..... የስም ልጠፋው አላዋጣ ካለ ህይወት እስከማጥፋትም ሊሸጋገሩ ይችላሉ፡፡ በዚህ ረገድ በቢድዐህ አራማጆች በኩል አቡ ኢስማዒል አልሀረዊ ላይ ተጠንስሶ የነበረው ሴራ መቼም የሚረሳ አይሆንም፡፡ እነዚህ የቢድዐህ ሰዎች ከሸይኹ መስገጃ ስር ከነሀስ የተሰራ ትንሽ ጣኦት ደብቀው ይወጣሉ፡፡ ከዚያም በጊዜው የነበረው ገዢ ዘንድ ተሰብስበው “ፈጣሪን በፍጡር ቅርፅ የሚገልፅ ነው! ከሚሕራቡ ስር የአላህ አምሳል ነው እያለ የሚያስበው ጣኦት አለው” ለገዢውም ሰው ቢልክ እንደሚያገኘው አስረግጠው ነገሩት፡፡ ገዢው ነገሩ እየከበደው ሰዎችን ይልካል፡፡ ሲደርሱ ጣኦቱን ያገኙታል፡፡ ይህኔ ገዢው ሸይኽ አልሀረዊን እንዲገኙ ያደርጋል፡፡ ሸይኹ እንደደረሱ ጣኦቱንም የተሰባሰቡትን መሻኢኾችንም ተመለከቱ፡፡ ገዢው ቁጣው ገንፍሏል፡፡ “ይሄ ምንድን ነው?” አላቸው፡፡ “አሻንጉሉት የሚመስል ከመዳብ የተሰራ ጣኦት ነው” አሉት፡፡ “ስለሱ አልጠየቅኩህም?” አላቸው፡፡ እናስ ስለምን ኖሯል የምትጠይቀኝ?” አሉት፡፡ እነዚህ ሰዎች አንተ ይህን እንደምታመልክ እና “አላህ የዚህ አምሳል ነው እንደምትል እየሞገቱ ነው?” አላቸው፡፡ ሸይኹ ይህኔ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ጥራት ይገባህ! ይሄ በርግጥም ትልቅ ቅጥፈት ነው” የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አነበቡ፡፡ ገዢው ይህኔ ሰዎቹ የሰሩት ተንኮል እንደሆነ ተረዳና ሸይኹን በክብር ወደቤታቸው እንዱመለሱ አደረገ፡፡ ከዚያም የተሰበሰቡትን መሻኢኾች እውነቱን እንዱያወጡ ሲያስፈራራቸው “እኛ ይሄ ሰውየ ህዝቡን ስለተቆጣጠረው እያስቸገረን ነው፡ ፡ እናም ተንኮሉን ለመገላገል ፈልገን ነው ይህን ያደረግነው” አሉት፡፡ [ተዝኪረቱልሑፋዝ፡ 3/358]
________
ሸይኽ አቡ ኢስማዒሌ አልሀረዊን አላህ ይማራቸውና የቢድዐህ ሰዎች ላይ ብርቱ ነበሩ፡፡ በዚህም ሳቢያ በተደጋጋሚ ህይወታቸው ለአደጋ ተጋርጧል፡፡ ሸይኹ እራሳቸው “አምስት ጊዛ ለሰይፍ ቀርቤያለሁ፡፡ (ለመገደል ስቀርብ) ከአካሄድህ ተመለስ” ሳይሆን ‘በሚፃረሩህ ላይ መልስ ከመስጠት ዝም በል’ ነበር ይሉኝ የነበረው፡፡ ‘ዝም አልልም’ እል ነበር” ይላሉ፡፡ [አልኣዳቡሽሸርዒያህ፡ 1/207]
______
[በ Ibnu Munewor ከተጻፈው ተውሒድ፡ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ከሚለው መጽሐፍ ገጽ 178-179 የተወሰደ 1ኛ እትም]
