Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለዚህ ነው ያሳደኩክ እንዴት ዓይነት እናት ናት

ለዚህ ነው ያሳደኩክ
እንዴት ዓይነት እናት ናት
ሸኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ለዲንና ለዳዕዋ ጉዳይ ወደ ግብፅ ሄዶ ከእናቱ በራቀ ጊዜ የራቀበትን ምክንያት የሚያስረዳበትን ደብዳቤ ወደ እናቱ ይልካል። የልጇ ደብዳቤ የደረሳት ይህች ምርጥ እናት እንዲህ ስትል መልስ ፃፈችለት:—
ውዱ ልጄ አህመድ ኢብኑ ተይሚያህ ሆይ ወአለይከሰላም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ ወመግፊረቱሁ ወሪድዋኑሁ
እኔኮ አሁን አንተ ላለህበት ጉዳይ ነው ተንከባክቤ ያሳደኩክ እስልምናንና ሙስሊሞችን እንድታገለግል ነው የተሳልኩት የእስልምናን ህግጋቶችን ያስተማርኩክ ። ልጄ ሆይ! ለዲንህ ቅርብ ከመሆንና ዲንህን እንዲሁም በተለያዩ ሀገር ያሉ ሙስሊሞችን ከማገልገል ይልቅ ወደኔ እንድትቀርብ የምፈልግ አድርገህ እንዳትጠረጥረኝ ።
ልጄ ሆይ! እኔ ላንተ ያለኝ ውዴታ የሚለካው ለእስልምናክና ለሙስሊሞች በምታደርገው አገልግሎት ልክ እንጂ በሌላ አይደለም።
ልጄ ሆይ! እኔ ነገ አላህ ፊት ከኔ በመራቅክ ምክንያት አልጠይቅህም (አልከስህም) ምክንያቱም እኔ አንተ የትና በምን ላይ እንዳለህ አውቃለውና ። ነገር ግን አህመድ ሆይ አንተን ነገ አላህ ፊት የምጠይቅህና የምተሳሰብክ የአላህ ዲንን አንዲሁም ይህንን ዲን የሚከተሉትን ሙስሊም ወንድሞችህን ከማገልገል ያጓደልክ ጊዜ ነው።
አላህ ስራህን ይውደድልህ መንገድህንም በመልካም ነገር የብራልህ እርምጃህንም ያስተካክልልህ በዚያ ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር እኔንም አንተንም ይሰብስበን!
ወሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
📚ምንጭ
መጅሙዑል ፈታዋ (28/48)
አላህ እንደዚህ ዓይነት እናቶችን ያብዛልን ምክንያቱም የመጀመሪያ መድረሳ እናት ናትና ። ለዲናቸው የሚጨነቁ እናቶች በበዙ ቁጥር ለዲናቸው የሚጨነቁ ልጆች ይበዛሉ እነዚህ እናቶች ጭንቀታቸው ዱንያ ከሆነ ግን .......
አላህ ይጠብቀን
የልጆቻችን ተርቢያ አደራ
መንቁል