ተውሒድ፣ ትኩረት የተነፈገው ሐቅ
ህዝባችን ከተውሒድ ያለውን ርቀት ያስተዋለ ሰው አብዛሀኛው ዱዓት የሚያተኩረው ሌሎች ርእሶች ላይ ሆኖ ሲመለከት እጅጉን ያዝናል፡፡ ይሄ ደግሞ ከሱንና መስመር ያፈነገጡ አንጃዎች ብቻ የሚወቀሱበት አይደለም፡፡ እውነት እንነጋገር ከተባለ በሱንና ስም በሰለፊያ ስም የሚንቀሳቀሰው እራሱ በሚያሳዝን ሁኔታ በተጨባጭ ለተውሒድ ትምህርት የሰጠው ትኩረት ለተውሒድ የሚመጥን፣ ህዝባችን ያለበትን ችግር ያገናዘበ አይደለም፡፡ ይሄ ደረጃው ይለያይ እንጂ ሁላችንም ጋር የሚታይ ችግር ነው፡፡ ቤተሰቦቻችን ነገ ወይም ከነገ ወዲያ የሚያጋጥማቸው ለህልፈት የሚዳርግ ከባድ አደጋ እንዳለ ብንረዳ በእግር በፈረስ ጠብጥበን ህይወታቸውን ለማትረፍ እንጥራለን፡፡ ዘላለማዊ ህይወታቸውን በሚያበላሸው ሺርክ እንደተወረሩ እያወቅን ግን የምናደርገው ጥረት እምብዛም ነው፡፡ ምናልባት ትንሽ እንጥር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውለታቸውን ሐቃቸውን የሚመጥን አይደለም፡፡ በትንሿ ጥረታችን በቂ ነገር እንደሰራን በማሰብ ለራሳችን ዑዝር እየሰጠን እንሸውዳለን፡፡ ከሐቅም በላይ ትልቁ ሐቅ የነገ ህይወታቸውን ከሚያበላሽ ብልሹ መንገድ መመለስ ነው፡፡ ልብሳቸውን ጉርሳቸውን ማሟላት ከዚህ ጋር የሚነፃፀር አይደለም፡፡ የልጆችን ሐቅ በተመለከተም ልክ እንዲሁ ነው፡፡
አሁን ይህቺን ማስታወሻ ለመፃፍ ሰበብ የሆነኝ የሖነ የጥንቆላ አፕሊኬሽን ሙስሊሞች ሲጠቀሙት ማየቴ ነው፡፡ በዚህ በ “ሰለጠነው” ዘመን የተለያዩ መልኮች ያሏቸው ጥንቆላዎችን በስልክ ሜሴጅ፣ በዋትሳፕ፣ በፌስቡክ በየጊዜው እናያለን፡፡ ታዲያ ይሄ ነገር ከእምነታችን ጋር የሚጋጭ እንደሆነ የሚያስገነዝብ ማሳሰቢያ አልፎ አልፎ ቢታይም በየጊዜው ግን እነዚህን ቆሻሻ ጥንቆላዎች በራሱ የሚጠቀም፣ አልፎም ለሌሎች የሚያሰራጭ ሰው አለመጥፋቱ የሚደንቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ሰዎች መቼ እንደሚሞቱ የሚጠነቁል አፕሌኬሽን ሙስሊም የሆነ ሰው ያውም በረመዳን፣ ያውም በነዚህ በከበሩ አስሩ የመጨረሻ ቀናት ላይ እየተጠቀመ ማየት ምንኛ የሚያሳዝን ነው?! ሰው እንዴት በማይረባ እንቶ ፈንቶ ፆሙን፣ ሶላቱን፣ ቁርኣን መቅራቱን፣ ዚክሩን፣ ከምንም በላይ ዐቂዳውን አደጋ ላይ ይጥላል?!! እስኪ ከአላህ በስተቀር ማንስ ቢሆን የት እንደሚሞት፣ መቼ እንደሚሞት ከየት ሊያውቅ ይችላል?!! አላሁል ሙስተዓን!!
አንዳንዱ ከሆነ ጥንቆላ ስትመልሰው ይቀበልሃል፡፡ ሌላ መልክ ያለው ጥንቆላ ሲመጣ ግን እንገና ሰለባ ሲሆን ይታያል፡፡ ከገጠር ድንጋይ ጣዮች፣ ከባህላዊ ኮከብ ቆጣሪዎች፣ ከስኒ ዘቅዛቂዎች፣ ከመዳፍ አንባቢዎች፣… ስትመልሰው ይቀበልና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ኮከብ ቆጣሪዎች፣ የሰውን ልጅ መፃኢ እድል “የሚተነብዩ” አታላይ ኹራፊዮች ግን ባለ ዲግሪው ሳይቀር ይሸወድባቸዋል፡፡ ይሄ ትልቅ መክሸፍ ነው፡፡ ይሄ ከመሰረታዊ የኢስላም ግንዛቤ መራቃችንን የሚያጋልጥ ሙሲባ ነው፡፡ ስለዚህ የኢስላማችንን መሰረታዊ ርእሶች ለመገንዘብ በርትተን ልንጥር፣ የቻለም ሊያስተምር ይገባል ማለት ነው፡፡ አላህ ከሺርክ ይጠብቀን፡፡