🔘እኛና ቁርኣን አሁንና ድሮ- 1 📝የዕለተ ጁሙዓ የቁርኣን
ማስታወሻ
ማስታወሻ
⭐ቁርኣን የሙእሚኖች የልብ ስንቅ፣ የመንገድ ብርሃን፣ የህይወት መመሪያና ከጥመት መጠበቂያ ነው!
💥የቂያማ ቀንም የሰው ልጆች ላይ መስካሪ ነው ዱኒያ ላይ ላነበቡትና ልባቸውን በርሱ ፈትሸው ለትእዛዛቱ ላደሩ ሲመሰክር ችላ ብለውትና ጀርባቸውን ሰጥተውት ስሜታቸንና ሰው ሰራሽ ህጎችን ያስቀደሙበት ሰዎች ላይ ምስክርነቱ የማይመለስ መስካሪ ነው!
🔹ቀደምት አማኞች ቁርኣንን ከምግብና ከመጠጥ ያስቀድሙና ያስበልጡ የነበረ ሲሆን፣ ከጊዜ በኋላ የመጡ ደካማ አማኞች ግን ቁርኣንን ትርፍ ሰዓት ካገኙ እንጂ ማንበቡም ይሁን ማድመጡ ትዝ የማይላቸው
ብዙ ናቸው።እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የቁርኣንን ጣእም የቀመሱ ወጣቶች መስጂድና ስራ ቦታ ላይ እንዲሁም መኪና ውስጥ እየተጓዙ ቁጭ ብለው አንገታቸውን ደፍተው ከመቅራትም በተጨማሪ የቁርእን ካሴት እየገዙ አቅማቸው ያልቻለ ወይም ያላገኙ ደግሞ እያስቀዱ በቴፕ ሲያደምጡ አንዳንዶችም ኪሳቸው ውስጥ ትንንሽ የካሴት ማጫወቻዎችን ( ዎክማን) አድርገው ሲያደምጡ እናይና እንሰማ ነበር! ዛሬ ግን ይህ የሚያስቀናና የሚያኮራ ተግባር አብዛኞቹ ዘንድ ጠፍቷል!
🔹የሙእሚን መለያና ውበት በሆነው ቁርኣን ፋንታ ሞባይልና ኮምፒውተር፣ በማንበቡና በማድመጡ ፋንታም ፌስቡክ፣ዋትሳፕና ዩትዩብ ተተክተዋል።የብዙዎች ቁርኣን ላይም ሸረሪት ሳታደራና አቧራዎች ሳይወሩ አይቀሩም!
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን❗
↪ጥቂቶች የቀሩ ወይም የሞከሩም እንደሆነ ለውስን ደቂቃዎች ብቻ ሲሆን ልብና ዓይናቸውም ከላይ ከተጠቀሱ ጫዎታዎች ጋር ሆኖ ነው! አዲስ ሚሴጅ በመጣና በተደወለ ቁጥርም ደግሞ ከእጃቸው እየጣሉት ለሆነ ላልሆነው ኀያልና አዛኝ የሆነውን ኻሊቁን አላህን እየተው ደካማና ጨካኝ ወደ ሆነው መኽሉቁ ይዞራሉ!
🔸የቁርኣን ሚስጥር የገባቸውና ጣእሙን የቀመሱ የአላህ ወዳጆች ግን እንዲህ አልነበሩም!
📝ኢማሙ አሕመድ ሙስነዳቸው ላይ ባሰፈሩት ሰሂህ ዘገባ መሰረት፡
💥ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንዴ ከጂሃድ እየተመለሱ በምሽት መንገድ ላይ ማረፍ ፈልገው አንድ ሸለቋማ አካባቢ ላይ ሰፈሩ፣ መላው ሰራዊት እንዲተኛና እንዲያርፍ ፈልገውም:—
[" እኛ ልንተኛ ነው ማነው የሸለቆውን መግቢያ በመጠበቅ ከድንገተኛ የጠላቶቻችን ወረራ ሊጠብቀን ፈቃደኛ የሚሆነው ?"]
ሲሉ ሁለት ሰሓባዎች ይህን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት ተስማምተው ስራ ጀመሩ ከዛም አንዱ ለሌላኛው
("እኔ የሌሊቱን ግማሽ ልጠብቅ፣ አንተ ደግሞ ግማሹን ትጠብቃለህ ተራ በተራ እንተኛ") ተባባሉ በዚህም መሰረት አንደኛው ተኛ ሌላኛው እየጠበቀ ለይል ሰላት መስገድ ጀመረ! እየሰገደ ሳለ ቀን ላይ በተደረገው ጂሃድ ባለቤቱ የቆሰለችና ድንገት ከጉዞ ሲመለስ በዚህ ቆስላ ያገኛት ባሏ(" ከነሱ መሀል አንድን ሰው ሳላቆስልና ደምም ሳላፈስ አልመለስም" )ብሎ ዝቶ ከቤቱ የወጣው አይሁዲ ከነቢዩና ባልደረቦቻቸው ማረፊያ መግቢያ ላይ ሲደርስ እየሰገደና ጌታውን እያናገረ (ቁርኣን እየቀራ) የአላህን ባሮችን የሚጠብቀውን ሰሃቢይ ከቅርብ ርቀት ተመለከተው
በያዘው ቀስትም ወርውሮ ወጋው ሰሓቢዩም ቀስ አድርጎ አውጥቶት ሰላቱን
ቀጠለ፣ለሁለተኛ ጊዜም ደግሞ ወረወረ አሁንም ወጋው እንደመጀመሪያው ቀስ አድርጎ አውጥቶ ጥሎት ሰላቱ ላይ
ቀጠለ! በቀስት ሰውነቱን ቀጥታ እየተወጋ የማይወድቀውና የማይጮኸው ግለ-ሰብ ሁኔታም እየገረመው ለሶስተኛ ጊዜ ወርውሮ ወጋው፣ ይህንም ቀስ አድርጎ አውጥቶ ጥሎት ሩኩዕ ከዛም ሱጁድ አድርጎ ከአጠገቡ የተኛውን አብሮት የሚጠብቀውን ሰሓቢይ ቀሰቀሰው እንቅስቃሴያቸውን ሲመለከትም አይሁዲው ቦታውን ጥሎ ጠፋ
☞ሌላኛው ሰሓቢይ ልክ ሲባንን ዙሪያው በደም ተሞልቶ ሲመለከት ምን እንደገጠመው ጠየቀው የሆነውን በነገረው ጊዜም {"ታድያ ምነው ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደወጋህ አልቀሰቀስከኝም"?}
ሲልም ጠየቀው ይህ ልቡ በጌታው ቃል ( በቁርኣን ) ፍቅር የተሞላና ጥፍጥናውም ሁሉን ነገር ያስረሳው ውድ ሰሓቢይ {{ "አንዲትን ሱራ ጀምሬ ነበር ሳልጨርሳት ማቆም አልፈለግኩም፣ ነቢዩ እርሳቸውንና ምዕምናንን የመጠበቁን ኃላፊነት ጥለውብኝ ባይሆን ኖሮ ነፍሴ እስካልወጣች ድረስ የሆነው ቢሆን ቁርኣኔን መቅራት አላቋርጥም ነበር"}}
ብሎ መለሰለት!!!
🕹ሐዲሱ ሰሒሕ ባይሆን አይደለም ማመን መናገርም ይከብድ ነበር❗
☞ይህ ሰሓቢይ እኛን ቢመለከት ምን ይል ነበር?! )
✍ኡስታዝ አሕመድ ኣደም
ጁሙዓ 17/3/1438 ዓ.ሂ