Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዘመቻ ሐዳዲያ፣ ክፍል ሁለት



Ibnu Munewor
ዘመቻ ሐዳዲያ፣ ክፍል ሁለት
 ወንድማዊ ምክር የሚለው ጽሑፍ እንደ ክፍል አንድ ተቆጥሮ ነው 
ይህን ብልሹ ስሌት ተመልከቱና ታዘቡ፡፡ ከአንዱ ሐዳዲ ወል ላይ ነው የወሰድኩት፡-
**/**/**/**/**/**/**/**/**/**/**/**/
“ሲርዋል ፣፣፣፣፣ሌላ፣፣፣፣፣ሱሪ፣፣፣፣፣ሌላ
ወግ አጥባቂ መሀበርተኞች ሆይ ይሄው ከኡለማ ጋር ተጋጩ የሚያዋጣችሁ ከሆነ,,,
አንተ ሱኒይ ሰለፍይ ሆይ ሱሪና ሲርዋል የተለያዩ ናቸው እነዚህ የማሀበሯ አባላቶች እንዳያታሉህ እንዳይሸውዱህ
ተመልከት እኝህ የዘመናችን የአህለል ሱና ወል ጀማአ(ሰለፍያ)ታላቅ ኡለማ የእውቀት ፈርጥ ሸይህ አልባኒ ናቸው ረሂመሁላህ
ይህንን ቀውል ሰምተህ የነዚህ ድብቅ ጀምኢዮች ሴራና ተንኮል እወቅእ ሱሪ ሌላ ሲርዋል ሌላ ተመልከት አንተ የአላህ ባረያ ይህ የማሀበሯ አባላቶች የሚያደርጉት ማወናበድ ማደናገር መሸወድና ማጭበርበር አይደለምን?
ስማና ተረዳ ከዛ አክክ ብለህ ቱፍፍ ትላቸዋለህ ።
**/**/**/**/**/**/**/**/**/**/
ይህንን ካለ በኋላ የአልባኒን ድምፅ ለጥፏል፡፡ በነገራችን ላይ እንዲህ አይነት ፅሁፎችን እየለጠፈ የሚበጠብጠው ከኢኽዋን ከወጣ ብዙ የቆየ አይደለም፡፡ ይህን የምለው በስሙ ከሚነግድበት የሰለፊያ ግንዛቤ ‪#‎አጅነቢ‬ እንደሆነ ለማስታወስ ያክል እንጂ የቅርብ ምልስ በመሆኑ ላንጓጥጠው አይደለም፡፡ ብቻ ከላይ በፃፈው ላይ የኔ አስተያየት ይህን ይመስላል፡
1. በመጀመሪያ የአልባኒን የሱሪ ሀሳብ አለመቀበል ከቁርኣንና ከሐዲሥ ጋር መላተም አይደለም፡፡ ይሄ እሳቤ በራሱ የሱን ጥሬነት ነው የሚያጋልጠው፡፡ ቢያስብ ኖሮ እሱም “ሱሪ ይፈቀዳል” ከሚሉት ዐሊሞች ጋር እየተላተመ ነው፡፡
2. ሱሪ ከሚከለክሉት ዐሊሞች ይልቅ የሚፈቅዱት ይበዛሉ፡፡ ይሄ ከግንዛቤ ይግባ፡፡ ስለዚህ በዚህ ልጅ ስሌት መሰረት እነ ኢብኑል ዑሠይሚን “ማህበርተኞች ስውር ኢኽዋንዮች ናቸው” ማለት ነው? ነዑዙ ቢላህ ሚነል ኹዝላን፡፡
3. “ሱሪ ሐራም ነው” የሚሉት አልባኒም በሱሪ ምክንያት ሰዎችን ከሱንና አያስወጡም፡፡ “ሐራም” በሚለው የሳቸው አቋም ላይ ተንጠልጥለው ሌሎችን ከሱንና የሚያስወጡ ደፋሮች በአልባኒ ስም የሚነግዱ ስሜት ተከታዮች ናቸው፡፡
