Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ልጅቱ የምትፈልገው #ድሃውን. .! ቤተሰቦቿ (ወሊዮቿ) ደግሞ #ሐብታሙን ካላገባሽ. .!


ልጅቱ የምትፈልገው #ድሃውን. .! ቤተሰቦቿ (ወሊዮቿ) ደግሞ #ሐብታሙን ካላገባሽ. .!
ኢብን ዐባስ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፦
أن رجلاً قال : يا رسول الله ، في حجري يتيمة قد خطبها رجل موسر ورجل معدم ، فنحن نحب الموسر ، وهي تحب المعدم ، فقال - صلى الله عليه وسلم - : لم ير للمتحابين مثل النكاح
« አንድ ሰው አለ፦ "የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንድን የቲም ልጃገረድ አሳድጌ ነበር። ሁለት የትዳር ጥያቄዎች መጡላት። አንዱ ሐብታም ሲሆን አንዱ ደግሞ ድሃ። እኔ ሐብታሙን እንድታገባ ፈልጌ ነበር። ሆኖም እርሷ ድሃውን ማግባት ፈለገች። ምን ላድርግ?»
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉት፦ «ለሁለት ለሚዋደዱ ሰዎች እንደትዳር ያለ (መልካም፥ ምርጥ ነገር) ምንም የለም!»
[ሙስተድረክ አልሐኪም 216፤ በይሃቂ ኪታቡ ኒካ 778 አልባኒ «ሶሒሕ» ብለውታል. . አስ_ሶሒሓህ እና ሶሒሕ አልጃሚዒ]

Abu Aisha