Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቀብር ላይ መስገድ እና ለሞቱ ሰዎች መስዋት ማቅረብ እንዴት ይታያል?


ቀብር ላይ መስገድ እና ለሞቱ ሰዎች መስዋት ማቅረብ እንዴት ይታያል?

ጥያቄ፡- ለቀብር መስገድና መስዋትን ለመቃብር ባለቤቶች ማቅረብ ሸሪዐዊ ፍርዱ ምንድን ነው?
መልስ፡- ለቀብር መስገድ እና መስዋትን ለሟቾች ማቅረብ ባእድ አምልኮ፤ መሀይምነትና፤ ታላቁ ሽርክ ነው፡፡ አነዚህ ተግባሮች ልዩ የሆኑ ለአላህ ብቻ የሚገቡ ናቸው፡፡ ይህን ተግባር ከአላህ ውጭ ላለ የሚያደርግ ሙሽሪክ ነው፡፡ አላህም እንዲህ ይላል
قُلْ إِنَّ صَلَاتِى وَنُسُكِى وَمَحْيَاىَ وَمَمَاتِى لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ
لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ
‹‹ሰላቴም፤ እርዴም፤ ህይወቴም፤ ሞቴም ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ነው በል (ያ ሙሃመድ)፡፡ ሸሪካም የለውም በዚህም ላይ ታዝዣለሁ እኔም የመጀመሪያው ሙስሊም ነኝ››

አላህ በመቀጠል እንዲህ ይላል
إِنَّآ أَعْطَيْنَٰكَ ٱلْكَوْثَرَ
فَصَلِّ لِرَبِّكَ وَٱنْحَرْ
‹‹(ያ ሙሃመድ) ከውሰርን ሰጥተንሃል፡፡ ለጌታህም ስገድ ለእርሱም እረድ››

ሌላ በርከት ያሉ የቁርዐን አንቀፆች አሉ፤ስግደትና ምስዋት የአምልኮ ክፍል መሆናቸውን የሚያመለክቱ፤ ከአላህ ውጭ ማድረግም ሽርክ ይሆናል፡፡ ያለ ምንም ጥርጥር ቀብርን ለስግደትና መስዋትን ለቀብር ለማድረግ ብሎ መዘየር ባላቤቶች ለማላቅና ለማምለክ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ለዚህም ሲባል የአላህ መልዕክተኛ ኢማሙ ሙስሊም ከአልይ ኢብን አቡ ጧሊብ (አላህ ይውደዳቸውና) ይዘው እነደዘገቡት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ ‹‹አልይ የአላህ መልዕክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው አስተማሩኝ ይላል፤ አላህ ይርገመው ከአላህ ውጭ ላለ ያረደ፤ አላህ ይርገመው ወላጆቹን የሚረግም፤ አላህ ይርገመው ቢድዐ የሚሰራን ሰው ያስጠጋ፤ አላህ ይርገመው የመሬትን ድንበር ልኬት ያጭበረበረ፡፡››

አቡ ዳውድ በዘገቡት ሀዲስ ሳቢት ኢብን ደሀሀክ (አላህ ይውደዳቸውና) እንዲህ ይላሉ ‹‹አንድ ሰው ቡዋናህ የሚባል ቦታ ስለት የገባውን ግመል መስዋት ማቅረብ ፈለገ፡፡ የአላህ መልክተኛንም እንደሚፈቀድና እንደማይፈቀድ ጠየቃቸው፤ አሳቸውም እንዲህ በማለት ጠየቁት ፤ በጃሂልያ ወቅት የነበሩ ጣዖቶች ቦታው ላይ ይመለኩበት ነበር ወይ? እነሱም አይመለኩም ነበር ብለው መለሱ፤ አሁንም የአላህ መልዕክተኛ ጠየቁ፤ ሙሽሪኮች (ጣዖት አምላኪዎች) እዚህ ቦታ ላይ ባዐላቸውን ያከብሩበት ነበር ወይ? እነስም አያከብሩም ነበር በማለት መልስ ሰጡ፡፡ ይህን ከሰሙ በኋላ ስለትህን ሙላ ምክንያቱም አላህ በሚታመፅበት ጉዳይ ላይ ስለት መሙላት የለም ብለው መልስ ሰጡ፡፡››

ያለፉት ሀዲሶች እንደሚያመለክቱት ከአላህ ውጭ ላለ የሚያርድ ሰው አላህ የረገመው ነው፤ ሌላው ከአላህ ሌላ የሚመለክበት ቦታ ላይ እርድን መፈፀም እንደማይቻል ቀብርም ይሁን ጣዖት፤ ከዚህም አልፎ የጃሂልያ ስርዐተ በዐል የሚከበርበት የነበረውን ቦታ ለዚህ ጉዳይ መያዝ አይቻልም፤ ምንም እንኳን ሰውየው ለአላህ ብዮ ነው የነየሁት ቢልም፤ አላህ በመልዕክተኛው ላይ ሰላትና ሰላም ያውርድ፡፡ (የሳውዲ ፈትዋ ኮሚቴ)
ግልፅ የሆነ የአላህ አንቀፅ እንመልከት
وَمِنْ ءَايَٰتِهِ ٱلَّيْلُ وَٱلنَّهَارُ وَٱلشَّمْسُ وَٱلْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا۟ لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَٱسْجُدُوا۟ لِلَّهِ ٱلَّذِى خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ
‹‹ሌሊትና ቀንም፤ ፀሀይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፤ ለፀሀይና ለጨረቃ አትስገዱ፤ ለዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ፤ እርሱን ብቻ የምትገዙ እንደ ኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)››

የአላህ ባሪያዎች ከአላህ ወጭ መላኢካንም (እንደ ጂብሪል ያለ)፤ ነብይም ይሁን (እንደ ኢሳ እና ሙሀመድ ‹ሰላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይሁን›፤ ከዛ በታች ደረጃ ያላቸውም ሷሊሆች ይህንን የአላህ መብት ሊጋሩት አይችሉም እነሱም ፍጥረታት ስለሆኑ ከሱ ከጃዮች ናቸው፡፡

አላህ እስልምና የበላይ ያደርጋት ዘንድ እለምነዋለሁ፡፡ እውነት የበላይ የሚሆንበትን ወቅት አላህ እንዲያሳየን እለምነዋለሁ፡፡ ህዝበ ሙስሊሙሙ ከእንደዚህ አይነት እውቀት ከሌላቸውና የመልክተኞችን ፈለግ ከማይከተሉ ሰዎች ፈተና አላህ ይጠብቀው፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በመጨረሻው ነብይ፤ በሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ ላይ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸውና የሳቸውን ፈለግ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን አሜን!