Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሚለፉለትን ነገር ይወቁ።

የሚለፉለትን ነገር ይወቁ።
ስራ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኘው ለአላህ ብቻ ተብሎ የተሰራና በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና መሰረት ሊሆን ግድ ይለዋል። አለበለዚያ ትርፉ አመድ አፋሽ መሆን ነው። ዋና ለዛሬ ማንሳት የፈለግኩት ረመዳን ላይ በዲን ስም ስለሚሰሩ ቢድአ (በዲን መሰረት የሌላቸው) ፈጠራዎች ነው በአላህ ፍቃድ።
ዚክርን የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ባልደነገጉት መንገድ እና ሁኔታ መፈፀም እራሱ ስራውን አላህ ዘንድ ውድቅ ያደርገዋል። ለዚህም ማስረጃው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ ነው "የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (ውድቅ ነው)"። ታድያ አንተ/ቺ የአላህ ባርያ ሆይ! በየመስጂዱ በጀመአ ኢማሙ እያወጣ መእሙሙ እየተቀበሉ
1) አሽሀዱ አን ላ ኢላሃ ኢለላህ፣ አስተግፊሩላህ፣
2) ነስአሉከል ጀነተ ወናኡዙ ቢከ ሚነናር፣
3) አስተግፊሩላህ 100 ጊዜ
እና የመሳሰሉትን።
ልብ በሉ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ከላይ ያሉት ትክክለኛ ዚክሮች ሽርክ የሌለባቸው የተውሂድ ቃላቶች ከመሆናቸውም ጋር ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲፆሙ እነዚህን ዚክሮች አገራችን ላይ እንደምናየው አይሉዋቸውም ነበር። የእኛ ትእዛዝ የሌለበት ስራ የሰራ ሰው ስራው ውድቅ ነው ባሉት መሰረት እነዚህ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው ያልሰሩትን በመስራት ወደ አላህ እቃረባለሁ ብሎ የሚያስብ ካለ በነፍሱ ላይ እየፈረደ ነውና ሳይመሽበት ይቶብት።
ፆምና ሌሎች ኢባዳዎችን አጥፊ የሆነው ደግሞ አንዳንድ መስጂዶች ላይ
1) "አጊስና ያረሱለላህ" (አጠጡን አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ)
2) "ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላህ" (አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እጄን ያዙኝ)
እንግዲግ እነዚ 2 ስንኞች እና መሰሎቻቸው ለብቸኛው ፈጣሪ አላህ ብቻ የሚገባውን ፀሎት ፍጡር ለሆኑት ነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የሚሰጡ ናቸው። ሽርክ ማለት ደግሞ አላህንም እያመለኩ ሌሎች አካላትን (መላእክት፣ ነብይ፣ ሰሃባ፣ ሷሊሆችን፣ ጂን -------) አብሮ ማምለክ ነው። በአላህ ላይ እያጋራ የሞተ ሰው የእሳት ነው። በአላህ ላይ ለሚያጋራ ሰው ፆምም፣ ሀጅም አይጠቅመውም ስለዚህ የሽርክን አደገኝነት ተገንዝበን ማህበረሰቡን እንደ ሰበብ እናንቃ።
ዲናችን ሀብታችን ነውና ስራችንን በኢኽላስና በሱና በማስጌጥ፣ ከሽርክና ቢድአ ከነባለቤቶቻቸው በመረቅ ለነፍሳችን እንዘን።
ሽርክና ቢድአ አደጋቸው ከባድ ነው።