ክብር ለዐሊሞች
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እነሆነ ዑለሞች የዚህ ዲን ( እምነት ) ባለውለታዎች ናቸው ብንል ደረጃቸውን ማጋነን አይሆንም ፡፡
ዑለሞች ህብረተሰቡ ካለበት የጥፋት ምህዳር ተላቆ በቀጥተኛው የኢስላም ጎዳና ላይ በመራመድ ለዱንያዊም ሆነ አኺራዊ ስኬት ይበቃ ዘንድ ከፍተኛ ጥረትን ያደርጋሉ ፡፡ በዚህም ጥረታቸው የብዙዎች ስህተት ይታረማል የብዙዎችም አላዋቂነት ( ጅህልና ) ይገፈፋል ከላይ እንደጠቀስነውም በሁለቱም አገሮች ስኬታማነትን እንዲቀዳጅ ይሆናል ፡፡
እና ታድያ.........ባለ ውለታ አይደሉምን ....? ( ናቸው እንጂ ! )
ይህንንም ባለውለታነታቸውን ኢስላም አልዘነጋም ፡፡ ስለነሱ ክብርና ደረጃም አብዝቶ አውግቷል በክብራቸው ላይ መረማመድ የሚሹ አካላትንም እጅግ በከበደ መልኩ አስጠንቅቋል ፡፡ ( እንዴትስ አያስጠነቅቅ ........ ባለውለታዎቹ እኮ ናቸው )
.
ታድያ ኢስላም ይህንን ደረጃ ያጎናፀፋቸው በአዕምሯቸው ስለሸመደዱት እውቀት ፣ በአይናቸው ስላነበነቡት ኪታብ ፣ በጣቶቻቸውለ ስለከተቧቸው መፅሀፍቶች ( ኪታቦች ) እና ብዙ ተከታይ ስላላቸው ብሎ ሳይሆን << ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮ በትክክለኛው መንገድ ስለሚያስፋፉ >> ነው ፡፡
አልያማ የአዋቂ አጥፊ ከሆኑ ምኑን አበጃችሁ ተብለው ይሾማሉ ?
ስለምኑስ ተብሎ ይወደሳሉ ?
በእውቀታቸው ብቻ የሚወደሱና የሚቀደሱ በነበረማ አይሁዶችን አላህ በቁርዐኑ ባላወገዘና ባልተቻቸው ነበር ፡፡
አላህም አይሁዶችን እንዲህ ሲል በቁርዐኑ ተችቷል
.
{ يسمعون كلام الله ثم يحرفونه من بعد ما عقلوه و هم يعلمون } ¤ البقرة آيه 75 ¤
.
《 ( አይሁዶች ) ከተረዱት በኀላ እነርሱ እያወቁ የሚለውጡት ሲሆኑ ( ለናንተ ማመናቸውን ትከጅላላችሁን ) 》
¤ ሱረቱል በቀራ 75 ¤
.
እናም ዑለሞች ( አዋቂዎች ) የሚከበሩትና የሚወደሱት በሸመደዱት እውቀት ሳይሆን በሚያስተምሩትና በሚያስተላልፉት #ትክክለኛ እውቀትና መረጃ እንዲሁም ብይን ( ፈታዋ ) ነው ፡፡
.
ይህን ሳይፈፅሙ ከቀሩና አላህ የጣለባቸውን የእውቀት አማናን ካጓደሉ ብሎም ሰዎችን በተሳሳተ አመለካከት የሚያጠምቁ ከሆነ ለነዚህ አካላት ሊሰጠው የሚገባውን ብይን በተመለከተ ቀደምት የኢስላም ሊቃውንቶች ያሰፈሩትን እናውሳ
- ማሊክ ከሸይኺ ረቢዕ እንዳወሳው
" የተጣመመ ፈትዋን ( ብይንን ) የሚያሰራጭ አካል ( ሸይኽ ) ከሌቦች በበለጠ ሊታሰር ይገባዋል "
- ከቀደምት ፉቀሀዎች መሀል አንዱ " ዝሙት ከሚሰራ ሰው ዘወትር የሚያጨስ አካል ይብሳል " የሚል ሰው አለ ይህ እንዴት ይታያል ....? ተብለው ተጠየቁ .......... እርሳቸውም " ይህንን ፈትዋ የሚሰጥ አካል ( ሸይኽ ) በመምታት አልያም በማሰር መቅጣትና ማረም ተገቢ ነው ፡፡ ምክንያቱም ይህ ሰው ( ሸይኽ ) የአላህን ሸሪዐ እየቀየረና እየበረዘ ነው ፡፡ እንደሚታወቀው ዚና ቁርጥ ያለ ሀራም ስለመሆኑ በሁሉም ዘንድ ስምምነት ያለው ተግባር ነው ፥ ማጨስ ግን ልዩነት አለበት " .......... በማለት መለሱ !
