Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ትዝብት!

ትዝብት!
እስኪ ላፍታ ቆም በሉና የናንተንና የሙስሊሞችን ሁኔታ ላይ ታቹን አማትሩት፤ ነቢዩ (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እና እነዚያ ምርጥ ሶሀቦች ከነበሩበት ዘመን ጋር አስተያዩት።
እውን እኛ እነርሱ በተጓዙበት መንገድ ላይ ነን?
ካስተዋላችሁ ግን!ሁኔታው የተገላቢጦሽ ሁኖ ታገኙታላችሁ። ብዙዎች ዘንድ መጠን ያለፈ አላዋቂነት ተንሰራፍቶ፣ ያለማወቅ ድር ሁለመናቸውን ተብትቦት ዝንጉነትና ስንፍና አከናንቧቸው ይገኛል።
ሙስሊሞች ከየአቅጣጫው በተለያዩ ፈተናዎች ማዕበል እየተናወጡና በጭንቅ ተወጥረው ሲዋልሉ በአደገኛ አውሎ ንፋስ ሲማቱ ታያለህ።
ፈተና እንደማይቀርልን ተነግሮን ሳለ ብዙዎች ግን በንፋሱ ሲወድቁ በማዕበሉ ሲሰምጡ ታዝበናል፦
ይህ የጌታችን ቃል ወዴት ተሰውሮብን ይሆን?
أَحَسِبَ النَّاسُ أَن يُتْرَكُوا أَن يَقُولُوا آمَنَّا وَهُمْ لَا يُفْتَنُونَ
«ሰዎቹ አምነናል በማለታቸው ብቻ እነሱ ሳይፈተኑ የሚተው መኾናቸውን ጠረጠሩን?» (69-2)
ታዘብ! እዚህ ጋር ደግሞ ሌላ ነቀርሳ አለ! ዛሬ አፈንጋጮች በዝተዋል፤ ሰዎችም ከነቢዩ ነቢዩ(ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ይልቅ ግለሰቦችን የሙጥኝ ብለው በጭፍን መከተልን ተያይዘዋል ለእነርሱ ሸሂድ ሊሆኑ ምለው ተገዝተዋል! ስህተታቸውን ላለማየት አይናቸውን በጥቁር ጨርቅ ሸፍነው እጆቻቸውን በጆሯቸው ጨምረዋል። ሱናን ትተው ቢድዐ ውስጥ ተዘፍቀዋል። ሸይጧን ስራቸውን አሳምሮ ከቀጥተኛው መንገድ አስፈንጥሮ ሊያወጣቸው ወደ ራሱ መጎተቱን አጠናክሮ ቀጥሏል! ይህን የቁርአን አያህ(አንቀፅ) እንዳያስተነትኑ ጋርዶባቸዋል፦
«በሦራዎች ከሳሪዎቹን እንንገራችሁን» በላቸው(103) እነዚያ እነሱ ሦራን የሚያሳምሩ የሚመስላቸው ሲሆኑ በቅርቢቱ ህይወት ሦራቸው የጠፋባቸው ናቸው።(104)»
(18:103–104)
ሌሎች ደግሞ በመሰረተቢስ እምነቶች ተተብትበው ዳግም ወደ ሽርክ ነጉደዋል። ተውሂዱ ሽርክ ሆኖባቸው የአላህ ብቸኝነት ሲወሳ ፊታቸው ይቀላል ፣ አካላቸው ይንቀጠቀጣል! በሽታቸው ይቀሰቀሳል!
ባዕድ አምልኮ በከፊል አንጃዎች ውስጥ ነፍስ ዘርቷል ብሎም እንደ ሰደድ እሳት ስር ሰዶ ተንሰራፍቷል።
በዚህም ምክርያት የሙስሊሞች አንድነት ተንዶ ፣ ብርቱ የነበረው ክንዳቸው ዝሎ ፣ አስፈሪ የነበረው ድምፃቸው ሲቃ ሆኖ በሚያሳዝን ሁኔታ በካፊሮችና ጠላቶቻቸው መጫወቻ ሁነው አንግተዋል።
በጉልበትም በባህልም ተወረዋል። ማንነታቸውን ዘንግተውና አፍረውበት በዲናቸው ተሸማቀዋል! ሙስሊም ተብለዋል እንጂ በእስልምናቸው አፍረው ዲኑን እርግፍ አድርገው ትተዋል ።
ወደ ሱና የተጠጋ፣ተውሂድ ላይ የቆመም እንደ እንግዳ ታይቷል። በል እንደ መጤ እንግዳ ለሀገሩ ባዳ እንደሆነ ሚስኪን መንገደኛ መጠጊያ አጥቷል፦
መልዕክተኛው እውነትን ተናገሩ! እንዲህ ብለው ነበር፦
«ኢስላም እንግዳ ሆኖ ነው የጀመረው ወደፊትም እንግዳ ሁኖ ይመለሳል፤ እንደ እንግዳ ለሚታዩት ጡባ(ጀነት) አለችላቸው»
[አልባኒ ሰሂህ ነው ብለዋል]
ዛሬ ብዙዎች የተፈጠሩበትን አላማ ረስተዋል፣ አኼራንም ዘንግተዋል። አላህን መታዘዝ ኋላ ቀርነት መስሏቸው የመልእክተኛው ሱና አሸማቋቸው በማመጽ ስይጣኔ ተኮፍሰዋል በቢድዓ ብልጭልጭ ተሸልመዋል። አላህ እብዲህ ብሏል መልዕክተኛው እንዲህ ብለዋል የሚል ቃል እጅ እጅ ብሏቸው የፍልስፍናና የፈላስፎች ንግግር ጣፍጧቸዋለል!
መሀይምነት ወርሷቸው ኋሊዮሽ በፍጥነት ተጉዘዋል። የጀነት ትኬት እንደደረሰው ዒባዳን ትተዋል። አላህን ሳይሆን (ረመዷን) ወርን አምላኪ ሁነዋል! ገሩን ዲን አክብደው ከባዱን ወንጀል አቅለዋል።
ውድ ወንድሜ/እህቴ! እስኪ መለስ እንበልና ራሳችንን እንገምግመው።
የቱ ጋር ነን?!
(አቡ ሀማድ ሀምሌ 25/07)

Post a Comment

0 Comments