Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለተወሰኑ የጥመት ቡድኖች መጠን ያለ እይታ (ክፍል 3 «አልኸዋሪጅ» እና «አልቀደሪይ-ያህ»)

ስለተወሰኑ የጥመት ቡድኖች መጠን ያለ እይታ
(ክፍል 3 «አልኸዋሪጅ» እና «አልቀደሪይ-ያህ»)

ጸሐፊ፡ አልኢማም ሙሐመድ ቢን አልዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸው)
ምንጭ፡ የኢብን ቁዳማህ “ሉምዐቱል-ኢዕቲቃድ” ማብራሪያቸው ላይ
(ገጽ 162)

3. «አልኸዋሪጅ»

እነርሱ ዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁን በአመራሩ አማኻኝነት ለመጋደል የወጡ ናቸው። አካሄዳቸውም ራሳቸውን ከዑሥማን እና ከዐሊይ ረዲየላሁ ዐንሁ ማራቅ፤ ሱንናህን የተቃረነ ኢማም (መሪ) ላይ አምጾ መውጣት እና ትላልቅ ወንጀሎችን የሰራ ሰውን ማክፈር ብሎም ይህ ግለሰብ (ትልቅ ወንጀል የፈጸመውን) በእሳት ውስጥ ዘውታሪ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው። በብዙ ይከፋፈላሉ።

4. አልቀደሪይ-ያህ»

እነርሱ በባሪያ ድርጊት ላይ አልቀደር (የአላህን ውሳኔን) የማይቀበሉ ሲሆኑ የርሱ ፍላጎት (ኢራዳህ) እና ችሎታ (ቁድራህ) ከአላህ (ኢራዳህ) እና ችሎታ (ቁድራህ) የተነጣጠለ ነው ይላሉ። ይህንን አስተሳሰብ ለመጀመሪያ ግዜ ግልጽ ያወጣው ሙዕበድ አልጁህኒይ የተባለ ግለሰብ ነው። ግዜውም የሶሓቦች የመጨረሻ ዘመን አካባቢ ሲሆን (አስተሳሰቡን) የተማረውም በበስራ ይኖር ከነበረው አንድ “መጁሲ’’ (እሳት አምላኪ) ግለሰብ ነው።

አንጃው በሁለት የሚከፈል ሲሆን “ጙላት” (ወሰን አላፊዎች) እና “ጘይረ ጙላት” (ወሰን የማያልፉ) ናቸው። ወሰን አላፊዎቹ የአላህ እውቀት፥ መሻት፥ ችሎታ እና በባሪያው ላይ አላህ ድርጊትን ፈጣሪ መሆኑን ይክዳሉ። እነኚህኞቹ ዛሬ ላይ ጠፍተዋል አልያም ከሌላው ጋር ተቀራርበዋል። ወሰን የማያልፉት ደግሞ አላህን አዋቂ መሆኑን እና በባሪያም ተግባር ያምናሉ። ሆኖም ይህ (የባሪያው ተግባር) በአላህ ፍላጎት፥ ችሎታ እና ፍጥረት መሆኑን ግን ያስተብብላሉ። በዚህ ላይ ነው እምነታቸው የተገነባው።