Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መንሃጅ አስሰለፊ ሸይኽ አልፈቂህ ሱለይማን አርሩሐይሊ



የሰለፊ አካሄድ

ጠያቂ፦ «በመንሃጅ አስሰለፊ ላይ እና ዛሬ ላይ ሁሉም ወደ ሐቅ እንጣራለን ስለሚሉት አንጃዎች ማብራሪያ እና ገለጻ እንዲሰጡኝ እጠይቃለሁ?»

መልስ፦ ከሸይኽ አልፈቂህ ሱለይማን አርሩሐይሊ (አላህ ይጠብቃቸው)፦
« በአጠቃላይ. .

የሰለፊ አካሄድ፡ በሌሎች ላይ በፍጹም ማለባበስ የሌለበት ፍንትው ያለ አካሄድ ነው።

የሰለፊ አካሄድ፡ አካሄዱ የተመሠረተው አላህን ፍጹም በሆነ መልኩ በአምልኮ ማጥራት (አልኢኽላስ) እና መልእክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መከተል (ሙታበዓህ) ላይ ነው።

የሰለፊ አካሄድ፡መሠረቱ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃል ነው. .

(فَلا وَرَبِّكَ لا يُؤْمِنُونَ حَتَّى يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا)

(( በጌታህም እምላለሁ: በመካከላቸው በተከራከሩበት ጉዳይ አንተን ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም በፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ቅሬታ እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም።)) [ሱረቱል ኒሳእ 65]

የሰለፊ አካሄድ፡ መሠረቱ እንዲህ የሚለው የአላህ መልእክተኛ ቃል ነው. .

«ከእናንተ ውስጥ ወደፊት በሕይወት የሚቆይ ብዙ አለመግባባቶችን ይመለከታል። (እነዚህ ኺላፎች በተከሰቱ ግዜ) በሱንናዬ ላይ እና ቅኑን መንገድ በተመሩት ተተኪዎቼ ሱንናህ ላይ አደራ! በርሷ ላይ የሙጢኝ በሉ። በክራንቻ ጥርሳችሁ አጥብቃችሁ ያዟት። (በሐይማኖት ጉዳይ ላይ) አዳዲስ መጤ ጉዳዮችን አደራ! ሁሉም መጤ ነገር ቢድዐህ ነው። ሁሉም ቢድዐህ ጥመት ነው።»

የሰለፊ አካሄድ፡ የተመሠረተው አላህ _አዝዘወጀል_ የዚህ ኡማ መጀመሪያ ባስተካከለበት ላይ ነው። እርሱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እና ባልደረባዎቻቸው የነበሩበት (ጎዳና) ነው።

የሰለፊ አካሄድ፡ የተመሠረተው ቢድዐን እና የግል ዝንባሌ መከተልን ከነባልተቤቶቹ መራቅ ላይ ነው።

የሰለፊ አካሄድ: የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱናን መርዳት ላይ እና ቢድዐን በመመለስ ብሎም ባለቤቶቹን በማጋለጥ እና ሁኔታቸውን በማብራራት፤ ከነርሱ የሚመጣውን ክፋት በማስጠንቀ ላይ ትግል ማድረግ ላይ መሠረት የጣለ ነው።

የሰለፊ አካሄድ: ከተቃራኒው ጋር ፍጹም አይቀላቀልም። የቁርኣን፣ የሱና፣ የዒልም፣ የግልፅ ማስረጃ፣ (ሰለፎችን) የመከተል አካሄድ ነው።

የሰለፍ አስሷሊሕ አካሄድ: እይታቸው በአላህ የተበራላቸው ማንኛውም ሰዎች ዘንድ ሊታይ የሚችል ነው።

የሰለፉነ አስሷሊሕን አካሄድ የሚቃረኑ አንጃዎች በዘረዘርናቸው ነገራቶች ላይ ሁሉ የሰለፎችን መንገድ ይጻረራሉ።

ከሰለፊ ባህሪያት መካከል: ሰዎችን በሸሪዐህ እንጅ ሸሪዐህ በሰዎች አይመለከትም፤ ብዙኃንን ቢቃረንና ጥቂቶች ብቻ እንኳን ቢቀበሉት ሸሪዐን ከሰዎች ዝንባሌ አያስቀድም፤ በሁሉም ጉዳዮች ላይ የመልእክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሱናን እና ጥራት የተገባው ጌታችንን ኪታብ ከብዙኃኑ ያስቀድማል።

ነገር ግን ቡድንተኞች ሸሪዐን የሚመለከቱት በሰዎች አይን ነው። ሰዎች የሚወዱትን ወይንም ብዛታቸውን የሚጨምርላቸው ካልሆነ በቀር ለሰዎች አያቀርቡ። ሰዎች በቀኝ በኩል ያለውን መውደዳቸውን ከተመለከቱ በቀኝ በኩል ይሄዳሉ ያጋንናሉም። ሰዎች በግራ በኩል ያለውን መውደዳቸውን ከተመለከቱ በግራ በኩል ይሄዳሉ ያጋንናሉም። ሰዎች ማቆየትን መውደዳቸውን ከተመለከቱ ያቆያሉ። ሰዎች መውጣት መውደዳቸውን ከተመለከቱ ይወጣሉ። ይህንን በቁርኣን እና በሱና አይመለከቱም። እነርሱ የሚመለከቱት ሰዎችን የሚያስደስታቸውን እና ብዛታቸውን የሚጨምርላቸውን ብቻ ነው።

ለማንኛውም፡ ይህ ጉዳይ በቀላሉ የሚገኝና የተጻፈ ነው። እናም ለማብራራት ረዥም ግዜን የሚፈልግ ነው። ሆኖም የጠቆምኩትን ያህል ጠቁሜ ብዙ ብዙ ማለት ቢቻልም እዚህ ጋር አበቃለሁ።»

[በድምጽ ለማድመጥ ይህንን ሊንክ ይጫኑ


bosted by brother Abu Aisha