“የተብራራ ሂስ (ትችት) ከሙገሳ ይቀድማል”
በቁርኣን እና በሱና የተመረኮዘ የሰለፎችን አካሄድ የሚከተሉ አህሉልሱንናዎች ዘንድ «ጀርሕ እና ተዕዲል» (ሂስ እና ሙገሳን) አስመልክቶ ካሉት ወርቃማ መርሆዎች ውስጥ መሠረት ነው ልንል በምንችልበት መልኩ የጎላ ተጠቃሽ አንድ መርህ አለ። እሱም. . «አልጀርሕ አልሙፈሰር ሙቀደም ዐላ አልተዕዲል» የሚል ሲሆን በቀላል አማርኛ “የተብራራ ሂስ (ትችት) ከሙገሳ ይቀድማል” በሚል መተርጎም ይቻላል። ይህም ሲተነተን በሂስ የታወቁ ሊቃውንት አንድን ሰው አሊያም ኪታብን ወይንም ጀመዐን አስመልክቶ የተብራራ ትችት ከሰጡ ሌላ ሊቅ ከሰጠው ሙገሳ ይበልጥ የነሱ ሂስ ቦታ ይሰጠዋል ወይንም ይቀድማል እንደማለት ነው።
የጀርሕ እና የተዕዲል ዑለማዎች ይህን መርህ ከቁርኣን እና ከሱና ብሎም ከሰለፎች ፋና ቂያስ አድርገው ያወጡት ሲሆን ይህ ቃዒዳ ለበርካታ ዓመታት በአህሉልሱንናህ ሊቃውንት ዘንድ ተፈጻሚ ሆኖ ቆይቷል።
ይህን መርህ አስመልክቶ ታላቁ ዐሊም ኢብን ከሢር (ረሒመሁላህ) ጠቅለል ባለ ዐረፍተ ነገር ሲገልጹት . .
“በጀርሕ እና በተዕዲል መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ፡ ጀርሕ ምንግዜም ቢሆን የተብራራ ሊሆን ይገባል። ታዲያ (ጀርሕ ከተዕዲል) ቀዳሚ ነውን? ወይንስ ብዛት ያለው ጀርሕ ነው መሆን ያለበት? ትክክለኛው መልስ በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን ጀርሕ የተብራራ ከሆነ (ከተዕዲል) ቀዳሚ ነው።” [ኢኽቲሳር ዑሉም አልሐዲሥ]
ታላቁ ዐሊም ሸይኸና ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ (ሐፊዘሁላህ) ይህንኑ መርህ አስመልክቶ ከተናገሩት እንመርቅ. .
“. . ብዙውን ግዜ እንዲህ እንላለን . . ‘ሰዎች እከሌን ሂስ ሰጡበት. .’ ፤ ‘ሂስ አልሰጡበትም. .’ ፤ ‘እነእከሌ እከሌን አሞገሱት.. ወይንም ሂስ ከተሰጠበት እከሌ ተከላከሉ. .’ የመሳሰሉትን. .
