#ደወል_ለገጣሚዎች!
ግጥም መልእክትን በአጭር የመግለፅ፣ ከልብ ውስጥ አልፎ የመስረፅ አቅም አለው። መብዛቱ ባይበረታታም ግጥም ልክ እንደ ስድ ፅሁፍ በጎ መልእክት ያዘለው የሚወደድ፣ መጥፎ መልእክት ያዘለው ደግሞ የሚወገዝ ነው።
አንድ ሐቅ ግን አለ። ገጣሚዎች በብዛት ጋየ ወጦችን ለማርካት ሲሉ ጋረ ወጥ መልእክቶችን የሚያስተላልፉበት አጋጣሚ ብዙ ነው። በረቀቀ ቋንቋ ርካሽ አመላቸው ስለሚሰበክላቸውም በርካታ ጋጠ ወጦች ከገጣሚዎች ኋላ ይልከሰከሳሉ። ገጣሚዎች ስለመልካም ነገር ቢሰብኩም ብዙ ጊዜ ግብራቸውና ቃላቸው አይገናኝም። ይህንን እውነታ አላህ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል-
وَالشُّعَرَاءُ يَتَّبِعُهُمُ الْغَاوُونَ(٢٢٤) أَلَمْ تَرَ أَنَّهُمْ فِي كُلِّ وَادٍ يَهِيمُونَ(٢٢٥) وَأَنَّهُمْ يَقُولُونَ مَا لَا يَفْعَلُونَ(٢٢٦) إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَذَكَرُوا اللَّهَ كَثِيرًا وَانْتَصَرُوا مِنْ بَعْدِ مَا ظُلِمُوا ۗ وَسَيَعْلَمُ الَّذِينَ ظَلَمُوا أَيَّ مُنْقَلَبٍ يَنْقَلِبُونَ(٢٢٧) " سورة الشعراء
"ባለ ቅኔዎችንም ጠማማዎቹ ይከተሏቸዋል፡፡ እነርሱ በ(ንግግር) ሸለቆ ሁሉ የሚዋልሉ መሆናቸውን አታይምን? እነሱም የማይሠሩትን ነገር የሚናገሩ መሆናቸውን (አታይምን?)፤ እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ አላህንም በብዛት ያወሱ፣ ከተበደሉም በኋላ (በቅኔ) የተከላከሉ ሲቀሩ፤ (እነርሱ አይወቀሱም)፡፡ እነዚያም የበደሉ (ከሞቱ በኋላ) እንዴት ያለን መመለስ እንደሚመለሱ በእርግጥ ያውቃሉ፡፡" [ሹዐራእ: 224–227]

