Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለተወሰኑ የጥመት ቡድኖች መጠን ያለ እይታ (ክፍል 2 - «ጀህሚያ»)

ስለተወሰኑ የጥመት ቡድኖች መጠን ያለ እይታ
(ክፍል 2 - «ጀህሚያ»)

ጸሐፊ፡ አልኢማም ሙሐመድ ቢን አልዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸው)
ምንጭ፡ የኢብን ቁዳማህ “ሉምዐቱል-ኢዕቲቃድ” ማብራሪያቸው ላይ
(ገጽ 162)

2. «አልጀህሚይ-ያህ»

የሚጠጉት ወደ አልጀህም ቢን ሶፍዋን ወደተባለ በሳሊም ወይንም በሰሊም ቢን አሕወዝ በ121 ዓመተ ሂጅራ የተገደለ ግለሰብ ነው። በአላህ ባሕሪያት ላይ አካሄዳቸው “ተዕጢል” (የአላህን ባሕሪያት በከፊልም ይሁን በሙሉ አለመቀበል (መጣል))፤ “ነፍይ” (የአላህን ባሕሪያት ማሳጣት) ፤ በቀደር (በአላህ ውሳኔ) ደግሞ በጀብር (ጀብር ወይንም ጀብርሪያህ ተብለው የሚታወቁት “የሰው ልጅ የራሱን እጣ ፈንታ በራሱ ይወስናል። አላህ በሰዎች ጉዳይ ሁኔታው እስከሚፈጸም ድረስ አያውቅም” የሚል ሰቅጣጭ እምነት ) አስተሳሰብን ሲይዙ በኢማን (በእምነት) ደግሞ የ”ኢርጃእ” እሱም ኢማን በልብ የሚቋጠር ብቻ ሲሆን ንግግርና ተግባር የኢማን አካላት አይደሉም የሚል እምነት ባለቤቶች ናቸው። በመሆኑም በእነርሱ አስተሳሰብ ከባድ ወንጀልን የፈጸመ ግለሰብ ሙሉ የሆነ ኢማን አለው ማለት ነው። ስለሆነም ጀህሚያዎች ሙዐጥጢላህ፥ ጀብርሪያህ፥ ሙርጂኣዎች ሲሆኑ በብዙ ይከፋፈላሉ። . .