እኛ ከሂስ ሰጪዎቹ የተብራራ ትችት እንሻለን። እናም የሂሳቸውን ሰበብ ትክክለኝነት ካብራሩልን እነሱን መከተል በእኛ ላይ ግዴታ ይሆንብናል። ምክንያቱም ይህ ሐቅን መከተል ነው። ማስተባበሉ ደግሞ ሐቅን ማስተባበል ነው። የሚቃረናቸው ሰው ላይ እንኳን (እውነታውን) ሊቀበልና ወደ ሐቁ እና ትክክለኛው መንገድ ሊመለስ በርሱ ላይ ግዴታ ነው። ይህ በርግጥም ትልቅ ጉዳይ ነው።”
እንደው በአመክንዮ ደረጃም ምሳሌ መስጠት ይቻላል።
ለምሳሌ አንድ ሰው ልጅህን ለትዳር ፈልጓት ወዳንተ ሽማግሌ ይልካል። አንተም "እሺ ስልለልጁ አጣርቼ መልሱን እሰጣችኋለሁ" ብለህ ትመልሳቸዋለህ። ስለልጁ ማጣራት ያዝክ። በጣም በርካታ ሰዎች ስለልጁ ክፉ ክፉ ነገር አንስተው ከማስረጃ ጋር መረጃ ሰጡህ።
“ልጁ ዋሾ ነው!፤ ልጁ ለቤተሰቦቹ መልካም አይውልም! ልጁ ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ጥሩ አይደለም! ልጁ ወንጀል አዘውታሪ ነው! ልጁ ሶላትን አይሰግድም! ልጁ ሴት ልጅን ይማታል!፤ ልጁ ተደባዳቢ ነው!፤ ልጁ ሌባ ነው! ፤ ልጁ . . ” መሠል በርካታ ክፋት የተሰባሰበበት ልጅ እንደሆነ የምታምናቸው ወዳጆችህ በማስረጃ አስደግፈው ስለልጁ ማንነት አስረዱህ።
ሆኖም ግን በተቃራኒው አንድ ወይንም ሁለት ሌሎች የምታምናቸው ግለሰቦች ደግሞ ስለልጁ መልካምን ነገር ነገሩህ። “ልጁ የዋህ ነው! ልጁ ጨዋ ነው! ልጁ . .” እያሉ ስለልጁ የሚያውቁትን ያህል ነገሩህ።
ሁለቱም የምታምናቸው ሰዎች ከመሆናቸውም ጋር ሁለቱም ውሸታቸውን ላይሆን ይችላል።
ጥሩ! ጥያቄ ልጠይቅህና ሽማግሌዎቹ ቀጠሯችሁ ደርሶ ወደ አንተ ቢመጡ ልጅህን ልትድርላቸው ትችላለህን? መልስህ “በፍጹም!” እንደሚሆን አልጠራጠርም። ምክንያቱም ልጁ ላይ የሰማሀው የተብራራና በማስረጃ የተደገፈ ትችት አንድና ሁለት ሰው ካሞገሰው ሙገሳ ይበልጥብሃልና!።
ልክ እንዲሁ ዑለማዎች አንድ ሰው ላይ በርካታ የተብራራ ሂስ ሰጥተውበት ሲያበቁ ይህንን ግለሰብ በዲን ጉዳይ ላይ ተምሳሌት አድርጎ መያዝ ወይንም ንግግሮቹን ማዳመጥ ለውድቀት እንደሚዳርግ ቢያስጠነቅቁን በተቃራኒው ደግሞ አንድ ሌላ ዐሊም ይህን ሰው ቢያሞግሰው የማንን ይዘን የማንን እንደምንጥል ግልጽ እና ግልጽ ነው። ትችቱ የተብራራና በማስረጃ የተደገፈ እስከሆነ ድረስ ሙገሳውን ትተን ሂሱን ልንከተል ይህም ማለት ሸይኽ ረቢዕ እንዳሉን ሐቅን መከተል እንደሆነ ከአውምሯችን የሚሰወር አይሆንም።
ስለዚህም ወዳጄ! ዛሬ ላይ የፊትና ተጣሪዎችና የጥመት አራጋቢዎች በበዙበት ዘመን ዑለማዎች ለእኛ በማሰብና ከኢስላም የተጣለባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት ከነዚህ የጥመት ተጣሪዎች አስጠንቅቀውናል። እንደ አስፈላጊነቱ እከሌ እና እከሌ እያሉ በማስረጃ አስደግፈው እንጠነቀቃቸው ዘንድ በአጽንዖት መክረውናል።
ታዲያ አንዳንዴ እነዚህ በበርካታ ዑለማዎች ሂስ የተሰጠባቸው የፊትና ተጣሪዎች በግላቸው አሊያም በደጋፊዎቻቸው አማኻኝነት አንዳንድ ዑለማዎችን በተናጥል ስለነርሱ ምን እንደሚያስቡ ይጠይቁና ጥሩ ምላሽ ሲያገኙ በዛች ምላሽ ተንጠልጥለው የሌሎች በርካታ ዑለማዎችን የተብራራና በመረጃ የተደገፈ ትችት ሊንዱ ይሞክራሉ።
ነገር በምሳሌ ነውና . .
