ስለተወሰኑ የጥመት ቡድኖች መጠን ያለ እይታ
(ክፍል 1 - «ሯፊዷ»)
ጸሐፊ፡ አልኢማም ሙሐመድ ቢን አልዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸው)
ምንጭ፡ የኢብን ቁዳማህ “ሉምዐቱል-ኢዕቲቃድ” ማብራሪያቸው ላይ
(ገጽ161-162)
የቢድዓ ሰዎችን የሚጠቁሙ የተወሰኑ ምልክቶች አሉ። ልክ እንደ . .
1. ከቢድዐ አዲስ በፈጠሩት ነገር ላይ በንግግርም፥ በተግባር እና በእምነት ከኢስላምም ሆነ ከሱንናህ ውጭ ወዳለ ነገር ራሳቸውን ያስጠጋሉ።
2. በአመለካከታቸው ላይ ጭፍን ተከታይ ሆነው ሐቅ እንኳን ግልጽ ቢደረግላቸውም ወደ (ሐቁ) አይመለሱም።
3. የኢስላምን እና የዲን አዋቂዎችን (ኢማሞችን) ይጠላሉ።
ከነርሱ አንጃዎች መካከል . .
1. «አር-ሯፊዷ»
እነርሱ በ”ኣሉ በይት” (በነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤተሰቦች) ላይ ድንበርን የሚያልፉ ሲሆኑ ከነርሱ የተቃረኗቸውን ሶሓባዎች የሚያከፍሩ ወይንም በወንጀል (በፊስቅ) የሚከሱ ናቸው። ራሳቸው ለየቅል የተከፋፈሉ ሲሆን ከነርሱ ውስጥ እጅጉን ወሰን የተላለፉት “ዐሊይ ጌታ ነው” የሚሉት እና ከነርሱ ውጭ ያሉት ናቸው።
የመጀመሪያ ቢድዐቸው ግልጽ የታየው በዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብ ኺላፋ ግዜ ሲሆን ዐብደ’ላህ ቢን ሰባእ (ዐሊይን) “አንተ ጌታ ነህ” ሲለው ነው። ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲቃጠሉ ያዘዘ ሲሆን ይህን የዐብደ’ላህ ቢን ሰባእ አስተሳሰባቸውንም እንዲወድም አድርጎ ተዋግቷቸዋል።
[ማስታወሻ፡ ዐሊይረዲየላሁ ዐንሁ እነዚህን ሰዎች እንዲቃጠሉ ሲያዝ ከሶሓቦች መካከል የተቃወሙት ያሉ ሲሆን እንደ ዐብዱ'ላህ ኢብን መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ የመሳሰሉት ሶሓቦች የተወሰደውን የሞት እርምጃ ቢደግፉም በተለየ መልኩ ተፈጻሚ ቢሆን "መልካም ነበር" ብለዋል። ለዚህ አስተያየታቸው መነሻ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም «የእሳቱ ጌታ እንጂ ማንም ፍጡር ማንንም በእሳት አይቀጣም።» ከሚለው ግሳጼ ነው።)
በአላህ ባሕሪያት ላይ ያላቸው አቋም የተለያየ ነው። ከነርሱ ውስጥ “ሙሸቢህ” (አላህን ከፍጡር አመሳሳይ) ፤ ከነርሱ ውስጥ “ሙዐጢል” (የአላህን ባሕሪያት በከፊልም ይሁን በሙሉ የማይቀበል (የሚጥል))፤ ከነርሱም ውስጥ (የአላህን ባሕሪያት) በትክክል የሚያጸድቅ አለ።
«ሯፊዷ» ተብለው የተጠሩበት ምክንያት ዘይድ ቢን ዐሊይ ኢብኑል፡ሑሰይን ቢን ዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብን ስለ አቡ በክር እና ዑመር ሲጠይቁት “አላህ ይዘንላቸው” በማለቱ «ረፍድ» ስላደረጉ (ባለመቀበል ስለመለሱ) እና ራሳቸውን ከርሱ ስላራቁ ነው።
ራሳቸውን «ሺዐህ» ብለው ሰይመዋል። የ”ኣሉ በይት” (የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤተሰቦች) “ተሸዩዑን” (ግብረ አበር) ነን በማለት የሚሞግቱ ሲሆን እንደሚረዷቸውና በ”ኢማማነት” (በመሪነት) ላይም ሐቃቸውንም እንደሚያስጠብቁላቸው ይሞግታሉ።