Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለረመዷን ይሰግዳል በሌሎች ወራት መስገድ ይተዋል!



ለረመዷን ይሰግዳል በሌሎች ወራት መስገድ ይተዋል!
ጠያቂ: – “ረመዷንን ወር ላይ ሰላት ይሰግዳል የሸዋል ስድስቱን ቀናትም ይፆማል ። ሆኖም ከረመዷን በህዋላ መስገድ ያቆማል፤ መጠጥም ይጠጣል፤ ዝሙትን ይፈፅማል ። ብይኑ ምንድር ነው? ከኛ ጋር ያለው አብዛኛው ህዝብ ይህን ይመስላል ። ስንመክራቸውም (ምክራችንን) አይቀበሉም”
መልስ ታላቁ የየመን ዐሊም ከነበሩት ሸይኽ ሙቅቢል (ረሒመሁላህ) :–
« በትክክለኛው የእውቀት ባለቤቶች አቋም መሠረት ይህን የሚያደርግ ግለሰብ ከሃዲ (ካፊር) ነው። ይህም የሆነው (ቀጥሎ ባለው) የመልዕክተኛው ሰለላሁ ዐለይሒ ወሰለም ሐዲስ መሠረት ነው: –
(( (በአላህ) ባሪያና በአጋሪዎች መካከል ምንም የለም ሰላት ቢሆን እንጂ ። (ሰላትን) የተወ ክዷል ።))
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሒ ወሰለም: – (( በኛና በነርሱ (አጋሪያን) መካከል ያለው ግርዶሽ ሰላት ነው።))
ነዐም! በመጀመሪያው ሐዲስ ላይ (በስሕተት) ጨምሬበታለሁና በድጋሚ እለዋለሁ ..
(( በባሪያና በክህደት፣ በሽርክ መካከል ምንም የለም ሰላት እንጂ))
(( በኛና በነርሱ (በአጋሪያን)) መካከል ያለው ግርዶሽ ሰላት ነው። (ሰላትን) የተወ ሰወ ክዷል።))
የላቀውና አሸናፊው ጌታችን አላህ በተከበረው መፅሃፉ እንተገለፀው አንዳንድ ምዕመናን ለጀሃነም ሰዎች እንዲህ ሲሉ ይጠይቋቸዋል:–
{{ ما سَلَكَكُمْ فِي سَقَرَ ٤٢ قَالُوا لَمْ نَكُ مِنَ الْمُصَلِّينَ ٤٣}}
{{ (ምዕመናን ይሏቸዋልም)፦ “በስቀር (ጀሃነም) ውስጥ ምን አገባችሁ?”
(እነርሱም) ይላሉ፦ “ከሰጋጆቹ አልነበርንም።”}} [ሙደሲር 42–43]
በተጨማሪም የላቀውና አሸናፊው ጌታ እንዲህ ይላል: –
{ {فَخَلَفَ مِنْ بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا } }
{{ ከነሱም በኋላ ሶላትን ያጎደሉ፣ (የተዉ)፣ ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ።}} [ መርየም 59]
እናም የላቀውና አሸናፊው እንዲህ ይላል: –
{{ فَوَيْلٌ لِلْمُصَلِّينَ ٤ الَّذِينَ هُمْ عَنْ صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ ٥}}
{{ ወዮላቸው ለሰጋጆች፤ ለነዚያ እነሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት።}} [አልማዑን 4–5]
እና የላቀውና አሸናፊው ጌታ እንዲህ ይላል: –
{{ فَإِنْ تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّين}}
{{ ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ ዘካንም ቢሰጡ፣ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው }} [አትተውባህ 11]
ከአንቀፁ የምረዳው ሰላትን የማይሰግዱ እንደሆን የእምነት ወንድሞቻችን አይደሉም ማለት ነው ። »
ምንጭ: – Source: http://muqbel.net/fatwa.php?fatwa_id=1467
ፈትዋውን በድምፅ ለመስማት ከታች የሚገኘውን አስፈንታሪ በመጫን ደ ውንሎድ አድርጋቹ ማድመጥ ተችላላቹ ። ባረከላሁ ፊኩም
https://phaven-prod.s3.amazonaws.com/…/HA-XUFC9iNA4FKks_5An…
ማስታወሻ: – ከላይ ያለውን ያነበበና በአላህ ቅጣት ማስፈራሪያ ያለተገሰፀ በምን ይገሰፃልን? አንተ ወጣት ሆይ! አንቺ ወጣት ሆይ! ይህን ረመዳን ለለውጥ ካልተተቀምነው መቼና የት ይሁን ከአላህ የምንታረቀው?
አላህ በሰላታቸው ላይ ቋሚዎች ያድርገን