Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ባልተገራው አንጓጣጭ አንደበቱ የተፈለፈሉ ትንንሽ ደፋር ሙፍቲዎች!!

Muhammedsiraj MNur Gidey

بسم الله الحمد لله وحده والصلاة والسلام على من لا نبي بعده:
በቀጥታ ወደ ቁም ነገሬ ልግባ
ከጥቂት ወራት በፊት "ቢድዓ ምንድን ነው ፣ ከ ኢስላም ያስወወጣልን? " እያሉ ሲጠይቁን የነበሩ የጀማል ያሲን ሃሳበ—ጥሬ "ጭፍን ተከታዮች" ዛሬ ፌስ ቡክ ላይ በጀምዒያና በሌሎች ጉዳዮች ሙፍቲ ሆነው አየሁና ምንም የማያውቁ ምስኪኖችን በ 3 እና 4 ወራት ውስጥ በሙፍቲነት በሚያስመርቀው የጀማል ያሲን "መድረሳ" ተደነቅኩ ። ባልተገራው አንጓጣጭ አንደበቱ የተፈለፈሉ ትንንሽ ደፋር ሙፍቲዎች!!
እናንተ ሚስኪኖች ሆይ: ምንም እንኳን እናንተ በ ጀምዒያ ምክንያት ብቻ አማኞችን ከሱና ቀለበት ብታስወጡም ይህን በስሜትና በትኩሳት የተሞላ አቋም የሚጋራችሁ አንድም የሱና ዓሊም የለም! የናንተው ብጤ ጭፍን ተከታይ ቢሆን እንጂ! መቸም የሚባለውን አዛብቶ መገንዘብ "ልዩ ምልክታችሁ" ነውና ልድገምላችሁ! የሱና ዓሊም ነው ያልኩት! ሰውያችሁን ናሙና አርጋችሁ እንዳትጠሩብኝ— ያሕያ አል ሓጁሪን! ደሞም የተፃፈውን ተገንዘቡ! የከለከለ ዓሊም የለም እያልኩ አይደለም! ። ማንም ዓሊም ሳይቀድማቸሁ በዚህ እና በመሰል ጉዳዮች ሙስሊሞችን ከሱና ማውጣታችሁ ማንም ያልተጋራችሁ ስር የሰደደ ደዌያቸው ነው እያልኩ ነው !! ይህ አልበቃ ብሏቸሁ ደሞ ከአንድም ጀምዒያ ጋር ላንዲት ደቂቃ እንኳን ግንኙነት ኖሮት የማያውቅን፣ ይቻላልም ብሎም ያልሰበከን ሱኒ "ጀምዒይ" እያላችሁ በዙልም ከሱና ታስወጣላችሁ። ለምን? በጀምዒያ ጉዳይ ብቻ ወንድሞችን ከሱና ማውጣት ተገቢ አይደለም በማለቱ ብቻ!! የበሸቀጠ አቋም ማለት ይሄ ነው!! ዑለሞች የማይጋሩት የሀዳድዮች ሰንካላ እርምጃ!! መስፈርቱን የጠበቀ ጀምዒያን የፈቀደውም ቢሆን ይሄው የዙልም መጠሪያ ሊለጠፍበት እንደማይገባ ከአስተዋይ አማኝ የሚሰወር አይደለም—
በርካታ ዑለሞቻችን መስፈርቶችን በማስቀመጥ ጀምዐያን ፈቅደዋልና ። ልብ በል! እንዲህ አይነት አቋሞች ከጀማል ያሲንም ይሁን ከመሰል ያገር ደካሞች አይወሰዱምና ለምትለው ነገር በትኩሳት የተሞሉ ወጠጤዎችን ሳይሆን የሰከኑ የሱና ዑለሞችን ተከተል!
🔴 ከፈቀዱት ዑለሞቻችን ውስጥ፣
ለምሳሌ ፣ 1⃣ ኢማም አል አልባኒ ፣ እንዲህ ይላሉ፣
أي جمعية تقام على أساس من الإسلام الصحيح المستنبطة أحكامها من كتاب الله ومن سنة رسول الله؛ ومما كان عليه سلفناـالصالح فأي جمعية على هذا الأساس
فلا مجال لإنكارها والتهامها بالحزبية لأن ذلك كله يدخل في عموم قوله تعالى (وتعاونوا على البر والتقوى)
ማንኛውም በትክክለኛው ኢስላም ላይ የተገነባ ፣ ሀግጋቶቹ ከቁርኣን ከአላህ መልክተኛ ሀዲሶች እንዲሁም መልካም ሰለፎቻችን ከነበሩበት የወጡ ( የተቀነጨቡ) ከሆኑ— በዚህ መሰረት ላይ ያለችን "ጀምዒያ"—ለመቃወምም ሆነ በቡድንተኝነት ለመጠርጠር ምንም አይነት ቦታ የለም ። የሄ ሁሉ "በመልካም ነገር እና አላህን በመፍራት ላይ ተባባሩ " የሚለው ( የቁርአን አንቀፅ) ውስጥ የሚገባ ነው።
ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር
2⃣ሸይኽ ሙቅቢል ደሞ ከናንተ ጋር የማይጣጣም አቋማቸውን እንዲህ በማለት አስቀምጠዋል፣

