መልካም ጥርጣሬ (ሑስነ ዞን) የምታሳድርበትን ቦታ እየለየህ!
ከእናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ተይዞ እንዲህ ብላለች።
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህቺን አንቀፅ ቀሩ
" هو الذي أنزل عليك الكتاب منه آيات محكمات هن أم الكتاب وأخر متشابهات فأما الذين في قلوبهم زيغ فيتبعون ما تشابه منه ابتغاء الفتنة وابتغاء تأويله وما يعلم تأويله إلا الله والراسخون في العلم يقولون آمنا به كل من عند ربنا وما يذكر إلا أولو الألباب {7} " آل عمران( 7 )
"እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሐፉን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ (ከመጽሐፉ) ፍንትው ያሉ አንቀጾች አልሉ፡፡ እነሱ የመጽሐፉ መሠረት ናቸው፡፡ ሌሎችም ተመሳሳዮች (አሻሚ ገፅታ ያላቸው) አልሉ፡፡ እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ፈተናን በመፈለግና ተእዊሉን ለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ፡፡ (ትክክለኛ) ተእዊሉን ከአላህ በስተቀር ማንም አያውቀውም፡፡ በእውቀትም የጠለቁት «በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው» ይላሉ፡፡ የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም፡፡"
ከዚያም እንዲህ አሉ:
" فَإِذَا رَأَيْتِ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ فَأُولَئِكِ الَّذِينَ سَمَّى اللَّهُ، فَاحْذَرُوهُمْ ".
"እነዚያን ከሱ (ከቁርኣኑ) የተመሳሰለውን የሚከተሉ ሰዎችን ካያችሁ እነሱን ነው (በአንቀጿ) ውስጥ የጠቀሳቸው። ስለሆነም #ተጠንቀቋቸው።"
[ቡኻሪና ሙስሊም]
ከሐዲሡ ከሚወሰዱ ቁም ነገሮች ውስጥ
① ቁርአናዊ አንቀፆች "ሙሕከም" እና "ሙተሻቢህ" ተብለው ለሁለት እንደሚከፈሉ፣
② ሰዎችም ከዚህ በመነሳት ለሁለት እንደሚከፈሉ፣
③ "በሙሕከሙ" የሚሰሩት ሁሉም ከአላህ ነው ብለው እንደሚያምኑ፣
④ "ሙሕከሙን" ችላ ብለው "ሙተሻቢህ" ላይ የሚያነጣጥሩት ፈተና አነፍናፊዎችና በልባቸው ውስጥ የስሜት በሽታ ያለባቸው እንደሆኑ፣
⑤ እነዚህ በሽተኞች ላይ መልካም ጥርጣሬ (ሑስነ ዞን) ልናሳድር እንደማይገባን፣
ከዘገባው ከምንማራቸው ቁም ነገሮች ውስጥ ከፊሎቹ ናቸው።