Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፍሬያማ ስራዎች

🌴 ፍሬያማ ስራዎች
" ሙስሊሞችን በመጥቀም ላይ መንቀሳቀስ "
📍 قال تعالى : (لَا خَيْرَ فِي كَثِيرٍ مِنْ نَجْوَاهُمْ إِلَّا مَنْ أَمَرَ بِصَدَقَةٍ أَوْ مَعْرُوفٍ أَوْ إِصْلَاحٍ بَيْنَ النَّاسِ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ ابْتِغَاءَ مَرْضَاتِ اللَّهِ فَسَوْفَ نُؤْتِيهِ أَجْرًا عَظِيمًا). [سورة النساء : ١١٤ ].
አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ በተከበረው ቁርአን እንዲህ ይላል ~
"ከውይይታቸው በምጽዋት ወይም በበጎ ሥራ ወይም በሰዎች መካከል በማስታረቅ ከሚያዙ ሰዎች ውይይት በስተቀር በብዙው ውስጥ ደግ ነገር የለበትም፡፡ ይኸንንም (የተባለውን) የአላህን ውዴታ ለመፈለግ የሚሠራ ሰው ታላቅ ምንዳን እንሰጠዋለን፡፡" [ሱረቱ አን–ኒሳእ 114]
📍عَنْ جَابِرِ بنْ عَبْدُ اللهِ عنِ النَّبيّ صلّى اللهُ عَليْهِ وَسَلّمَ أنّهُ قالَ:
( خيرُ الناسَ أنفعُهُمْ لِلناس ).
📝 رواه الطبراني وحسنه الالباني.
📍 ከጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ – አላህ ይውደድለትና–ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም " ከሰዎች በላጩ ሰውን የሚጠቅም ነው" ብለዋል።
📝 ጦበራኒ ዘግበውታል… አልባኒ ደህና ዘገባ ነው ብለውታል።
📍وعن أبي هريرة رضي الله عنه قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( من نفس عن مؤمن كربة من كرب الدنيا ، نفس الله عنه كربة من كرب يوم القيامة ، ومن يسّر على معسر ، يسّر الله عليه في الدنيا والآخرة ، ومن ستر مؤمنا ستره الله في الدنيا والآخرة ، والله في عون العبد ما كان العبد في عون أخيه...... الحديث ) .
📝 رواه مسلم .
📍 ከአቡ ሁረይራ –አላህ ስራውን ይውደድለትና– እንደተዘገበው፦ ነቢዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም " ከአማኝ የዱንያ ጭንቀትን የገላገለ አላህ ከትንሳኤው ቀን ጭንቅ ይገላግለዋል። ከተቸገረን ሰው ችግሩ ያቀለለ አላህ ዱንያውን እና አኺራውን ያቀልለታል። አማኝን የሸፈነ (ከክፉ ነገር) አላህ በዱንያም በአኺራም ይሸፍነዋል። አላህ ባሪያውን በመርዳት ላይ ይገኛል አንድ ባሪያ ወንድሙን በመርዳት ላይ እስካለ ድረስ…" ብለዋል።
📝 ሙስሊም ዘግበውታል።
📍 قال النووي رحمه الله:
"في هذا فضل إعانة المسلم وتفريج الكرب عنه وستر زَلاَّته، ويدخل في كشف الكربة وتفريجها مَنْ أزالها بماله أو جاهه أو مساعدته، والظاهر أنه يدخل فيه مَنْ أزالها بإشارته ورأيه ودلالته".
📝 شرح صحيح مسلم [١٦ / ١٣٥ ].‍
📍 ኢማም አን–ነወዊ አላህ ይዘንላቸውና ሀዲሱን ሲያብራሩን ~
" ይህ ሐዲስ ሙስሊሞችን መርዳት፣ ከችግራቸው እንዲላቀቁ ማገዝ፣ ስህተቶቻቸውን ማለፍ ያለውን ደረጃ ሲያመላክት ይህም በገንዘቡ፣ በስልጣኑ ወይም በእገዛው ሊሆን ይችላል። እንደውም በጥቆማው፣ በአስተያየቱ እና በአመለካከቱም በዋናነት ይገባል።
📝 ሸርሕ ሶሒሕ ሙስሊም [16/135]
© ተንቢሀት