ወሰጢያ ሰለፎች የተጓዙበት ጎዳና እንጂ ኸለፎች የነጎዱበት የጥመት መንገድ አይደለም!
አዎን! ከሌሎች ሐይማኖቶች አንፃር ሲታይ ኢስላም መካከለኛ ሐይማኖት ነው፡፡ ኢስላም ውስጥ ካሉ ሌሎች ቡድኖች አንፃር ሲታይ ደግሞ የአህሉልሱንና አካሄድ መካከለኛ አካሄድ ነው፡፡ በኢስላምና በሌሎች ሐይማኖቶች ካለው ፍጥጫ ይልቅ በአህሉሱና እና በአህሉል ቢድዐህ መካከል ያለው ፍጥጫ የከፋ እንደሆነ ኢብኑ ተይሚያ ተናግሯል፡፡ በርካታ የጥመት አራማጆች ያሉበትን የተሳሳተ አካሄድ "ወሰጢያ" (መካከለኛ አካሄድ) በማለት የተቃወማቸውን ሁሉ ጠርዘኛ አድርገው ሊያሳዩ ይውተረተራሉ፡፡
ወሰጢያ (መካከለኛ አካሄድ) ማለት ቁርኣንና ሱና ላይ የተገነባ መስመር እንጂ በሐቅና በባጢል መካከል የሚገኝ ሐሳባዊ መስመር አይደለም!! በታሪክ በርካታ የሱና ጠላቶች መካከለኛውን መንገድ /ወሰጢያን/ እነሱ የያዙት መሃል ሰፋሪ መንገድ አድርገው ለማሳየት ሲጥሩ፣ የሱና ሰዎችን ፅንፈኛ፣ ሒክማ ያልገባቸው፣
ጭራቅ ፣ አውሬ … አድርገው ሲስሉ በአንፃሩ ግን ሶሃባ የሚሳደቡትን፣ ለሽርክ የሚያራግቡትን፣ ሙስሊሙን በጅምላ የሚያከፍሩትን፣ ወዘተ.. . ሲያደንቁና ሲክቡ ይታያሉ፡፡
ጥንቃቄ፡
1. ቴክኖሎጂ ስለረቀቀ፣ ዐለም “ስለሰለጠነ”፣ ሺርክ ተውሂድ አይሆንም፣ ቢድዓም ሱና አይሆንም፡፡ ሺርክና ቢድኣ በተወገዘ ቁጥር “ፈትዋ ከቦታና ከጊዜ አንፃር ሊቀያየር ይችላል” በሚል ማማኸኛ የደዕዋ እንቅፋት የሚሆኑ ስንቶች ናቸው?
እነሱ ደቂቅ ኢስላማዊ ጉዳዮች ውስጥ ገብተው ሲያቦኩ ምንም ሳይባሉ ሌላው መሠረታዊ የተውሂድ ጉዳይ ላይ ሲፅፍ/ ሲናገር “ያላቅምህ ፈትዋ አትስጥ” ሲሉ “ይመክራሉ፡፡” እራሳቸውን ውቅያኖስ ሌሎችን ኩሬ አድርገውም ያቀርባሉ፡፡ ይህን የተሳሳተ አካሄዳቸውንም “ወሰጥያ” ብለው ኒሻን ያጠልቁለታል፡፡
ከዚያስ?
ከዚያማ የተቃወማቸውን ሁሉ ከወሰጥያ የወጣ ጠርዘኛ አድርገው ያቀርባሉ፣ ያወራሉም፡፡ በተለይም በዚህ
ዘመን የሙብተዲዖች ሁሉ መጠለያ #የውሸት_ወሰጥያነው፡፡ የመረጃ ማጣፊያው ሲያጥራቸው የራሳቸው “ወሰጥያ” ሊፈጥሩ ይሞክራሉ፡፡
2. ስለወሰጢያ ሲወራ ሁሌም ሊታሰብ የሚገባው ነገር ቢኖር ሽርክና ቢድዓን ማውገዝ፣ አጥፊን ማስጠንቀቅ የወሰጥያ ዋና መገለጫው መሆኑ ነው፡፡ ለዚህም ከጥንት ጀምሮ የዓሊሞቻችን አካሄድ ዋቢ ምስክር ነው፡፡
- ወሰጥያ በሁለት ጠርዘኛ አቋሞች መካከል የሚገኝ ሐቅ እንጂ በሀቅና በባጢል መካከል የሚገኝ ሸዋጅ/ማታለያ መንገድ አይደለም፡፡
- ወሰጥያ መረጃን መሰረት አድርጎ በመልካም የሚያዝ ከመጥፎ የሚከለክል አካሄድ እንጂ የአህሉሱንና ስም የሚጠፋበት ሙብተዲዕ የሚደነቅበት አካሄድ አይደለም፡፡ ሆኖም አያውቅም!
አንድ ዘፈንን የሚፈቅድ ሰው ዘፈን የሚከለክለውን ጠርዘኛ ቢል፣
አንድ የሶሃባን ክብር የሚያንቋሽሽ ሰው ተቃውሞ ሲያጋጥመው “ጠርዘኛ አትሁኑ” ቢል፣
አንድ የአላህን ትክክለኛ መገለጫዎች የሚያስተባብል የቢድዓ አራማጅ የሚቃወመውን “ሰፋ በል አታካብድ” እያለ በ“ወሰጥያ” ቢያታልል አንድ ሰሞን ነው የሚሸውደው፣ እሱም ከተሳካ፡፡ ያለበለዚያ ኢስላማችንን ሊበክል የመጣውን የአሕባሽ አመለካከት “መጅሊሱን ስለያዘብን ብቻ ነው የምንቃወመው”
እያለ ወደ “ወሰጥያ” ቢጣራ ማንን ይሸውዳል? የሱው ቢጤ ስልጣን ናፋቂዎችን ካልሆነ በቀር?