Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ ትላለች . .


ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ ትላለች . .
« አንድ ግዜ የአላህ መልእክተኛን በመልካም ሁኔታ ላይ ሆነው ተመለከትኳቸው። እንዲህም አልኳቸው ፡
“የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ዱዐህ አድርጉልኝ?”
እሳቸውም፡ "አላህ ሆይ! የዓኢሻን የቀደመውንም ሆነ የወደፊቱን ፤ የደበቀችውንም ይሁን ግልጽ ያወጣችውን ወንጀል ማራት።"
ከዚያም እኔ በደስታ ምክንያት ጭንቅላቴ የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን ባት እስኪነካ ድረስ መሳቅ ጀመርኩ።
የአላህ መልእክተኛም፡ "ዱዐዬ አስደሰተሽን?" ብለው ጠየቁኝ
እኔም፡ "እንዴታ! የርሶ ዱዐህ እንዴት አያስደስተኝም?" አልኳቸው
እሳቸውም፡ "ወላሂ! ይህ በእያንዳንዱ ሶላቴ ለኡማዬ የማደርገው ዱዐህ ነው።'' አሉኝ
[ምንጭ፡ ሶሒሕ መዋሪድ አዝ፡ዘማን (1875) እና በሲልሲለቱ አስ፡ሶሒሓህ (2254)]