.
ዑለሞች ( አዋቂዎች ) የተጣለባቸውን ሀላፊነት በአግባቡና በትክክለኛው መንገድ ከመወጣት ይልቅ ለስሜታቸውና ለጥቅማቸው አድረው የጠራና ትክክለኛ የሆነውን የአላህን ዲን ከበረዙና በጥፋት ላይ ተሰማርተው ህብረተሰቡን ወደ ስህተት ጎዳና የሚመሩና የሚጣሩ ከሆነ ከስህተታቸው እንዲታረሙና ህብረተሰቡም ከውድቀትና ጥፋት እንዲጠበቅ በነዚህ #አውቆ_አጥፊዎች ( ዑለሞች ) ላይ መልስ ሊሰጥ ተገቢ ከመሆን አልፎ ግዴታም ይሆናል ፡፡ ይህ ደግሞ በፍፁም #ሀሜት አይባልም ፡፡ ምክንያቱም ዲነል ኢስላም ለሰዎች ጥብቅና ከመቆም ይልቅ ለሀቅና ለትክክለኛ ጎዳና ጥብቅና እንቆም ዘንዳና ግለሰቦችንም ( ዐሊምም ይሁን ተራ ግለሰብን ) ከስህታቸው እናርማቸው ዘንድ አበክሮ አስተምሮናል ፡፡
ይህንንም በተመለከተ የቀደሙ ታላላቅ የኢስላም ምሁራኖች ተከታዩን ብለዋል ፡፡
.
1 ] ኢብኑ ረጀብ አልሀንበሊ
<< ጀርህና ተዕዲል የተፈቀደ ነው ፡፡ በዚህም ላይ ተቀባይነት ያለውንና ተቀባይነት የሌለውን ለማጣራት ስለሚረዳ በቀደምት ህዝቦችና አዒማዎች ዘንድ ስምምነት አለ ፡፡ በእርግጥ እውቀት የሌለው አካል ይህ ተግባር ሀሜት መሆኑን ይጠረጥራል ፡፡ ነገር ግን የሰዎችን ነውር ( ስህተት ) መናገር ( ግልፅ ማድረግ ) ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ችግር የለውም ፡፡ >>
.
2 ] ኢማሙ አህመድ
አንድ ሰው እርሳቸው ዘንድ በመምጣት " ከሚፆም ከሚሰግድ እንዲሁም ኢዕቲካፍ ከሚያደርግ ሰውና በቢድዐ ( የስህተት ጎዳና አራማጅ ) የሆኑ አካላት ላይ መልስ ከሚሰጥ ሰው እርሶ ዘንድ የተሻለውና በላጩ ማን ነው ? " ሲል ጠየቃቸው
እርሳቸውም " ሰውየው ከሰገደ ፣ ከፆመ እና ኢዕቲካፍ ካደረገ ይህ በራሱ ላይ የሚገደብና ለራሱ ብቻ ጥቅም የሚያስገኝ ተግባር ነው ፡፡ ነገር ግን በቢድዐ ( የስህተት ጎዳና አራማጆች ) ላይ መልስ ከሰጠ ይህ ለአጠቃላይ ሙስሊሞች ነውና ይህ ይበልጣል ፡፡ " ብለው መለሱለት !
.
3 ] አቡ ዐሊ አል ደቃቅ
" በሀቅ ላይ ዝም የሚል ዲዳ ሸይጧን ነው ፡፡ " ብለዋል
.
4 ] ኢማም ሀሰን አል - በስሪ
" ስለ አንድ እርኩስ ሰው ማውጋትን ትሻላችሁ ? .......... በሉ ሰዎች ከርሱ ( አደገኝነት ) ይጠነቀቁ ዘንዳ ተናገሩ " ብለዋል !
.