الشيخ مقبل الوادعي
نسمعهم بعد ذلك يقولون: أنتم تطعنون في الجمعيات؛ فمن قال لك إننا نطعن في الجمعيات؟ نعم إننا نطعن في بعض.الجمعيات التي اشتملت عى حزبيات وعلى ولاء ضيق وعلى لصوصية واختلاس الأموال فهذه هي التي نطعن فيها وننفر عنها
تحفة المجيب .. ص 195
🔵 ደሞ ከዚህ በሁዋላ እንዲህ ሲሉ እንሰማቸዋለን ፣ "እናንተ በ‘ጀምዒያ‘ ላይ ታነውራላችሁ" ማን ነው በጀምዒያ ላይ ያነውራሉ ያለህ?! አዎ!ቡድንተኝነትን... ገንዘብ ዝርፊያና ሌብነትን ማዕከል ያረጉ ከፊል (የተወሰኑ) ጀምዒያዎች ላይ እናነውራለን (እንቃወማለን) ። ይቺ ናት የምናነውራትና (ሰዎችንም) ከሷ እንዲሸሹ የምናረገው።
ሌሎችም ኢማሞችን ኢብኑ ባዝ ዑሰይሚን....... በርካቶች ፈቅደዋልና በሉ በተለመደው ገደብ አልባ ትኩሳታችሁ ተነዱና ፍረዱባቸው!!
ሌላው የሚገርመው ደሞ በሚናገሩትና በሚፅፉት ላይ "ቀጣፊ" መሆናቸው ነው! ሁሉም ባይሆኑም ብዙዎቹ ላይ የሚስተዋል በሽታ ነው ። አንድ ናሙና ልጥቀስ— በቅርቡ ፌስ ቡክ ላይ የልጆችን የቁርአን ሒፍዝ ተከትለው የሚደረጉ ድግሶች በድዓ መሆናቸውን አስረግጠው ብይን ካሰፈሩ በሇላ የዑለሞችን ፈትዋዎች ጠቃቀሱ። የዑሰይሚን ፈትዋም ቀረበ ። የቀረበው ግን በቅጥፈት እና በማጭበርበር ነበር ። የቀረበው ፈትዋ ላይ ሸይኹ የሚያወሩት መድረሳዎች ላይ ስለሚደረጉት ድግሶች ሳይሆን ሰዎች ቀርአን ቀርተው ባኸተሙ ግዜ ደግሰው ማብላታቸውን ነው! መድረሳዎች ላይ የሚደረገውንማ ፈቅደዋል ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ጥቅሞቹን በመጠቆም ዝግጅቱን አበረታትተዋል!!! በነገራችን ላይ ሌሎችም ዑለሞች ፈቅደዋል
🔵 የቡድንተኝነት በሽታቸውን ያስተዋለ የሱና ሰው ደግሞ በሁኔታቸው መደመሙ አይቀሬ ነው። ምንም ነገር ቢያጋጥማቸው ለጉዳዩ ብይን የሚጠየቁት ፈውዛንም ፣ዓባድም ፣ ሉሔይዳንም ማንም አይደለም! ያንው ሓጁሪ እንጂ! ሸኻቸው ተሸሁድ ላይ ጣትን ማንቀሳቀስ ዳንስ ነው ብሎ አደብ የጎደለው ብይን ሲሰጥ ባንዲት ጀምበር ጣታቸው ማንቀሳቀስ ያቆማሉ! ኣልባኒና ሌሎችም ትልልቅ ዑለሞች የተደነገገ መሆኑን መግለፃቸው ለሀጁሪ ሙሪዶች ግመት የሚሰጠው አይደለም። የቁኑት ዱዓ ላይ የመዕሙሙ እጅ ማንሳት ክልክል ነው ሲባሉም ባንድ ለላይ ወደዚሁ አቋም ይጎርፋሉ! ደምባራ ተከታዮች!
አሁንም ልብ በሉ! እየተቃወምኩ ያለሁት ቁኑት ላይ እጅ አለማንሳታችሁንም ሆነ ተሸሁድ ላይ ጣታችሁን አለማንቀሳቀሳችሁን ሳይሆን በጭፍን እየተከተላችሁ መደናበራችሁን ነው! እንጂ እኔም አቋሙን ልጋራው እችላለሁ — ያለ "ተዓሱብ" !
ሌላው የተለከፉበት ደዌ፣ በያገሩ ያሉ የነሱ " ዱዓቶች" ተጠሪነታቸው ለሰውያቸው ነው። እነዚህ የሀጁሪ ተጠሪዎች ደግሞ ማን ማስተማር እንዳለበትና እንደሌለበት ይደነግጋ ሉ! ይሾማሉ ይሽራሉ! እኛም አገር ላይ አቡ ፉላን ያልፈቀደለት ያልሾመው ማስተማር አይችልም ይባላል ! ይህን ጉዳይ በተመለከተ በነሱ አንጃ ስመ ገናና ከሆኑት አንዱን ከጥቂት አመታት በፊት በነቀፌታ አንስቸለት"ለዳዕዋ መስለሓ ሲባል ነው " ብሎ ነበር የመለሰልኝ ። አሁን አሁን አንዳንዶቻቸው ከዚህ አቋም ስልታዊ ማፈግፈግ አርገው የደገፋቸውንና ያልነቀፋቸውን ሀሉ ማግበስበስ የጀመሩ ይመስላሉ።
ከጀማል ያሲን እና ከጭፍን ተከታዮቹ የተሻሉ ልጆች በውስጣቸው መኖራቸው የታወቀ ቢሆንም በሰውየውና በመሰሎቹ ዙሪያ መሆናቸው ብቻውን አደጋ ነው — የሚጋሯቸው ስህተቶች ከመኖራቸው ጋራ ።

