Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢኽዋኖች በረመዳም አፍጥር ሰዓት ኡማውን ከዱኣ አዘናግተው

ኢኽዋኖች በረመዳም አፍጥር ሰዓት ኡማውን ከዱኣ አዘናግተው
1) ገመድ ጉተታ፣
2) ዳርት፣
3) እግር ኳስ ጨዋታ
ብለው ኡማው በፆም አንቅሮ የተፋውን አስልመው ሊያመጡለት ነው።
ገርሞ የሚገርመው ደግሞ እነሱ በአደባባይ ይህን ቢድአቸውን በረመዳን እያሰራጩ፣ እኛ ከነሱ ስናስጠነቅቅ የሚከተለውን የሚሉ ደፋሮችን ማየታችን ነው
1) በድብቅ ምከሯቸው፣
2) ቀንታችሁ ነው (አሁን እርኩሱ ቢድአ ምኑ ተቀንቶበት ይሆን?)፣
3) በረመዳን ሀሜት አይደብራችሁም (ምስጋና ይገባው ይሄ ሀሜት አይደለም በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል እንጂ። ሌላው በረመዳን ቢድአቸውና ጥመታቸው የባሱትንስ ሰዎች ምነው ዝም አሏቸው?)

ሊታወቅ የሚገባው የሱና ሰዎች የቢድአ አራማጆች ቢድአቸውን ሲረጩ ዝም አይሏቸውም። መልስ ይሰጥባቸዋል ወደ ሱና እስኪመለሱ ድረስ።
ሙስሊሞች ሆይ! ወደ ቂያማ እየቀረብን ነው። ከረመዳን ውጭ ሙስሊሙን እያዘናጋ ያለውን ኳስ በረመዳን ያውም በአፍጥር ሰአት አላህ እየተለቀሰ በሚለመንበት ሰአት ይህን መሟዘዛቸውን ካላሳየን የሚሉ አታላዩችን ተጠንቀቁ።
አላህ ከሸራቸው ይጠብቀን።