4. በመቀጠል የአልባኒ ንግግር ቁርኣን ወይም ሐዲሥ አይደለም፡፡ እናም ልክ እንደሚፈቅዱ ዑለማዎች ንግግር ለፍተሻ የሚቀርብ እንጂ የሌሎች ዑለማዎችን ንግግር የሚሽር ብቸኛ ዳኛ አይደለም፡፡
5. ከዚያም ባለፈ ይሄ የፊቅህ እንጂ የዐቂዳ ወይም የሚንሃጅ መስአላ አይደለም፡፡ በፊቅህ መስአላ ሰዎችን ከሱንና ማስወጣት የሰለፊ ሳይሆን የሙብተዲዕ አካሄድ ነው፡፡ በዚህ መልኩ እየበጠበጡም “ሐዳዲ የለም” እያሉ ሲጮሁ አያፍሩም፡፡
6. ይልቅ ሱሪ ይህን ያክል ከባድ ጉዳይ ከሆነ አሜሪካን ግቢ በየመንገዱ ዳር እየጮሁ ሱሪ የሚያከፋፍሉ ሰዎቻችሁን ቢያንስ እንዳያስፎግሯችሁ ከዚህ ንግዳቸው እንዲያቆሙ ከጩኸታችሁ ትንሽ አድርሷቸው፡፡
7. በነገራችን ላይ ለራሴ እየተከላከልኩ አይደለም፡፡ እኔ ሐራም ነው ባልልም ሱሪ ለባሽ አይደለሁም፡፡
8. በተረፈ “ወግ አጥባቂ ማህበርተኞች” የምትሉት መጃጃል እያስፎገራችሁ ነው፡፡ በቅድሚያ ወግ አጥባቂው ማን እንደሆነ ስራችሁ ይመሰክራል፡፡ በመቀጠል አብዛሀኛው እየተቃወማችሁ ያለው ሰለፊ ወጥ ረገጥ አካሄዳችሁን ስለማይደግፍ እንጂ ከማህበር ጋር ንክኪ ኖሮት አይደለም፡፡ ይልቅ ውሸታችሁ ብዙ ስለሚያስከፍላችሁ ብትተውት ይሻላል፡፡
ወንድም እህቶች!
ወላሂ እነዚህ ሰዎች ጊዜያችንን በጭቅጭቅ ላለማሳለፍ፣ አዲስ ወደ ሰለፊያ የሚጎርፉትን ላለማደናገር፣ የኢኽዋኖች መሳለቂያ ላለመሆን ብለን ብንተዋቸውም የሚገባቸው አይነት አልሆኑም፡፡ ጭራሽ ሊታገሷቸው ከሚገባው በላይ ደርሰዋል፡፡ “በአፍሪካ ቲቪ ስለታየ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ ሙብተዲዕ ነው፡፡ እሱን ሙብተዲዕ ስላላለ ኢልያስም ሙብተዲዕ ነው፡፡ ኢልያስን ሙብተዲዕ ያላለም ሙብተዲዕ ነው፡፡ የኢልያስን ፖስት ሼር ያደረገም ሙብተዲዕ ነው” የሚል የጂል ስሌት ውስጥ ተነክረዋል፡፡ ይሄ ተክፊርኛ ስሌት ነው፡፡ “አላዋቂ ሰው ሺርክ ላይ ቢወድቅ ካፊር ነው፡፡ እሱን ያላከፈረም ካፊር ነው” ከሚለው የተክፊሮች ቀመር ጋር የሚመሳሰል ቆሻሻ አካሄድ ነው፡፡ ደግሞም በእንዲህ አይነት ሂሳብ እንተሳሰባቸው ብንል ከነሱም አንድም አይተርፍም፡፡ አንዱ በሱሪ ጉዳይ ከሚንሃጅ ሲያስወጣ ሌላው ያልፋል፡፡ ሱሪ የሚያከፋፍለው አባል እዚህ ላይ አንገቱን ይደፋና በሌላ ርእስ ይበጠብጣል፡፡ አንዱ በጀምዒያ ሲያስወጣ ሌላው ያልፋል፡፡ እንዲያውም አንዳንዱ በጀምዒያ የቀረበ በግ፣ ዱቄት፣ ኡዱሒያ፣ ዘካተል ፊጥር እየጎተተ ይሄዳል፡፡ ወላሂ በአይኔ ያየሁትን ነው የምናገረው፡፡ አንዴ ሁለቴ አይደለም ብዙ ጊዜ፡፡ አንዱ የጀምዒያ መተዳደሪያ ደንብ ውስጥ ከቁርኣን ህግ ጋር የሚፃረር ኩፍር ስላለበት በሚል ከሱንና እያስወጣ በትምህርት ቤት በዩኒቨርሲቲ ሲቪክስ ይማራል ወይም ተምሯል፡፡ ሰሞኑን የሚበጠብጡትም የዚህ አካል ናቸው፡፡ ከአዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ በፌስቡክ የሚበጠብጠውም እዚያው አስተማሪ ነው፡፡ ሱሪ ለብሶ ኢኽቲላጥ ውስጥ ሆኖ ያስተምራል፡፡ ከዚያም ዞሮ ይበጠብጣል፡፡ በቃ አንዱ በኢኽቲላጥ ምክንያት ሰዎችን ከሱንና ሲያስወጣ ሌላው ከኢኽቲላጥ ቦታ ይማራል፣ ያስተምራል፡፡ አዋላጅ ነርስ ሆኖ ሁሉ የሚማር አውቃለሁ፡፡ ይሄም አያፍርም እንግዲህ “ዶሩራ ነው” ይል ይሆናል፡፡ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ፡፡” በትምህርት ጉዳይ የሚሞግታቸውን ግን “ከነ አስቴር ጋር ካልተቃቀፍኩ ነው ወይ የምትለው?” እያሉ ዝቃጭ ስነ-ምግባራቸውን ያሳያሉ፡፡ ለመሆኑ እነሱ በታክሲ በባስ ከሰፈር ሰፈር፣ ከሀገር ሀገር ሲዘዋወሩ ከነ አስቴር ጋር ተቃቅፈው ነው የሚዘዋወሩት?! ማገናዘብ፣ ጭንቅላት የሚባል ነገር ኢንጂሩ!!! አጃኢብ የሆኑ ፍጡሮች ናቸው፡፡ ቀደም ብሎ ደርሳቸውን በወክማን እየቀዳ ሲያከፋፍላቸው የነበረውም የአምስት ኪሎ ተማሪ ነበር፡፡ ከኢኽቲላጡም ባለፈ ያለጥርጥር ሲቪክስ ተምሯል፡፡ በውስጡ ዛሬ በጀምዒያ ምክንያት ከሚበጠብጡበት የባሰ ብዙ ነገር እንዳለ አይሰወርም፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን ለራሳቸው ሲሆን አንዱ ሌላውን ከሱንና አያስወጡም፡፡ “ከፊላችን ለከፊሉ ዑዝር ይስጥ” በሚለው የኢኽዋን መርህ ስለሚተላለፉ እንጂ በህጋቸው መሰረት ሁሉም ከሰለፍያ ውጭ ናቸው፡፡ በዚያ ላይ ውሸታቸው አይጣል ነው!!!!!!! ከቁንጮዎቻቸው አንዱ “ጀለቢያ ቢድዐ ነው ብለዋል” እያለ በውሸት ሌሎችን የሚከስበት ድምፅ በእጄ አለ፡፡ “ሐሰት” ካሉ እዚሁ ነው የምለጥፈው፡፡


ወንድማዊ ምክር የሚለው ጽሑፍ እንደ ክፍል አንድ ተቆጥሮ ነው  
 (ኢን ሻአላህ ክፍል ሶስት ይቀጥላል)
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 11/2008)