ለአብነት ያህል በፊትና አቀጣጣይነቱ የታወቀው ታላቁ የየመን የሓዳዲያዎች አባት የሕያ አልሐጁሪ በበርካታ ዑለማዎች ብዙ ግዜ የተብራራ እና በማስረጃ የተደገፈ ሂስ እና ትችት ተሰጥቶበታል።
ሂስ ከሰጡት ዑለማዎች በጥቂቱ . .
ሸይኽ ሙሐመድ አልወሷቢ፥ ሸይኽ አሕመድ አንነጅሚ፥ ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሃዲ፥ ሸይኽ ዐብዱ’ላህ አልቡኻሪ፥ ሸይኽ ዑበይድ ኢብን ዐብዱ’ላህ አልጃቢሪ፣ ሸይኽ ሐሰን ዐብዱል’ወሃብ አልበና፣ ሸይኽ ዐዲል አልመንሱር፥ ሸይኽ ዐሊይ አሕመድ አልራዚሂ፥ ሸይኽ ዐብዱል‘ዐዚዝ አልቡርዒ . . እና ሌሎችም በርካታ ዑለማዎች ተጠቃሽ ናቸው።
በእነዚሁ ዑለማዎች እኛ ከርሱ እንጠነቀቅ ዘንድ ምክር ተሰጥቶናል።
ሆኖም ደጋፊዎቹ “ትንሽ ቆሎ ይዘህ ከአሻሮው ተጠጋ” ነውና ብዙ ግዜ በተናጥል ዑለማዎችን ስለርሱ እየጠየቁ መልካምን ነገር እንዲናገሩ ጥረት ያደርጉ ነበር። ሰሞኑን ሸይኽ ፈውዛን ጋር ደውለው ድንገት ስለርሱ ሲጠይቋቸው ሰውየውን እንደማያውቁ ሆኖም ስለርሱ መልካምን እንጂ እንዳልሰሙ ይናገራሉ።
ድምጹ እንደሚከተለው ይላል . .
-----------
ጠያቂ ፦ “አስሰላሙ ዐለይኩም?”
ሸይኹ፦ “ወአለይኩም አስሰላም”
ጠያቂ፦ “ሸይኽ ሷሊሕ?”
ሸይኹ፦ “ነዐም”
ጠያቂ፦ “የሚቻል ከሆነ ክቡርነትዎ ጥያቄ ልጠይቆት እፈልግ ነበር?”
ሸይኹ፦ “ነዐም”
ጠያቂ፦ “እሺ ሸይኽ! ልጠይቆት የምፈልገው እዚህ ባለሁበት ሃገረ አሜሪካ የሸይኽ የሕያ አልሐጁሪን የድምጽ ቅጂዎችን መስማት እወዳለሁ። ነገር ግን አንዳንድ ወንድሞች መጥተው ከዚህ ሰው ያስጠነቅቁኛል። ምን ይመክሩኛል?”
ሸይኹ፦ “እኔ ሐጁሪን አላውቀውም። ነገር ግን ስለርሱ ጥሩን እንጂ አልሰማሁም።”
ጠያቂ፦ “ጥሩ! ታዲያ እርሶ የዚህን ሰው ድምጽ ቅጂ እና ሙሓደራ እንዳደምጥ ይመክሩኛልን?”
