Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ ክርስትናን (ነስራኒያን) መሲሒያ ማለት ወይም ክርሲቲያንን «መሲሒይ» ማለት ይቻላልን?

 
 
ጥያቄ፦ ክርስትናን (ነስራኒያን) መሲሒያ ማለት ወይም ክርሲቲያንን «መሲሒይ» ማለት ይቻላልን?

መልስ፦ ከነቢዩ ‏ ﷺ በኋላ ክርስቲያኖች መሲሒዮች (የመሲሁ ዒሳ ተከታዮች) መባላቸው ስህተት ነው። የመሲህ ተከታይ ቢሆኑ ኖሮ በሙሐመድም ‏ﷺ ባመኑ ነበር። በሙሐመድ ‏ﷺ ማመናቸው በመሲህ ዒሳ ቢን መርየምም ማመናቸው ነውና። አላህ እንዲህ ይላል፦

وَإِذْ قَالَ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ إِلَيْكُم مُّصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيَّ مِنَ التَّوْرَاةِ وَمُبَشِّرًا بِرَسُولٍ يَأْتِي مِن بَعْدِي اسْمُهُ أَحْمَدُ ۖ فَلَمَّا جَاءَهُم بِالْبَيِّنَاتِ قَالُوا هَٰذَا سِحْرٌ مُّبِينٌ

የመርየም ልጅ ዒሳም፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! እኔ ከተውራት በፊቴ ያለውን የማረጋግጥና ከእኔ በኋላ በሚመጣው መልክተኛ ስሙ አሕመድ በኾነው የማበስር ስኾን ወደእናንተ (የተላክሁ) የአላህ መልክተኛ ነኝ» ባለ ጊዜ (አስታውስ)። በግልጽ ተዓምራቶች በመጣቸውም ጊዜ «ይህ ግልጽ ድግምት ነው» አሉ።
[አል‐ሶፍ፡ 61፥6]

አልመሲህ ዒሳ ቢን መርየም በሙሐመድ ‏ﷺ መምጣት ያበሰሩት እሳቸው ይዘው በሚመጡት እንዲያምኑ እንጂ ለሌላ አይደለም። በማይጠቅም ነገር ማብሰር ጫወታ ነውና። በማይጠቅም ነገር ማብሰር ከሩሱሎችና ከኡሉልዐዝም አንዱ ከሆኑት ዒሳ ቢን መርየም ወለይሂ ሰላም ይቅርና ከአንድ ተራ ሰው እንኳ አይጠበቅም። ዒሳ ቢን መርየም የእስራኤል ልጆችን ያበሰሩት ሙሐመድ ‏ﷺ ናቸው። «… በግልፅ ታምራቶች በመጣላቸው ጊዜ ይሄ ግልፅ ድግምት ነው አሉ» የሚለው አንቀፅ የተበሰሩት ነቢይ በርግጥ የመጣላቸው ሲሆን በርሱ የካዱ (የከፈሩ) እና ይህ ግልፅ ድግምት ነው ማለታቸውን ያመለክታል። በሙሐመድ ‏ﷺ ካዱ ማለት ደግሞ በሙሐመድ ‏ﷺ ባበሰራቸው ዒሳ ቢን መርየምም ካዱ ማለት ነው። ስለዚህም መሲሒዮች (የመሲሁ ዒሳ ተከታዮች) ሊባሉ አይችሉም። መሲሒዮች ቢሆኑ ኖሮ መሲህ ቢን መርየም ባበሰራቸው ነቢይ ባመኑ ነበር። ዒሳ ቢን መርየምና ሌሎችም መልክተኞች በሙሐመድ ‏ﷺ እንዲያምኑ አላህ ቃል ኪዳን አስገብቷቸው ነበር።
አላህ እንዲህ ይላል፦

وَإِذْ أَخَذَ اللَّهُ مِيثَاقَ النَّبِيِّينَ لَمَا آتَيْتُكُم مِّن كِتَابٍ وَحِكْمَةٍ ثُمَّ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مُّصَدِّقٌ لِّمَا مَعَكُمْ لَتُؤْمِنُنَّ بِهِ وَلَتَنصُرُنَّهُ ۚ قَالَ أَأَقْرَرْتُمْ وَأَخَذْتُمْ عَلَىٰ ذَٰلِكُمْ إِصْرِي ۖ قَالُوا أَقْرَرْنَا ۚ قَالَ فَاشْهَدُوا وَأَنَا مَعَكُم مِّنَ الشَّاهِدِينَ

አላህ የነቢያትን ቃል ኪዳን ከመጽሐፍና ከጥበብ ሰጥቻችሁ ከዚያም «ከእናንተ ጋር ላለው (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ መልክተኛ ቢመጣላችሁ በርሱ በእርግጥ እንደምታምኑበት በእርግጥም እንድትረዱት ሲል በያዘ ጊዜ (አስታውስ)። አረጋገጣችሁን በዚህም ላይ ኪዳኔን ያዛችሁምን» አላቸው። «አረጋገጥን» አሉ። «እንግዲያስ መስክሩ፤ እኔም ከእናንተ ጋር ከመስካሪዎቹ ነኝ» አላቸው።
[አል‐ኢምራን፡ 3፥81]

ከነሱ ጋር ለነበረው (መፅሐፍ) አረጋጋጭ ሆነው የመጡት ሙሐመድ ‏ﷺ ናቸው።

وَأَنزَلْنَا إِلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِّمَا بَيْنَ يَدَيْهِ مِنَ الْكِتَابِ وَمُهَيْمِنًا عَلَيْهِ ۖ فَاحْكُم بَيْنَهُم بِمَا أَنزَلَ اللَّهُ ۖ وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَاءَهُمْ عَمَّا جَاءَكَ مِنَ الْحَقِّ ۚ

ወደ አንተም መጽሐፉን ከበፊቱ ያለውን መጽሐፍ አረጋጋጭና በእርሱ ላይ ተጠባባቂ ሲኾን በእውነት አወረድን። በመካከላቸውም አላህ ባወረደው ሕግ ፍረድ። እውነቱም ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌዎቻቸውን አትከተል።
[አል‐ማኢዳ፡ 5፥48]

እናም ክርስቲያኖች (ነሳራ) የአልመሲሕ ዒሳ ቢን መርየም ተከታዮች (መሲሒዮች) ናቸው ማለት ትክክል አይደለም። እውነታው አለመሆናቸውን ያሳያልና። በአልመሲህ ዒሳ ቢን መርየም ብስራት ክደዋልና። ማለትም በሙሐመድ ‏ﷺ ክደዋልና። በሙሐመድ ‏ﷺ መካዳቸው ደግሞ በዒሳ ቢን መርየምም መካዳቸው ነው።

[በሸይኽ መሐመድ ቢን ሷሊህ አል‐ዑሰይሚን ረሒመሁላህ]