መጽሐፍ “ቅዱስ” (ወንጌል) እንዴት ተለወጠ?
ኢብን ሐዝም (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ እንዳሉት. . ክርስቲያኖች ደግሞ፡ ዒሳ ምድር ላይ በቆየበት ግዜ እያለ ከመቶ ሃያ ሰዎች በቀር በእርሱ እንዳላልመኑ በመካከላቸውም ሆነ በሌሎችም ዘንድ ምንም አይነት ተቃርኖ የለም። በርሱ ያመኑት በጠቅላላ ደግሞ እርሱ ምድር ላይ እያለም ይሁን ወደ ሰማያት ካረገ በኋላ በፍርሃት የተነሳ እምነታቸውን ይደብቁ ነበር። ወደ ሐይማኖታቸው ይጣሩ የነበረው በሚስጥር ነበር። ማንም ሰው በግልጽ አይጣራም ወይንም የአምልኮ ተግባሩን በግልጽ አይፈጽምም። ምክንያቱም ይህን ሲያደርግ የተገኘ ሁሉ በድንጋይ ተቀጥቅጦ ወይንም በሰይፍ ተቀልቶ አሊያም በመርዝ ይገደል ነበር።
መሲህ (የአላህ ሰላም በርሱ ላይ ይሁን) ወደ ሰማያት ካረገ ወዲያ በዚህ አይነት ሁኔታ ለሶስት መቶ ዓመታት ያህል ቆዩ። በዚህ ግዜያት ነበር ከአላህ ያወረደው ወንጌል ለሙግታቸው እና እነሱን ለማሳፈር ይቀር ዘንድ አላህ ከፈቀደው በቀር ሊጠፋ የቻለው።

ከዚህ ቀደም እንደጠቀስነው አጼ ቆንስጣንጢኒዮስ ክርስትናን ሲቀበል ክርስቲያኖች የበላይነት አገኙ። እናም እምነታቸውን በግልጽ ማራመድ ጀመሩ። በአደባባይ ያለምንም ስጋት መሰባሰብና መተግበር ጀመሩ።
ሐይማኖት በዚህ መልኩ ከሆነ የሚተላለፍልን ንግግር ምንጭ ተዋረዳዊ የአስተላላፊዎችን ሰንሰለት ምን ያህል አስተማማኝ እንደሆነ ለማወቅ አዳጋች ነው። ምክንያቱም እነዚህ አስተላላፊዎች ሰይፍን ፈርተው ይህንን የሚያደጉት በድብቅ ነውና። በመሆኑም ሊከላከሉት ወይንም ከመዛባት ሊታደጉት አይቻላቸው።
ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚይያህ (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ይላል፦ ክርስቲያኖች እጅ ላይ ያለው ወንጌል በአራት ወንጌሎች የተዋቀረ ነው። እነርሱም የማቴዎስ ወንጌል፤ የሉቃስ ወንጌል፤ የማርቆስ እና የዩሐንስ ወንጌል ሲሆኑ በሁሉም ስምምነት መሰረት ሉቃስ እና ማርቆስ ዒሳን አላዩትም። ባይሆን ያገኛቸው ማቴዎስ እናዮሐንስን ብቻ ነበር። እነኚህ አራቱም ወንጌሎች የተጻፉት ዒሳ ወደ ሰማያት ካረገ ወዲህ ነው። ሆኖም ይህ የአላህ ንግግር ነው ግን አላሉም። ዒሳም ከአላህ የተተላለፈለት ነውም አላሉም ሆኖም የተወሰኑ ንግግሮችን ከዒሳ ተቀብለው አስተላልፈዋል። የተወሰኑ ተግባራቶቹን እና የተወሰኑ (በአላህ ፍቃድ የተሰጡትን) ተዓምራቶች።
[አልጀዋብ አልሶሒሕ ሊምን በደለ ዲነል’መሲህ]
by Abu Aisha