Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መኪና ላይ ሙስበሃ ; አያተል ኩርሲ ማንጠልጠል? ....

መኪና ላይ ሙስበሃ ማንጠልጠል?
መኪና ላይ አያተል ኩርሲ ማንጠልጠል?
መኪና ላይ ‹‹ማሻ አላህ›› ብሎ መፃፍ?
መኪና ላይ የአላህ 99 ስሞች ያሉበት የተቀጣጠሉ ሬክታንግሎች ማንጠልጠል?
አስገራሚው ሹፊሩ ፍሪን ሲይዝ የአላህ ስሞች የተባለው ጌጥ ከመስታወት ጋር እየሄደ ይላተማል፡፡ ሱብሃነላህ ሸይጧን ምን ያህል የሰው ልጆችን ለነሱ ያሰበና ሃይማኖታቸውን ያከበሩ በማስመሰል ስም እየተጫወተባቸው ይገኛል፡፡ ትልልቅ ኤፍ ኤስ አር እና አይሱዙዎች ላይ የጭቃ መከላከያ ላይም አንዳንዴ ሲፃፍ ይታያል፡፡ ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን፡፡
ይህ ሁሉ ምን ይሆን ሸሪዐዊ ማስረጃው?
እኛ መጓጓዣ ላይ ስንወጣ የታዘዝነው
سُبْحَٰنَ ٱلَّذِى سَخَّرَ لَنَا هَٰذَا وَمَا كُنَّا لَهُۥ مُقْرِنِينَ
«ያ ይህንን የማንችለው ስንኾን ለእኛ ያገራለን ጌታ ጥራት ይገባው፡፡
وَإِنَّآ إِلَىٰ رَبِّنَا لَمُنقَلِبُونَ
እኛም በእርግጥ ወደ ጌታችን ተመላሾች፤ነን» (እንድትሉ)፡፡
ከዚህ ውጭ ለምን ይሆን አሳማሪዎች ነን ብለን የምናበላሸው
አላህን እንፍራ ሃይማኖታችንን ጠንቅቀን እንወቅ፡፡ ሌሎች ሃይማኖቶች መገለጫዎቻችን የሚሉትን ነገር መኪናቸው ላይ ለጠፉና እኛም መለጠፍ አለብን ማለት አይደለም፡፡
አላህ እውቀትን ይጨምርልን፣ እሱን በእውቀት ከሚያመልኩት ባርያዎቹ ያድርገን፣ አሳምራለሁ ብሎ ከማበላሸት ይጠብቀን፡፡