Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሺዓዎች አምላክ ማን ነው?



















የሺዓዎች አምላክ ማን ነው?
አንብበው ሲጨርሱ SHARE ማድረግ አይርሱ!
በርግጥ ይህን ሺዓዎች ይላሉ ብሎ ለማመን ሊከብድዎት ይችላል ግን ምንም ማድረግ አይቻልም! ሺዓዎች እንዲህ ናቸው፤ ለዚህም ነው ከነርሱ የምናስጠነቅቀው ...
ሺዓዎች ዘንድ እንደታላቅ ዓሊም የሚታየው ኒዕመቱላህ አል-ጀዛኢሪ፣ አል-አንዋሩ አ'ኒዕማኒያህ በተሰ�ኘው ኪታቡ ላይ እንዲህ ይላል ...
==> "በጥቅሉ እኛ (ሺዓዎች ከአህሉሱናዎች ጋር) በአምላክ በነቢይም ይሁን በኢማም ስር አንሰባሰብም። እነርሱ አምላካችን የሚሉት እኮ (የላከው ነቢይ) ከርሱ በኋላ ኸሊፋው አቡበክር የሆነው ሙሐመድ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ነው፤ እኛ ደግሞ ይህንን ጌታችን ያንንም ነቢያችን አንልም። እንደውም እኛ የምንለው የነቢዩ ኸሊፋ አቡበከር የሆነ ጌታ ጌታችን አይደለም ነቢዩም ነቢያችን አይደለም ነው!" አል-አንዋሩ 'ኒዕማኒያህ ቅፅ 3 ገፅ 278 [የዓረብኛውን ኪታብ ገፅ በምስሉ ላይ ያገኙታል]
እስቲ ደግሞ የዘመናችን የሺዓዎች ኢማምና መሪ እንዲሁም የአዲሲቷ ኢራን መስራች አል-ኹመይኒ 'ከሽፉል አስራር' በተሰኘው ኪታቡ ላይ ምን እንደሚል ይመልከቱ ...
==> "እኛ የምንገዛው አምላክ ስራዎቹ በአእምሮ መሰረት ላይ የተመረኮዙ የሆነ ነው። ለአዕምሮ የሚቃረን ስራን አይሰራም፤ የአምልኮ፣ የፍትህ፣ የሀይማኖተኝነትን ግዙፍ ግንብ ገንብቶ በእጁ የሚያፈርስ(አይደለም)። መሪነትን ለየዚድ፣ ሙዓዊያ፣ ዑስማን እና መሰሎቻቸው የሚሰጥ አይደለም" የኹመይኒ ንግግር አበቃ
ታዲያ አላህ ይህን ሁሉ ማድረጉን እያወቁ 'ይህን የሚያደርግ ጌታ የለንም' ካሉ የሺዓዎች ጌታ ማን ሊሆን ነው?
በእርግጥም ሺዓዎች በውስጣቸው የሚደብቁትና በመዛግብቶቻቸው የሚያስቀምጡት እምነት በሌላ በኩል ለአህሉሱናዎች በማስመሰል የሚገልፁት እምነት እጅጉን የተለያየ ነው። ይህን ለምን እንደሚያደርጉ እና ይህ ተግባራቸው(ቱቅያ) ምን እንደሆነ ወደ ፊት በአላህ ፈቃድ እንዳስሰዋለን።
©ለአላህ ከዚያም ለታሪክ