5 ] ከላይ በተራ ቁጥር አራት ላይ የጠቀስነውን የኢማም ሀሰን አል-በስሪን ንግግር ታላቁ ዐሊም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንደሚከተለው አብራርተውታል ፡፡
" ይህ ማለት ወንጀሉን ( ስህተቱን ) የደበቀና ግልፅ ያላደረገ አካል እስኪቶብት ድረስ በሚስጥር ( በግል ) ይመከራል ፡፡
ወንጀሉን ( ስህተቱን ) ግልፅ ያደረገና በአደባባይ ያወጀ አካል ግን ከላይኛል ( ከደበቀው ) በተቃራኒ በአደባባይ ይወገዛል ፥ በአደባባይም መልስ ይሰጥበታል ! "
------
በዚህም መሰረት ሰዎችን በግልፅና በአደባባይ ወደ ስህተት የሚጣሩ አካላት ላይ በተመሳሳይ#በግልፅና_በአደባባይ_መልስ_መስጠት ከስህተታቸውም ማረም ተገቢ ይሆናል ፡፡
ምክንያቱም ህብረተሰቡን ከጥፋትና ውድቀት ለመታደግ ይህንን መተግበር የግድ ስለሆነ ማለት ነው ፡፡
እስካሁን በዚህ ዙሪያ የቀደሙ የኢስላም ሊቆችን አቋም ስንገልፅ ዘልቀናል እንደ ማሳረጊያ ግን አንድ የነቢያችን ﷺ ሀዲስን በማስቀመጥ ነገሩን በደንብ ግልፅ እናድርገው ፡፡
.
ፋጢማ ቢንት ቀይስ ለነብያችን ﷺ " በርግጥ አቡ ጀህምና ሙዐዊያ ለትዳር ጠይቀውኝ ነበር ፡፡ ( ማንን ልምረጥ ? ) አለቻቸው "
እርሳቸውም የሁለቱንም ትዳር ጠያቂዎች ስም በማንሳት ስለ ሰዎቹ ትክክለኛ ማንነትና ስላለባቸው ችግር እንዲህ በማለት አወጓት
<< አቡ ጀህም ሴቶችን የሚመታ ነው ፥ ሙዐዊያ ደግሞ ቤሳቢስት የሌለው ድሀ ነው ........... ቤይሆን ኡሳማ አግቢ " አሏት ፡፡
.
እንግዲህ ተመልከቱ ነብያችን ሙሀመድ ﷺ የአንዲትን እንስት ትዳር ለማቃናት ሲሉ የሰዎችን ስምና ስህተታቸውን በሌሉበት አንስተዋል ፡፡
ታድያ ልክ እንደ አንዳንድ ወንድምና እህቶች አባባል ከሆነ ..... ነብያችን ﷺ #አምተዋል ማለት ነው ?#የሰው_ስጋስ በልተዋል ማለት ነው ........... ?
( እንዲህ ካለው ንግግር በአላህ እንጠበቃለን )
ነገር ግን ይህ የሚያሳየን የሰዎች ስምና ስህተት መወሳቱ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ ማንሳት እንደሚቻል ነው ፡፡
መቼም የአንዲትን እንስት ትዳር ለማቃናት የሰዎች ስም ከተነሳ የአላህ ዲንና የብዙ ሚልዮኖችና ቢልዮኖች እምነት የሆነውን #እስልምናን ለመጠበቅ ሲሆን ደግሞ ማንሳት ከመፈቀድም አልፎ ግዴታ ለመሆንም የሚቃረብ እንደሆነ አውቆ ለተኛ እንጂ ለማንም የማይሰወር ግልፅ እውነታ ነው ፡፡
.
በዚህም መሰረት አላህ ከፈቀደ በቀጣይ ለተወሰኑ ተከታታይ ክፍሎች ከቀደሙትም ይሁን አሁን በህይወት ካሉት መሻይኾች መካከል ባለንበት ተጨባጭ ህብረተሰቡ መሀል የተሳሳተ አቋምን የበተኑና እየበተኑ ያሉ አካላትን ነቅሰን በማውጣት ህብረተሰቡን እነርሱ ካንሰራፉት ስህተት ለመታደግ የበኩላችንን አስተዋፅዖ እናደርጋለን ! ( ኢን ሻ አላህ )
-
እባኮትን !
" ለሰው ጥብቅና ከመቆሞት በስተፊት
በቅድሚያ ፅሁፉን በጥሞና ያንብቡ
በመቀጠል ደግሞ በቅንነት ለመረዳት ይሞክሩ
በመጨረሻ ለግለሰቦች ሳይሆን ለሀቅ ይወግኑ "
__________________________ _______
f / Edris ibn Elias ( አቡ ማሂ)

__________________________
f / Edris ibn Elias ( አቡ ማሂ)