁረይሾች ሂድና ንገራቸው! እኛ ማንንም ለመጋደል ሳይሆን ይህንን ቤት ለመጎብኘት፤ ልቅናውን ለማክበር ነው የመጣነው። እንደምታዩት ግመሎች በእጃችን ይገኛሉ። (ግመሉንም) እናርዳለን ምጽዋትም እንሰጣለን።»
ዑሥማንም መልእክቱን ለማድረስ ወደ መካ አጋሪያን ዘንድ አቀና። ይህንን መልእክት ለማድረስ በወጣበት መዘግየቱን ያስተዋሉ መናፍቃን ዑሥማን መገደሉን መርዶ ማናፈስ ያዙ። ያኔ ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እጅግ የሚወዱት ታላቅ ሰው መሞቱን መርዶ በሰሙ ግዜ ታላቅ ሐዘን ገብቷቸው ባልደረባዎቻቸውን በጠቅላላ ሰብስበው “ዑሥማን ተገድሎ ቤታችን አንገባም!” በማለት ጦርነት ሊያውጁ እንደሆነና ሁሉም ባልደረባዎቻቸው ቃል ኪዳናቸውን እንዲያድሱ አዘዙ። ከሙናፊዎች በቀር ሁሉም እጃቸውን በረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ በመደረብ ቃል ኪዳን በማደስ የዑሥማንን ደም ለመበቀል ሞት ሲቀር ፊት ለፊታቸው ምንም እንደማያስቆማቸው ቃል ገቡ። ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም ቀኝ እጃቸውን ከሁሉም ላይ በመጫን “ይሄ የዑሥማን እጅ ነው!” በማለት የቃል ኪዳኑ እድሳት መታወጁን አበሰሩ። ይህኔ ነበር ጌታችን አላሁ ሱብሓነሁ ወተዓላ ይህንን ታላቅ ቃል ኪዳን እያወደሰ እንዲህ ሲል አምሳያ የሌለው ቃሉን ያወረደው. .
لَّقَدْ رَضِيَ اللَّـهُ عَنِ الْمُؤْمِنِينَ إِذْ يُبَايِعُونَكَ تَحْتَ الشَّجَرَةِ فَعَلِمَ مَا فِي قُلُوبِهِمْ فَأَنزَلَ السَّكِينَةَ عَلَيْهِمْ وَأَثَابَهُمْ فَتْحًا قَرِيبًا
{{ በእርግጥም ምእመናን አንተን በዛፉ ስር ሆነው ቃል ኪዳን በገቡልህ ግዜ ወደደ። በልቦቻቸው ያለውን (እውነተኝነት) አውቆ እርጋታንም አወረደባቸው። ቅርብ የሆነ ድልንም መነዳቸው። }}
የዑሥማን ቢን ዐፋን መጨረሻ ምን ይሆን?
ቀጣዩን ትምህርት ይጠብቁ. . ኢን ሻ አላህ
___
ምንጭ፡
- አልቁርኣን አልከሪም
- ታሪኽ አጥጦበሪ [ኢማም አጥጦበሪ]
- አልዐዋሲም ሚነልቀዋሲም [ኢማም ኢብን አልዐረቢ]
- አልቢዳያ ወንኒሃያህ [ኢማም ኢብን ከሢር]
- "ዙ ኑረይን" ዑሥማን ቢን ዐፋን [ሸይኽ ሙሐመድ ረሺድ ሪዷ]
- ሶሒሕ አልቡኻሪ [አልኢማም አልቡኻሪ]
- አንሳቡል አሽራፊ [አሽሸይኽ አሕመድ ቢን የሕያ]
- አልካሚል ፊል ታሪኽ [ኢማም ኢብኑል አሢር]
እና ሌሎችም ... ..