እውነት ነው አላህ አንድ ሁኑ ብሎናል፡፡
=====================
አላህ አንድ ሁኑ ሲለንም አሁንም የማይካድ እውነት አለ እሱም በአላህ የእምነት ገመድ ላይ ብቻ አንድ እንድንሆን ተነግሮናል፡፡ የአላህ የእምነት ገመድ ቁርዓን፣ ሱና፣ ሃቅና፣ የሰሃባዎች አረዳድን ይይዛሉ፡፡
አላህ አንድ ሁኑ ሲለን እሱን በማምለክ ላይ ምንም ልዩነት ሊኖረን አይገባም፡፡ አንዱ ‹‹ያ አላህ›› ሲል ሌላው ‹‹ያ አልይ›› ወይንም ‹‹ያ አብድል ቃድር ጀይላኔ›› ወይንም ‹‹የ ቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ›› ካለ ይህ በፍፁም አንድነትን ሊያመጣ አይችልም፡፡ ይህን እና መሰል አንድነቶችን አላህ አላዘዘባቸውም፡፡

አላህ ያዘዘን አንድነት የሱን ብቸኛ ጌትነት፣ ብቸኛ አምላክነት፣ ለእርሱ መልካም ስምና ባህሪያቱን በማፅደቅ፣
የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና እንደ ብቸኛ ዋስትና በመቀበል መጤ በዲን ላይ የተጨመሩ ቢድዐዎችን በመራቅ፣
የሰሃባዎችን (የሰለፉነ ሷሊሂንን 3ቱ ምርጥ ትውልዶች እና ክፍለ ዘመን) አረዳድ በመያዝ ላይ ብቻና ብቻ ነው፡፡
ሀቅ አንድ ብቻና ብቻ ናት የእኛም ግዴታ እሷን ብቻ መከተል ነው፡፡ ይህችም ሃቅ ታማኙ ነብይ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንደጠቀሷት ‹‹እኔና ባልደረቦቼ (ሰሃባዎች) ዛሬ ያለንባት መንገድ ናት›› ብለዋል፡፡
ስለዚህ ስለ አንድነት ስናስብ መጀመርያ አንድነቱ በምን ላይ እንደሚመሰረት ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባናል፡፡ ሰላት ለመስገድ መስፈርት እንዳለው ሁሉ አንድነትና ወንድማማችነትም አምልኮ ኢባዳ ነው፡፡ ከማን ጋር አንድ እንደምንሆን፣ ከማን ጋር ወንድማማች እንደምንሆን ከማን ጋር እንደማንሆን ጠንቅቀን ልናውቅ ይገባናል፡፡
ለምሳሌ ሺዓዎች፣ ቀደርያዎች፣ ሙዕተዚላዎች፣ አሽአርዬች፣ ማትሩድዬች፣ ኸዋሪጆች፣ ሱፍዬች እና በዘመናችን የመጡም የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና የሰሃባዎችን መንገድ የተቃረኑ ቡድኖች ጠቅላላ አንዷን የሃቅ መንገድ ስተዋልና ከነዚህ ጋር አንድ ነን ሳይሆን የሚባለው እነዚህ ቡድኖች ወደ አንዷ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው ወደ ነበሩበት እምነት ሊመለሱ ብቻና ብቻ ነው የሚገባቸው፡፡
እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው አንድ ዋና ነጥብ አለ እሱም ከላይ የተጠቀሱት መጤ፣ አዲስ መንገድ የሳቱ ቡድኖች ስህተት መሆናቸው ሲነገር አንዳዶች ‹‹አትለያዩን፣ አትበታትኑን›› ይላሉ፡፡ በብዛት ካለማወቅ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድነት የሚመሰረተው ከማን ጋር እንደሆነ አላወቁም እነዚህ ወንድም እና እህቶች፡፡ አንድነት የጥንት የወዋቷን መንገድ ከተከተሉ ጋር ብቻ እንጂ መጤ መንገዶችን ከሚከተሉት ጋር አይደለም፡፡ መጤ መንገድ ላይ ያሉትማ መጤ አካሄዳቸውን ትተው ወደ 1ዷ ብቸኛ የሃቅ መንገድ መመለስ አለባቸው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው የነበሩበት መንገድ እስከ ቂያማ ድረስ፣ ለማንኛውም ቦታ፤ ለማንኛውም ዘመን፣ ለየትኛውም የእድሜ፣ ለየትኛውም ማህበረሰብ ብቁ፣ ምቹ፣ ሁሉን ያሟላ፣ ምንም የማይጎድለው አላህ ዘንድ የተመረጠልን፤ አላህ ፀጋውን የሞላልን እንት ነውና እሱን ብቻ እንያዝ፡፡ በዚሁም መንገድ ላይ ብቻ አንድ ሆነን እንተሳሰር፡፡ አዳዲስ የጥመት ቡድኖችን ርቀን፣ ተጠንቅቀን፣ አስጠንቅቀን፣ በዚሁ መንገድ ላይ አላህ እንዲገድለን እየለመን መኖር አለብን፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًا
ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡
ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ) ይህ አንቀፅ ሲያብራሩ ያን ቀን (ይህ አንቀፅ የወረደ ቀን)ዲን ያልነበረ ዛሬ ዲን ሊሆን አይችልም፡፡
ታድያ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሃቅ አንድ ብቻ ከሆነች ለምን እሷ ላይ ብቻ አንሰባሰብም ?
ለምን ሃቅን (1 ዷን ብቸኛ መንገድ) ከባጢል (ጨለማዎች ከሆኑት የጥመት መንገዶች) መደባለቅ አስፈለገ ?
አላህ ሆይ! እውነተኛ አንድነት ስጠን፡፡ አንተን አንድ አድርገን በማምለክ ላይ ካንተ ውጭ ባሉት በመካድ ላይ፣ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱናን በመከተል ላይ ከዛ ውጭ ባሉት መጤ ቢድኣዎችን በመራቅ ላይ፣ ቁርዓንና ሀዲስን ሰሃባዎችና ምርጡ 3 ትውልድ በተረዳው መሰረት ላይ የተመሰረተ አንድነት ስጠን፡፡ ላንተ ብለው ከተዋደዱት ላንተ ብለው ከጠሉት አድርገን፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው፣ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