Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የቁኑት ዱዓ ምን ማለት ነው? 🔹መቼስ ነው የሚደረገው?

🌴የቁኑት ዱዓ ምን ማለት ነው?
🔹መቼስ ነው የሚደረገው?
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተወሰኑ ሰሓቦቻቸው በከሃዲያን እጅ በግፍ ተገድለውና ሙስሊሞች ላይም በደል ደርሶ ለአንድ ወር ገደማ ሰላት ላይ ከመጨረሻው ሩኩዕ በኋላ ዱዓ አድርገዋል ከዛም አቁመዋል' በዚህ ነቢያዊ ተግባር መሰረትም በየትኛውም ዘመንና ቦታ ላይ በሙስሊሞች ላይ ግፍና በደል ከደረሰ ☞የሱብሒ ሰላት ላይም ይሁን ☞ሌሎች ሰላቶች ላይ ከመጨረሻው ሩኩዕ በኋላ ኢማሙ ዱዓ (ቁኑት) እያደረገ ሰጋጆች ከኋላው አሚን ማለት ይችላሉ፣ እጅ ማንሳትና ዱዓውን ጠበቅ ማድረግና አላህን ችክ ብሎ መለመንም ይወደዳል
🍃በመሰረቱ አንድን ግለ-ሰብ በስሙ ነጥሎ መርገም የተወገዘ ቢሆንም በእንዲህ አይነቱ ዱዓ ላይ ግን ግፈኛ የሆነን ሰው ስሙን እያነሱ አላህ እንዲያጠፋውና፣ እንዲረግመው ጌታን መለመን ይፈቀዳል' ሆኖም ይህ አይነቱ ዱዓ (ቁኑት) የተፈቀደው ለተገደበ ዓለማና ሁኔታ ከመሆኑ አንፃር ግፈኞች እንዲጠፉ፣ ተበዳዮችም እንዲረዱና ሐቃቸውን እንዲያገኙ ብቻ ነው ዱዓ መደረግ ያለበት !
መስፋትና ወደ ሌላ ጉዳይ መግባት አይኖርበትም!
➡️ በተለያዩ ምክንያቶች ፈርድ ሰላቶችን ለብቻው የሚሰግድ ሰውና ሴቶች እንዲህ ዓይነቱን ዱዓ (ወቅታዊ ቁኑትን) በግላቸው ዊትር እየሰገዱ ነው ማድረግ የሚችሉት
🔸በችግር ጊዜም ይሁን በሌላ ወቅት ከሰላት በኋላ በጀመዓ ተሰብስቦ ዱዓ ማድረግ ከነቢዩም ይሁን ከሰሓባዎች አልተለመደምና ማድረግ አይቻልም'
ከጥንት ጀምሮ በተለያዩ ጊዜዎች ዓለም ላይ ያለው ሙስሊሙ ኡማ ላይ ግፍና በደል እየደረስ ይገኛል ይህን ግፍ ከምንጋፈጥባቸው መንገዶች መሀል አንዱ ዱዓ ነውና ቁኑት ይደረግ ብሎ የሙስሊሙ መሪዎች ባዘዙበትና በፈቀዱበት ወቅት ልዩ ቁኑት በማድረግ ይህ በሌለባቸው ወቅቶች ደግሞ ሁሉም በየግሉ በሱጁድና በዊትሩ ቁኑት ላይ አላህን መማጸን ይጠበቅበታል!
💥ሰማይም ላይ ይሁን ምድር ላይ ምንም የማይሳንህ ኅያሉ አላህ ሆይ መላው ዓለም ላይ በዲናቸው ምክንያት እየተበደሉና እየተሰቃዩ ያሉ ባሪያዎችህን ከጭንቃቸው ገላግላቸው! ጠላቶቻቸውንም ለሌሎች ግፈኞች መማሪያ የሚሆንን ማጥፋት አጥፋቸው የሙስሊሞችንም ልብ ወዳንተ መልሰው መመኪያችንና አለኝታችን አንተ ብቻ ነህና! የጠላት መጫወቻ አታድርገን አላዋቂዎች ባጠፉትም ሁላችንንም አትቅጣን!
➡️ሶሪያ ላይ ያለው ግፈኛ መንግስትና ተባባሪዎች ላይም ቁጣህን አዝንብ! ለህጻናት፣ ለአረጋዊያን፣ ለህሙማንና ለሴቶች እዝነትህን አውርድ ያረብ!
የአላህ ባሮች ሆይ ሶሪያ ላይ ጭንቅና ስቃይ ውስጥ ያሉ ወገኖቻችሁን በዱዓ እርዷቸው!
✍ኡስታዝ አህመድ ኣደም
18/3/1438 ዓ.ሂ