ሸይኹ፦ “ማድመጡን ከቻልክበት አድምጥ።”
_----------
ይሄኔ ይህንን የስልክ ምልልስ ቀደተው በርሱ ላይ የተሰጡ የተብራሩ ትችቶችን ሊንዱ ተጣጣሩ። ይህ የቂል አካሄድ ከመሆኑም ጋር የአህሉልሱናን መሰረታዊ የሂስና ሙገሳ መርህ የሚጥስ እንደሆነ እነርሱ ራሳቸው አጥተውት አይደለም። ነገር ግን ቀልባቸው ስልታመመባቸውና ስሜታቸውን ስለሚከተሉ እንጅ።
ይህንን ሽወዳቸውን ተውሰናቸው እንተግብረው ብንል የትኛውም ሙብተዲዕ ልንል በምንችለው መልኩ ቢያንስ ቢያንስ ከአንድ ታማኝ ዐሊም ሙገሳን ሊያገኝ ይችል ይሆናል። ታዲያ የአንድ ዐሊም ሙገሳ የሌሎች በርካታ ዑለማዎችን እርሱን አስመልክተው የሰጡትን ትችት ወዲያ አሽቀኝሮ ይጥላልን?
{{አታስተነትኑምን?}}
ለማንኛውም ሐዳዲዮች ጮቤ መርገጣቸውን ያቆሙ ዘንድ የሕያን አስመልክቶ ከሸይኽ ፈውዛን ሙገሳ ተቸረው የሚሉትን ጉዳይ ሌላ ዐሊም ተጠይቀው የሰጡትን ፈትዋ አንስተን ጽሑፉን እንቋጭ . .
ጸሐፊው እንዲህ ይላል. .
“ሸይኽ ሐሰን ዐብዱል ወሃብ ጋር ሰኞ እለት (ረቢዑል ሣኒ 4 ፤ 1438) ደወልኩላቸው . .
ሸይኽ ፈውዛን ጋር ስልክ ስለደወለውና ስለሐጁሪ ጠይቆ ሸይኽ ፈውዛን “እኔ ሐጁሪን አላውቀውም። ነገር ግን ስለርሱ ጥሩን እንጂ አልሰማሁም።” ስለማለታቸው ጉዳይ አስመልክቶ ጠየቅኳቸው. .
ሸይኹ የሰጡኝ ምላሽ ሸይኽ ፈውዛን ራሳቸው የሕያን እንደማያዉቁት (በንግግራቸው) እንደገለጹ ሆኖም ደግሞ እርሱን (የሕያ አልሐጁሪን) አስመልክቶ የተብራራ ትችት (ጀርሕ አልሙፈሰል) እንዳለና መቀበል ያለብን እሱን እንደሆነ ነገሩኝ።
በተጨማሪም ይህንን የስልክ ቃለምልልስ የሚያሰራጩ ሰዎች ከዑለማዎች የሕያን አስመልክቶ የተሰጡትን ትችቶች እንደማይቀበሉ ትክክልም እንዳልሆነ እንደሚያምኑ ለሸይኹ ስነግራቸው ሸይኹ. . “ትክክል አይደለም የሚሉን ማን ሆኑና!? እነሱ ከአዋቂዎች አይደሉም!” ብለው መልሰውልኝ ከየሕያ እና ከርሱም ውጭ ካሉት የቢድዓ አራማጆች የሚከላከሉት ሰዎች ጥርት ያለውን ትተው አምታች የሆነውን (ሙተሻቢህ) የሆነውን እንደሚከተሉ ነግረውኝ በሱረቱ አልዒምራን አያህ ቁጥር 7 ላይ ያለውን የጌታችን ቃል ቀርተውልኛል።
እንዲህ ይላል. .
{{أَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ ابْتِغَاءَ الْفِتْنَةِ وَابْتِغَاءَ تَأْوِيلِهِ}}
እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ፈተናን በመፈለግ እና የራሳቸውን ትርጓሜ በመፈለግ አሻሚ የሆነውን ይከተላሉ።
[ጥያቄውን ለሸይኹ የጠየቀውና ያስተላለፈልን አቡ ሲራህ አሕመድ ዩሱፍ አልዐረቢ ይባላል።]