ونحب أصحاب رسول الله صلى الله عليه وعلى آله وسلم ، ولا نفرط في حب أحد منهم ، ولا نتبرأ من أحد منهم ، ونبغض من يبغضهم ، وبغير الخير يذكرهم ، ولا نذكرهم إلا بخير ، وحبهم دين وإيمان وإحسان ، وبغضهم كفر ونفاق وطغيان
«የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አስሓቦችን እንወዳለን። አንዳቸውንም ከመውደድ አንወገድም። ከአንዳቸውም ቢሆን ራሳችንን አናጥራራም። የሚጠላቸውን እንጠላለን። በመልካም እንጅ አናወሳቸውም። እነሱን መውደድ የዲን፥ የኢማን፥ የመልካምነት መገለጫ ነው። እነርሱን መጥላት ደግሞ ኩፍር፥ ኑፋቄ፥ አመጸኝነት ነው።»
[አልቂደቱ አጥጠሃዊያህ]
ሺዓዎች በጣት የሚቆጠሩ አስሓቦችን ሲቀር ሌሎቹን ይጠላሉ፥ ያከፍራሉ፥ ራሳቸውንም ከነርሱ ያጥራራሉ። በመሆኑም እኛ ሺዓዎችን እና ለሺዓዎች ጥብቅና የሚቆሙትን ለአላህ ብለን እንጠላቸዋለን።
የአሕባሾች መስራች ዐብዱላህ አልሐረሪ፥ የጀመዐቱል ኢስላሚያህ መስራችና መሪ መውዱዲ፥ የኢኽዋን ቁንጮ የሆነው ሰይድ ቁጥብ ታላላቅ አስሓቦችን በኒፋቅ፥ በአመጽ፥ በኩፍር ይወነጅላሉ። በመሆኑም እኛ እነርሱንም ሆነ ለነርሱ ጥብቅና የሚቆሙትን በጠቅላላ ለአላህ ስንል እንጠላቸዋለን።
