Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ልኢማም ረቢዕ አልመድኸሊ (ሐፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ

አልኢማም ረቢዕ አልመድኸሊ (ሐፊዘሁላህ) እንዲህ አሉ፦
« አማኝ የሆነ ሰው ሁሌም ያለሁበት ሁኔታ ይቀየራል በሚል ይሰጋል።
ከዓኢሻ እና ከአነስ ረዲየላሁ ዐንሁማ በተያዘው ሐዲሥ :
ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም . .
«ቀልቦችን ገለባባጭ የሆንከው ጌታ ሆይ! ቀልቤን በእምነትህ ላይ አጽናልኝ» ማለትን ያበዙ ነበር...
እኔም . . «አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ባንተ እና ይዘኸው በመጣከው ነገር አምነናል። በእኛ ላይ ትሰጋለህን?» ስል ጠየቅኳቸው. .
እንዲህ አሉኝ. . «አዎን! ቀልብ እኮ ከአላህ አዝ_ዘወጀል ጣቶች በሁለት ጣቶቹ መካከል ነች። እንዳሻውም ይገለባብጣታል።»

ወላሂ ይህ ነው ግንዛቤ ማለት. .
ማንም ሰው በነፍሱ ሊተማመን አይገባም!
ምክንያቱም «ሸይጧን በአደም ልጅ የደም ስር ይዘዋወራል።»
ስለዚህ ማንም ሰው በቀልቡ፥ በአእምሮው፥ በተግባሩ ላይ እጅጉን ተጠባባቂ ሊሆን ይገባል። ገንዘቡንና ክብሩን ከሚጠብቀው በላይ. .! (ቀልቡን ከጥመት) ሊጠብቅ ይገባል።
ከምንም ነገር ቀድሞ ቀልቡን መጠባበቁ ላይ ጥንቁቅ ሊሆን ይገባል።
(( (እነርሱም ይላሉ) ፦ ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን (ወደ ጥመት) አታዘምብልብን፤ ከአንተ ዘንድ የሆነን ችሮታም ለኛ ስጠን፤ አንተ በጣም ለጋስ ነህና። )) [አልዒምራን፡8] »
[መርሓበን ያ ጧሊበል ዒልም ገጽ 75]
Abu Aisha