የዘካ አወጣጥን የተመለከቱ ጥቅል ነጥቦች
የዘካህ ህግጋትን አስመልክቶ በኢልያስ አህመድ ከተዘጋጀው መጽሀፍ የተወሰደ
1. ዘካን በየአመቱ ማውጣት

ከአዝርዕት በስተቀር ያሉ የዘካ ንብረቶች ከ«ኒሷብ» እስካልጎደሉ ድርስ አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በየአመቱ የዘካህ ወጪ ይመለከታቸዋል።
2. ዘካህና ዕዳ
ዕዳ በዘካህ ላይ የሚያሳድረውን ትፅእኖ አስመልክቶ የኢስላም ሊቃውንት የተለያየ አቋም ይዘዋል። ሆኖም ሚዛን የሚደፋውን አመለካከት መጥቀሱ በቂ ይሆናል፤
2.1 ዕዳ ያለበት ሰው ዕዳውን የሚከፍልበት ጊዜ ካልደረሰ በስተቀር ከዘካህ ሒሳቡ ላይ ዕዳውን አይቀንስም። ምክንያቱም በእጁ ባለው ገንዘብ መጠቀም እስከቻለ ድረስ ዘካውን የማውጣት ሐላፊነት ስለሚኖርበት ነው። ዕዳውን የሚመልስበት ወቅት ከደረሰ ወይም ከቀረበ ግን መጠኑን ቀንሶ ሒሳቡን ያሰላል።
2.2 ሌላ ሰው ዘንድ የዕዳ ገንዘብ ያለው ግለሰብ ደግሞ በፈለገው ጊዜ በእጁ የሚያገኘውና የሚጠቀምበት ባለመሆኑ ገንዘቡ እስኪመለስለት ድረስ ዘካህ የማውጣት ግዴታ አይኖርበትም፤ በአንድ ንብረት ላይ ሁለት ዘካህ አይወጣምና! ሆኖም ገንዘቡ የሚመለስበት ጊዜ ደርሶ ባለዕዳው ዕዳውን ለማስረከብ ዝግጁ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ የዘካህ ሒሳቡ በባለንብረቱ ላይ የሚታሰብ ይሆናል።
3. ዘካህና ወርሀዊ ገቢ
ለዘካህ የደረሰ የንብረት መጠን ኖሮት ዓመት ሳይሞላው ሌላ ጭማሪ ያገኘ ግለሰብ ያገኘው የንግድ ትርፍ ወይም ከቀድሞ ከብቶች የተወለደ ግልገል እስካልሆነ ድረስ አዲስ የዘካህ ዓመት ይጀምርለታል።
በዚህም መሠረት ገቢውን የሚያጠራቅም ደሞዝተኛ ጥርቅሙ የዘካህ ኒሷብ ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ አመት መቁጠር ይጀምራል። ከዚያ በኋላ በየወሩ የሚያገኘው ደሞዝ ለየብቻው ኒሷብ ባይሞላ እንኳ አመት ሲሞላው 1/40ኛውን (2.5%) ለዘካህ ወጪ ያደርጋል።
ይህ መንገድ ለእያንዳንዱ ወር አዲስ ሒሳብ በማስላት ከአመት በኋላ በየወሩ ዘካህ ማውጣት ስለሚያስፈልገው አፈፃፀሙ ለብዙዎች አሰቸጋሪ ይሆናል።
ስለሆነም ቀላልና ገር የሆነው መንገድ በአመቱ መጨረሻ ላይ በእጅ ያለውን ገንዘብ ባጠቃላይ በማስላት 1/40ኛውን ማውጣት ነው። በዚህ ጊዜ የተወሰነው የገንዘብ መጠን አመት ሳይሞላው በቅድሚያ ዘካህ ይወጣለታል ማለት ነው።
ሌሎች የዘካህ አሰጣጥን የተመለከቱ ጥቅል ነጥቦች
1. ዘካህን ለዘመድ መስጠት፦ ማስተዳደሩ ግዴታ ላልሆን ዘመድ ዘካህን መስጠት ይፈቀዳል። ወጪያቸውን መሸፈን ግድ ለሚል የቅርብ ዘመዶች መስጠቱ ግን ወጪን በማስቀረት እራስን መጥቀም በመሆኑ የተከለከለ ይሆናል። በዚህም መሠረት ለወላጆች፣ ለልጆችና ለሚስቶች ዘካህ መስጠት ይከለከላል።
2. የአላህ መልዕክተኛ ቤተሰቦችና ዝርያዎች፦ የዘካ ገንዘብን መቀበል አይችሉም።
3. ሙስሊም ላልሆነ ሰው ዘካህ መስጠት አይቻልም። ከዘካ ውጪ ያለ ተራ ምፅዋት መሰጠት ግን አይከለከልም ።
4. ዘካህ ግዴታ የሆነበት ሰው ወቅቱ ከደረሰ በኋላ በቂ ምክንያት ሳይኖር ማዘግየት የለበትም።
5. የሁለት ዓመት ዘካህ አስቀድሞ ማውጣት እንደሚፈቀድ የሚያሳይ ሀዲሣዊ መረጃ አለ።
6. ዘካህን ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር ማሻገር፦ ይበልጥ ጥቅም የሚያስገኝ ከሆነ እንዲሚፈቀድ በርካታ ሊቃውንት ይጠቅሳሉ