የደም ጅረት
ጥንታዊቷ ሐለብ (አሌፖ) ከተማ ደም እየጎረፈባት ነው፡፡ የበሻር- ራሺያ-ኢራን-ሒዝበላህ አራጅ ግበረ ሃይል አዛውንት ከህፃናት ሳይመርጥ የጭካኔ ለከቱ እስከየት እንደሆነ ለአለም እያሳየ ነው፡፡ ሃገሪቱ በቀላል ጊዜ በማይጠገን መልኩ በከባዱ ፈራርሳለች፡፡ ህዝቧ እርስ በርሱ የሚባላ በርካታ አንጃ ተፈልፍሎበታል፡፡ ከምንም በላይ ደግሞ በሃገሪቱ አመፁ ከተቀጣጠለ ጊዜ ጀምሮ የረገፈው የሰው ህይወት ስድስት መቶ ሺህ ካለፈ የሰነባበተ መሆኑ ነው፡፡
ተወደደም ተጠላም በሶሪያ ለደረሰውም ይሁን ለሚደርሰው የኢኽዋን አመራሮች እጅ አለበት፡፡ በእርግጥ በሻረል አሳድ ከጭካኔውም፣ ከአረመኔያዊ ድርጊቱም ባለፈ የአፈንጋጩ ኑሶይሪያ (ዐለዊያ) ቡድን ተከታይ ነው፡፡ ሆኖም ግን፡- እነ ቀርዷዊ፣ እነ ዐሪፊ፣… ሰውየውን ትላንት ጥመቱም ጭካኔውም ላይ ሳለ ሲያወድሱት፣ ሲያሞካሹት ነበር፡፡ ኢራንንም እንዲሁ ከነ ጥመቷ ከነ ጭካኔዋ ሲያወድሷት ሲያንቆለጳጵሷት ነበር፡፡ የሊባኖሱ መዥገር ሺዐው “ሒዝበላህንም” እንዲሁ ሌላው ቀርቶ በኛም ሃገር ጭምር ሲያስተዋውቁት ኖረዋል፡፡ ከፊሎቹማ ሽብርን በመዋጋት ስም የገባችዋን ራሻን ሳይቀር “አበጀሽ” እያሉ እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ጭምር ሲያወድሷት ነበር፡፡ ቀርዷዊ የሚመራው “የአለም ዑለማዎች ማህበር” ተብየው የበሽተኞች ስብስብም ከምክትሎቹ አንዱ ሺዐ መሆኑ ይሰመርበት፡፡
ሰዎቹ የአሳድን አገዛዝ ሳያውቁት ቀርተው እንዳይመስላችሁ፡፡ በሰማንያዎቹ በቀሰቀሱት አመፅ ከ20 ሺ በላይ ህዝብ እንደጨረሰ የሚታወቅ ነው፡፡ ጥመቱም ጭካኔውም አዲስ አይደለም፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ምስኪኑን የሶሪያ ህዝብ ባዶ እጁን እስከ አፍንጫው ከታጠቀ ሰራዊት ጋር አጋፈጡት፡፡ እነዚህ የሚንበር አርበኞች፣ የወረቀት ላይ ነብሮች፣ የዲሽ አንበሶች እሳት የሚያቀጣጥሉ ንግግሮችን ካደረጉ በኋላ ከፊሉ ወደ ቱርክ ከፊሉ ወደ ለንደን ሄደው በሚያማልል መስክ ላይ ሲምነሸነሹ ነበር፡፡ የሶሪያን ህዝብ ግን እሳት በላው፡፡ የሶርያን ህፃናት ግን ጭራቅ ፈጃቸው፡፡ የሶሪያ ደካማ ሴቶች ግን የአውሬ ሲሳይ ሆኑ፡፡ የሶሪያ አዛውንቶች ግን ሽበትን በማያከብር ጎረምሳ ብርቱ ክንድ ተደቆሱ፡፡ ይበልጥ የሚያስጨንቀው ግን መከራው ገና ያላባራ መሆኑ ነው፡፡
ዛሬ የኢኽዋን አመራሮች ከሞቀ ቤታቸው ሆነው ምናልባት ካዘኑ ከንፈር እየመጠጡ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈ ግን አቅምን ባላገናዘበ ፊትና ቀስቃሽ ስብከታቸው ስለደረሰው ከመቆጨት ይልቅ አሁንም ድረስ ትልቁ ስራቸው ጣታቸውን የሚቀስሩበት ማመካኛ መፈለግ ነው፡፡ በየሄዱበት መታወቂያቸው ይሄው ነው፡፡ እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ተማሪዎች ሶላት ሲከለከሉ የዱላ ጂሃድ ከመስጂድ ሲያውጁ የነበሩ ቂላቂል “ዱዓቶችን” አስታውሳለሁ፡፡ አላህ ድክመቱን አይቶ ምሮት እንጂ በተደጋጋሚ ጊዜ ህዝባችንን ከእሳት ውስጥ ማግደውታል፡፡ ማሰቢያቸው በቡድናዊ አስተሳሰብ ፍፁም የተደፈነ ነው፡፡
