Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለወንድ ሱሪ መልበስ አይከለከልም!

ለወንድ ሱሪ መልበስ አይከለከልም!
ጥቂት የዋሆች በሰለፊያህ ስም ለሚሰሩት ጥፋት እርምት ይሆናቸው ዘንድ በጀምዒያ/ማህበር ጉዳይ የዑለሞች አቋም ምን እንደሆነ በተወሰነ መልኩ ማየታችን ይታወሳል።ምንም እንኳ በዚህ ርእስ ዙሪያ ድንበር ላለፉ ሰዎች የሚሰጠው ማረሚያ ባይጠናቀቅም በሌሎች ርእሶችም ድንበር ማለፋቸው ስለቀጠለ ከዑለሞች ንግግር ማስተካከያ ማቅረብ አስፈልጓል። ስለዚህም ዛሬ ስለ ሱሪ ዓሊሞች ምን እንዳሉ እናያለን።
ዓሊሞች ሱሪን ስለመልበስ ምን አሉ ...
=> በሳዑዲ አረቢያ የፈትዋና ጥናት ቋሚ ኮሚቴ በውስጡ አለም ያወቃቸው ያከበራቸው ትላልቅ ዑለማዎች የሚገኙበት ለብዙ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥ ተቋም ነው። ይኸው የዑለማዎች ኮሚቴ ለወንድ ሱሪ መልበስን በተመለከተ ለቀረበለት ጥያቄ የሰጠውን ምላሽ እንሆ ...
|||| "ሸሪዓ የነጠለው ሲቀር በአልባሳት ላይ ያለው መሰረት(አስል) በልቁ የተፈቀደ ነው! (ሸሪዓ የነጠለው ስንል) እንደ ለወንድ ወርቅ ማድረግና ሀር መልበስ -ለእከክ እና ለመሳሰሉት (በሽታዎች ለያዙት) ሲቀር- ማለት ነው። (በንጠሉን) ሱሪ መልበስ ካፊሮች የሚለዩበት አይደለም። ነገርግን ሀፍረተ-ገላ ድረስ የሰውነት አካላትን የሚያጎላ ጠባብ መልበስ አይፈቀድም፤ ለባሹ በልብሱ ከከሀድያን ጋር መመሳሰል እስካላሰበበት ድረስ ሰፊው ግን ይፈቀዳል። ልክ እንደዚሁ ኮትና ሱሪ እንዲሁም ከረቫት የከሀድያን መለያ ልብስ አይደለም። እነርሱን መመሳሰልን ለባሹ እስካልፈለገበት ድረስ ይፈቀዳል! በአጠቃላይ እንዳሳለፍነው በአልባሳት ላይ ያለው መሰረት(አስል) ሸሪዓዊ ማስረጃ መከልከሉን እስካላመላከተ ድረስ የተፈቀደ ነው። በነቢያችን ሙሐመድ በቤተሰቦቻቸውና በሶሀባቻቸው ላይ የአላህ ውዳሴና ሰላም ይስፈን" ||||
የፈትዋ እና የጥናት ቋሚ ኮሚቴ
ሸይኽ ዓብዱልዓዚዝ ቢን ባዝ >>>> ሊቀ-መንበር
ሸይኽ ዓብደረዛቅ ዓፊፊ >>>> ምክትል ሊቀ መንበር
ሸይኽ ዓብደላህ ቢን ቁዑድ >>>> አባል
ሸይኽ ዓብደላህ አል-ጉደያን >>>> አባል
ፈትዋ ለጅነቱ ዳኢማ 24ኛ ሙጀለድ ፈትዋ ቁጥር 4257
**********************************
እነኝህ የዒልም ቁንጮዎች እንዲህ ሲሉ ገና እውቀታቸው ከአባ-ስንዝሮ ደረጃ ያላለፈ ጥቂት የዋሆች 'ሱሪ በኪታብ በሱና ሐራም ነው'፣ 'ሰለፎች አላደረጉትም'፣ 'የካፊሮች ሱና ነው' የሚሉ ውዥንብሮች መንዛታቸው እጅግ አስነዋሪ ጥፋት ነው!!!
አላህ እንዲህ ይላል ...
ﻭَﻟَﺎ ﺗَﻘُﻮﻟُﻮﺍ ﻟِﻤَﺎ ﺗَﺼِﻒُ ﺃَﻟْﺴِﻨَﺘُﻜُﻢُ ﺍﻟْﻜَﺬِﺏَ ﻫَٰﺬَﺍ ﺣَﻠَﺎﻝٌ ﻭَﻫَٰﺬَﺍ ﺣَﺮَﺍﻡٌ ﻟِّﺘَﻔْﺘَﺮُﻭﺍ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟْﻜَﺬِﺏَ ۚ ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻔْﺘَﺮُﻭﻥَ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺍﻟْﻜَﺬِﺏَ ﻟَﺎ ﻳُﻔْﻠِﺤُﻮﻥَ ( ﺳﻮﺭﺓ ﺍﻟﻨﺤﻞ 116 )
"በአላህም ላይ ውሸትን ልትቀጣጥፉ ምላሶቻችሁ በሚመጥኑት ውሸት ይህ
የተፈቀደ ነው፣ ይህም እርም ነው አትበሉ፤ እነዚያ በአላህ ላይ ውሸትን የሚቀጣጥፉ አይድኑም!" ሱረቱ ነህል 116
አላህ ከዚህ ጥፋት ይጠብቀን!