Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ: ―ሴት ልጅ ፈጣሪዋን በአግባቡ ለማምለክ እና ቤተሰቦቿን ከማገልገል አንፃር በረመዷን ሊኖራት የሚገባው ፕሮግራም ምንድን ነው? ሸይኽ ሱለይማን አሩሀይሊ





 ام محمد
ሸይኽ ሱለይማን አሩሀይሊ ረመዷንን አስመልክቶ የሚከተለውን ጥያቄ ተጠይቀው ሲመልሱ
ጥያቄ: ―ሴት ልጅ ፈጣሪዋን በአግባቡ ለማምለክ እና ቤተሰቦቿን ከማገልገል አንፃር በረመዷን ሊኖራት የሚገባው ፕሮግራም ምንድን ነው?
መልስ:― የሴት ልጅ ፕሮግራም ከወንድ ልጅ ፕሮግራም ጋር ተመሣሣይ ከመሆኑም ጋር ሴት ልጅ በተጨማሪ የምትሰራቸው የአምልኮ ተግባራት አሉ እነሱም
ሴት ልጅ ባሏን እና ቤተሰቧን በማገልገል ላይ ጥረት ካደረገች ለነሱ የሚበቃቸውን ምግብ ካዘጋጀችላቸው በኢባዳ ላይ እንዳለች ነው የሚቆጠረው ። ባይሆን በዚህ ስራዋ ከአላህ ዘንድ አጅር ማግኘትን ተስፋ ካደረገችበት ነው ።
ይህ ተግባር የአጅር ማግኛዋ እና ከአላህ የምታገኘውን ምንዳዋን ማብዣ ነው። ሴት ልጅ ምግብ በምታዘጋጅበት ሰዓት ምላሷን በዚክር የተጠመደ ልታደርግ ይገባታል
―ሱብሀን አላህ እያለች ታበስላለች
―ላኢላሀኢለሏህ እያለች ታበስላለች
―ሌሎች ዚክሮችንም እያለች ምግቧን ታዘጋጃለች።
ይህን በማድረጓም ከአላህ ዘንድ ትልቅ አጅርን ታገኝበታለች። በረመዷን ቀን ምግብ ማዘጋጀቷ አላህ ሱብሀነወ ተአላን ለመገዛት አያግዳትም።
ሙስሊም ሴት ምንኛ የታደለች ናት! ያቺ ባሏን እና ቤተሰቧን በማገልገል ከአላህ ሱብሀነወ ተአላ አጅር ማግኘትን ተስፋ ከማድረጓም ባሻገር በስራዋ ላይ ሆና አላህ ሱብሀነወ ተአላን ከማውሳት የማትዘናጋ እና በረመዷን ቀን የምትችላቸውን የአምልኮ ተግባራት የምተገብር የሆነችዋ
ይህቺ አይነቷ ሴት በእርግጥም ትልቅ የሆነ እድለኝነትን ተጎናፅፋለች።


ምንጭ ከረመዷን ፊት ለፊት በሚል ርዕስ ከዘጋጁት ትምህርታቸው የተወሰደ