በሸሪዓ ድንጋጌዎች ላይ ጤናማ አረዳድን ተነፍገው ቸልተኞችና እንቅልፋኞች የሆኑትን ኢኽዋኖች ተመልክቶ የነዚህንም ፅንፈኝነት ያስተወለ አማኝ ሰለፊያ በሁለቱም ጠርዘኞች መካከል መሆኑ ወለል ብሎ ይታየዋል።
በተጠየቁ ፣በተናገሩና በፃፉ ቁጥር "ችግር የለበትም፣ ይቻላል " በማለት ደንዝዘው ማህበረ ሰብን በማደንዘዝ ላይ ያሉትን ኢኽዋኖች ተመልክቶ በተቃራኒው ሁሌ "ቢድዓ " ሓራም " "ሙብተዲዕ" ማለት የሚቀናቸውን እነዚህን የጀማል ያሲንን ፅንፈኞች ያስተዋለ የሰለፊያ መንሃጅ በሁለቱ ጠርዘኞች መሃል እንደሆነነ ይገነዘባል።

ምንም እንኳን የነዚህ "ልጆች " እንቅስቃሴ ቀድሞውንም የታወቀ ቢሆንም ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የወፈፌ አካሄዳቸው በእጅጉ ፈሩን እየለቀቀ በመምጣቱ የተለከፉበት ደዌ ቀላል እንዳልሆነ ያሳያልና በጅጉ ልንጠነቀቃቸው ይገባል!!!