ይሄው ዛሬ ሶሪያ ጣእረ ሞት ላይ ናት፡፡ ይሄው ዛሬ መላው አለም ቅስሙ ተሰብሯል፡፡ እነ እንቶኔ ከዚህ ይማራሉ ብሎ የሚገምት ካለ ግን የዋህ መሆን አለበት፡፡ ሰዎቹ ከቁርኣን ከሐዲሥ፣ ከኢስላማዊ ታሪክ አይማሩም፡፡ ሰዎቹ ከሚያዩት፣ ከሚደርሰው ከተሞክሮም አይማሩም፡፡
በነገራችን ላይ የእሳት ዶፍ የሚዘንብባት፣ የደም ጎርፍ የሚጎርፍባት፣ ህይወት እንደ ቅጥል የሚረግፍባት ሐለብ ከቱርክ ድንበር የአንድ ሰዓት ተኩል መንገድ ያክል እንኳን አትርቅም፡፡ አይንና አፍንጫ!! ማዶ ለማዶ፡፡ ይህን የምጠቅሰው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ቡድናዊ ስሌትን መሰረት የሚያደርገው የኢኽዋኖች ወቀሳም ይሁን ሙገሳም ስለታወሰኝ ነው፡፡ ባቀጣጠሉት ፊትና ሳቢያ ስለሚደርሰው መከራ ሲወቀሱ ሁሌ ጣታቸውን የሚቀስሩት ወደ ሳዑዲ ነው፡፡ ይህን የምለው የሳዑዲ ጉዳይ አሳስቦኝ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሳዑዲን ለማብጠልጠል ግፋ ሲልም ለማክፈር ሳይቀር የሚያነሷቸው ሂሶች ለቱርክ መንግስት ሲሆን ጆሮ ዳባ ማለታቸው ቢደንቀኝ ነው፡፡ ሳዑዲና ሶሪያ ጎረቤት አይደሉም፡፡ ቱርክና ሶሪያ ግን ጎረቤት ከመሆናቸውም በላይ በተለይም ከሰሞኑን እልቂት የሚፈፀምባት ሐለብ ከቱርክ ድንበር ያላት ርቀት 60 ኪሎ ሜትር የማይሞላ መሆኑ ነው፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ግን ቱርክ ከሽምግልና እና ድርድር ባለፈ በበሻር ሰራዊት ላይ የሃይል እርምጃ በመውሰድ #እልቂቱን_ለማስቆም አልሞከረችም፡፡ ይስተዋል ሰብአዊ እርዳታዋን አልዘነጋሁም። እንዲያውም ይህን የማነሳው ቱርክን ለመሀየስ አይደለም፡፡ ውስብስብ በሆነው የአለም ፖለቲካ ውስጥ ገብቼ ጥራዝ ነጠቅ ድምዳሜ መስራት አልልግም፡፡ ነገር ግን ለቱርክ ሲሆን ማለፊያ ምክንያቶችን የሚደረድሩ ኢኽዋኖች ለምን ለሌላው ሲሆን ማስተዋል እንደሚያጥራቸው ሳይ ይደንቀኛል፡፡
“በዚህ ሰዓት ለምን እንዲህ አይነት ነገር ታነሳለህ?” አይነት ተቃውሞ የሚያነሱ ሰዎችም አሉ፡፡ በዚህ ሰዓት ካልተነሳ በየትኛው ሰዓት ይነሳ?! ሰዎቹ እኮ አሁንም አልተማሩም። ሠዎቹ እኮ አሁንም የደረሰውን አቅልለው እያዩ ነው። የጥፋታቸው ውጤት ጣራ በደረሰበት ሰዓት ጉዳቸው ካልተነሳ መቼ ይነሳ?! ከወገናቸው ሰቆቃ ይልቅ ፖለቲካዊ ትርፍን የሚያስቀድሙ አካላት ቁማር ለምን ይሸውደናል?! ከትላንት ወዲያ ጋዳፊን ሲሰቃቅሉ ቆዩ፡፡ ትላንት “ግደሉት” “ስቀሉት” እያሉ ቀሰቀሱ፡፡ ዛሬ ደግሞ “ነጮች ለምን ጋዳፊን እንደጣሉት ታውቃላችሁ?” እያሉ የጋዳፊን ገድል እየዘረዘሩ ወይም ለሚዘረዝሩ ሰዎች እያራገቡ የጅል ሂሳብ ይሰሩብናል፡፡ ከቃላት ክሸና እና ለፊትና ከመቀስቀስ ያለፈ ችሎታ የማይታይበት አስገራሚ ጭንቅላት!! አላህ “ኢኽዋነል ሙስሊሚን” ከሚባል ነቀርሳ ሙስሊሙን ይገላግለው፡፡
ይህን ሊንክ ይክፈቱና ይታዘቡ፡፡ https://youtu.be/boVv49Cv1lo
ከስር ያሉ ምስሎችንም ይመልከቱ፡፡