ልጅ እያለ በነዚህ ስንኞች ያዜመ አለ?
"መካና መዲና አንድ ነው መሬቱ
መዲና ይበልጣል ነቢ ያሉበቱ"
"መካና መዲና አንድ ነው መሬቱ
መዲና ይበልጣል ነቢ ያሉበቱ"
ይሄ ስህተት ነው። መዲና ከመካ አትበልጥም። የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀብርም ከከዕባ አይበልጥም። በጥቂት
ዑለማዎች ከተንፀባረቀው ውጭ የብዙሃኑ ዑለማዎች አቋምም መካ ከመዲና እንደምትበልጥ ነው። የሶላት ምንዳን
በተመለከተም በመካ ሐረም የተሰገደ ሶላት በሌላ ቦታ ከተሰገደ ሶላት በመቶ ሺህ ሲበልጥ በመዲና የሚሰገደው ግን
በአንድ ሺህ ነው የሚበልጠው። ሌሎችም ብዙ ነጥቦችን መዘርዘር ይቻላል።
